9 months ago
በቀጥታ ስርጭት (Live) ላይ አደገኛ ፈተና ሲሞክር የነበረው ወጣት ህይወቱ አለፈ
#ethiopia | በዲጂታል ዓለም ውስጥ ገንዘብ ለማግኘት ሲባል የሚደረጉ አደገኛ "ቻሌንጆች" (Challenges) ዋጋ እያስከፈሉ ነው።
"ሳንቾ" (Sancho) በሚል መጠሪያው የሚታወቀው የ37 ዓመቱ ስፔናዊ ስትሪመር ሰርጂዮ ጂሜኔዝ፤ በአዲስ ዓመት ዋዜማ በተከታዮቹ ለሚከፈለው ገንዘብ ብሎ ባደረገው አደገኛ ሙከራ በቀጥታ ስርጭት ላይ እያለ ህይወቱ አልፏል።
የነገሩ መነሻ ምንድን ነው?
ሰርጂዮ በ Kick የተሰኘው ፕላትፎርም ላይ በቀጥታ ስርጭት እያለ፤ ተመልካቾች ለሚልኩለት ገንዘብ (Donation) ምትክ ግማሽ ሊትር ውስኪ እና 6 ግራም ኮኬይን በአጭር ጊዜ ወስዶ ለመጨረስ ቃል ይገባል። ይህንኑ መርዛማ ውህድ እየወሰደ እያለ ነው ድንገት ህይወቱ ያለፈው።
ልብ የሚነካው አጋጣሚ
በጣም የሚያሳዝነው፤ ልጇ ካለበት ክፍል ድምፅ ሲጠፋ የተጨነቀችው እናቱ፤ በሩን ከፍታ ስትገባ ልጇ በስርጭት ላይ እያለ ተንበርክኮ ህይወቱ አልፎ አግኝታዋለች። በወቅቱ ኮምፒውተሩ እንደበራ ነበር፤ ተመልካቾችም በኮሜንት መስጫው ላይ "ተኝቶ ይሆን?" እያሉ ይጠይቁ ነበር።
የህግ ጉዳይ
የስፔን ፖሊስ ይህንን ጉዳይ በከፍተኛ ሁኔታ እየመረመረ ሲሆን፤ ወጣቱ ይህን አደገኛ ድርጊት እንዲፈጽም ገንዘብ የከፈሉ እና ያበረታቱ ተመልካቾች በህግ ሊጠየቁ እንደሚችሉ ፍንጭ ሰጥቷል።
ይህ በ2026 መባቻ ላይ የተሰማው አደጋ፤ በማህበራዊ ሚዲያ የሚደረጉ አደገኛ ፉክክሮች ምን ያህል አሳሳቢ እንደሆኑ ማሳያ ሆኗል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#socialmediadanger #kickstreamer #sancho #spain #awareness #livestreamtraged

Comments