5 months ago
ፌስቡክ የቲክቶክና የዩቲዩብ ተፅዕኖ ፈጣሪዎችን በዶላር እያማለለ ነው
* በወር እስከ 3,000 ዶላር ክፍያ
#ethiopia | ሜታ (ፌስቡክ) "Creator Fast Track" የተሰኘ አዲስ መርሃ-ግብር ይፋ በማድረግ፣ የታወቁ የቲክቶክ እና የዩቲዩብ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ወደ ፌስቡክ እንዲመጡ ከፍተኛ የገንዘብ ጥሪ አቀረበ።
ኩባንያው ፈጣሪዎች ቀደም ሲል በሌሎች መድረኮች የለቀቋቸውን ቪዲዮዎች በፌስቡክ ላይ መልሰው በመለጠፍ ብቻ፣ እንደ ተከታዮቻቸው ብዛት እስከ 3,000 ዶላር የሚደርስ ወርሃዊ ክፍያ እንደሚፈጽም አስታውቋል።
በሌሎች መድረኮች (ቲክቶክ ወይም ዩቲዩብ) ቢያንስ 20,000 ተከታዮች ሊኖራቸው ይገባል።
18 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆኑ ፈጣሪዎች።
በአሁኑ ወቅት በአሜሪካና በካናዳ ለሚኖሩ ፈጣሪዎች የተከፈተ ነው።
ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ በፌስቡክ ገጻቸው ላይ ምንም ዓይነት አጭር ቪዲዮ (Reels) ያልለቀቁ መሆን ይጠበቅባቸዋል።
ሜታ ይህንን እርምጃ የወሰደው የቪዲዮ ገበያውን ከተቀናቃኞቹ ለመንጠቅ ሲሆን፣ በ2025 ለፈጣሪዎች የከፈለውን የክፍያ መጠን በ35 በመቶ በመጨመር 3 ቢሊዮን ዶላር አድርሶታል።
በተለይም ቲክቶክ በአሜሪካ ውስጥ ካለበት የሕግ እገዳ ስጋት ጋር ተያይዞ፣ ፌስቡክ አጋጣሚውን በመጠቀም ተፅዕኖ ፈጣሪዎች የእርሱን መድረክ ዋነኛ አማራጭ እንዲያደርጉት ግፊት እያደረገ ይገኛል።
ከገንዘቡ በተጨማሪ ፌስቡክ ለሚለቀቁ ቪዲዮዎች ሰፊ ተደራሽነት (Reach) እንዲያገኙ ልዩ የቴክኒክ ድጋፍ እንደሚያደርግም ቃል ገብቷል።
#getu #meta #facebook #tiktok #youtube #contentcreator #digitalmarketing #socialmedianews #ፌስቡክ #ቴክኖሎጂ #ገቢ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

Comments