28 days ago
ከልማዳዊ አሠራር ወደ ተቋማዊነት እየተሸጋገረ ያለው የመረዳዳት ባህላችን
****************
በእኛ በኢትዮጵያውያን ማህበራዊ ሕይወት ውስጥ ሰብዓዊነትና መረዳዳት አዲስ ሀሳብ አይደለም።
በችግርናም ሆነ በደስታ ጊዜያት አብረን የመቆም፣ ደካሞችን የመደገፍና ያለንን የማጋራት ጥንታዊ ባህል አለን።
በ2018 ዓ.ም የተከናወኑ ሰው ተኮር የልማትና የበጎ አድራጎት ሥራዎች ይህን ባህላዊ ዕሴት ከዕለት ተለት መፍትሔነት አውጥተው ወደ ተቋማዊና ዘላቂ የልማት ባህል ያሸጋገሩ ሆነዋል።
በአሁኑ ወቅት በመላው ሀገራችን በስፋት እየተተገበረ ያለው ሰው ተኮር ልማት የዜጎችን የዕለት ተለት ሕይወት ጥራት የመቀየርና የማኅበረሰብ አብሮነትን የማጠናከር ትልቅ ዓላማ ያለው ነው።
በበዓላትና በክረምት ወራት የሚከናወኑ የማዕድ የማጋራት መርሐ ግብሮች ለበርካታ አረጋውያንና ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ዜጎች የማኅበራዊ ዋስትና መረቦች ሆነዋል።
በተመሳሳይ መልኩ በክረምት ወራት በሺዎች የሚቆጠሩ ያረጁ የአቅመ-ደካሞች መኖሪያ ቤቶች የዜጎችን ክብርን በሚያስጠብቅ ደረጃ በበጎ ፈቃደኞች በመታደስ ላይ ይገኛሉ።
የከተሞች ጽዳትና ውበት ሥራዎችም መሠረተ ልማትን ከማስፋፋት ባለፈ የዜጎችን ጤና በመጠበቅ፣ ሰብዓዊ ክብርን ማዕከል ያደረገ የከተማ ሕይወት እንዲፈጠር አድርገዋል።
የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ሕይወትን የማዳን ቅዱስ ተግባር ከሆነው የደም ልገሳ በተጨማሪ በርካታ ዜጎች ነፃ ሕክምና ያገኙበት ሀገራዊ ባህል እየሆነ መጥቷል።
እነዚህ በላቀ ደረጃ የተፈፀሙ ተግባራት ትልቁ ፋይዳቸው በዜጎች ቀጥተኛ ተሳትፎ የተከናወኑ መሆናቸው ነው።
ወጣቶች፣ ባለሀብቶች፣ የመንግሥት ሠራተኞችና የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጉልበታቸውን፣ ዕውቀታቸውንና ሀብታቸውን አስተባብረው በመሥራታቸው በዜጎች መካከል የጠበቀ የማኅበራዊ ትስስር ፈጥሯል።
አቅመ-ደካማ ጎረቤቱን የሚረዳ፣ ቤቱን የሚያድስለት ወይም ደሙን የሚለግሰው አንድ ወጣት፣ የሀገሩና የማኅበረሰቡ ዋና አካል እንደሆነ ይሰማዋል።
ይህ ደግሞ በዜጎች መካከል አለኝታነትንና የጋራ ኃላፊነት ስሜትን በመገንባት ለሀገራዊ ጽናት፣ ለሰላም እና ለዘላቂ ልማት የማይተካ ምሰሶ ይሆናል።
ሰብዓዊነትን የልማት ማዕከል ማድረግ ማለት ድህነትንና ማኅበራዊ ፈተናዎችን በጋራ አቅም የመቀነስ ስትራቴጂ ነው።
በዚህ ዓመት የተከናወኑ ሰው ተኮር የልማት ተግባራት እንደሚያሳዩት፣ የበጎ አድራጎትና የመረዳዳት ሥራ ከጊዜያዊ ድጋፍነት አልፎ ሀገራዊ የልማት ማዕቀፍና የመልካም አስተዳደር አካል በመሆኑ ለነገዋ ኢትዮጵያ ግንባታ ትልቅ መንገድ ከፍቷል።
በኢንቲሃድ አብራር
#ethiopia #communityservice #socialsafetynet #socialcohesion #ebc

Comments