1 month ago
ከ35 ዓመት በኋላ አዲስ ብር! ሱማሌያ ከዶላር ጥገኝነት ልትፋታ ነው!
#ethiopia | ሱማሌ ከ35 ዓመታት በኋላ የራሷን የገንዘብ ኖት ልታትም ነው።
ሶማሊያ ከአሜሪካ ዶላር ወጥታ የራሷ የብር ኖት መጠቀም ሊትጀምር ነው።
የሱማሌ ማዕከላዊ ባንክ ከ35 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ አዲስ ብሔራዊ የገንዘብ ኖት ለማተምና ወደ ሥራ ለማስገባት የሚያስችለውን ዝግጅት እያጠናቀቀ መሆኑን አስታወቀ።
በፈረንጆቹ 1991 ላይ የማዕከላዊው መንግሥት መፍረስን ተከትሎ በሀገሪቱ የነበረው የማዕከላዊ ባንክ ቁጥጥር በመዳከሙ በገበያው ላይ የነበረው የሱማሌ ሺሊንግ ከ95 በመቶ በላይ ሀሰተኛ እና የተበላሸ እንደነበር ይታወቃል።
ማዕከላዊ ባንኩ ይህንን የገንዘብ ለውጥ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) እና ከዓለም ባንክ ጋር በመተባበር የሚያካሂደው ነው።
በአሁኑ ሰአት በሱማሌ አብዛኛው የንግድ እንቅስቃሴ በዶላር እና በሞባይል የገንዘብ ዝውውር ነው እየተካሔደ የሚገኘው።
አዲሱ ገንዘብ ወደ ሥራ ሲገባ አነስተኛ ገቢ ያላቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች ተጠቃሚ እንደሚያደርግና የሀገሪቱን የገንዘብ ፖሊሲ ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር ያስችላል ተብሎ ይጠበቃል።
ሐሰተኛ የገንዘብ ህትመቶችን ለመከላከል የሚያስችሉ ዘመናዊ የደህንነት ምልክቶች ያሏቸው አዳዲስ የሺሊንግ ኖቶች ወደ ገበያ የሚገቡ ይሆናል ተብሏል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #somalia #currency #imf #centralbank #americadollar #shilling

Comments