3 months ago
የሂትሮው አውሮፕላን ማረፊያ በኢራን ጦርነት ምክንያት የመንገደኞች ቁጥር ሊቀንስ እንደሚችል አስጠነቀቀ
*************
የለንደኑ ሂትሮው አውሮፕላን ማረፊያ በኢራን ጦርነት ሳቢያ በተፈጠረው አለመረጋጋት በዘንድሮው የፈረንጆቹ ዓመት ቀሪ ወራት የመንገደኞች ቁጥር ሊቀንስ እንደሚችል ማስጠንቀቂያ ሰጠ።
አውሮፕላን ማረፊያው ባወጣው የንግድ ሪፖርት መሠረት፣ በመካከለኛው ምሥራቅ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ በአየር ጉዞ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እያሳደረ ይገኛል።
እንደ ቢቢሲ ዘገባ ጦርነቱን ተከትሎ በየቀኑ ግማሽ ሚሊዮን የሚጠጉ መንገደኞች የሚስተናገዱባቸው እንደ ዱባይ፣ ዶሃ እና አቡ ዳቢ ያሉ የትራንዚት ማዕከላት ጫና አርፎባቸዋል።
ከዚህ ጋር ተያይዞ በአሜሪካ የሚገኘው ስፕሪት አየር መንገድ (Spirit Airlines) በከፍተኛ የነዳጅ እጥረት ምክንያት ሁሉንም በረራዎቹን ማቋረጡንና ሥራ ማቆሙን ፎክስ ኒውስ ዘግቧል።
ይህ ውሳኔ በሺዎች የሚቆጠሩ ሠራተኞችን ከሥራ ውጭ ያደረገ ሲሆን፣ በአሜሪካ የአየር ትራንስፖርት ዘርፍ ላይ ትልቅ ድንጋጤ ፈጥሯል።
ከስፕሪት በተጨማሪ ሌሎች ታዋቂ ዓለም አቀፍ አየር መንገዶችም በነዳጅ ዋጋ መናርና በአቅርቦት እጥረት ምክንያት የበረራ መርሐ-ግብሮቻቸውን ለመቀነስና መስመሮቻቸውን ለማጠፍ መገደዳቸው ተመልክቷል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቅርቡ ምንም እንኳን በርካታ የዓለም አቀፍ አየር መንገዶች አሁን ባለው የነዳጅ ቀውስና ጂኦ-ፖለቲካዊ ውጥረት ምክንያት በረራዎቻቸውን ቢቀንሱም፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግን ያለ ምንም እንከንና መስተጓጎል መደበኛ አገልግሎቱን እያስቀጠለ መሆኑን መናገራቸው ይታወሳል።
ይህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጥንካሬና አስተማማኝነት በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለውን ተወዳዳሪነት የሚያሳይ መሆኑንም ጠቁመዋል።
በለሚ ታደሰ
#ebc #middleeastconflict #heathrowairport #spiritairlines #ethiopianairlines #globaltravel

Comments