4 months ago
ለጤናማ እናትነት ዘላቂ የፋይናንስ ምንጭ!
#ethiopia | በኢትዮጵያ ለ20ኛ ጊዜ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ39ኛ ጊዜ የሚከበረው የጤናማ እናትነት (Safe Motherhood) ወር “ለጤናማ እናትነት ፈጠራ የታከለበትና ዘላቂ የፋይናንስ ምንጭ” በሚል መሪ ቃል ተከብሯል።
በኢትዮጵያ የእናቶችን ሕይወት ለህልፈት እየዳረጉ ያሉ ዋና ዋና የጤና ችግሮች ከወሊድ በኋላ የሚከሰት የደም መፍሰስ፣ ከእርግዝና ጋር የተያያዘ የደም ግፊት፣ ኢንፌክሽን፣ የምጥ መገታት እና ካልተገባ ውርጃ ጋር የተያያዙ ውስብስብ ችግሮች መሆናቸውን መረጃዎች ያሳያሉ። እነዚህን ችግሮች ለመቅረፍም “ሦስቱ መዘግየቶች” በመባል የሚታወቁትን ማለትም፦
የሕክምና እርዳታ ለማግኘት የመወሰን፣
የጤና ተቋም የመድረስ፣
ተቋም ከደረሱ በኋላ ፈጣንና ጥራት ያለው ሕክምና የማግኘት ክፍተቶችን ማጥበብ እንደሚገባ ተመላክቷል።
የቅድመና ድህረ ወሊድ ክትትል አስፈላጊነት
አንዲት እናት በእርግዝና ወቅት ቢያንስ ከ4 እስከ 8 ጊዜ የቅድመ ወሊድ (ANC) ክትትል በማድረግ ለደም ማነስ፣ ለደም ግፊትና ለተላላፊ በሽታዎች ምርመራ ማድረግ እንዳለባት ተገልጿል።
በተለይም ከወሊድ በኋላ ያሉት የመጀመሪያዎቹ 48 ሰዓታት ለእናቶች ሕይወት እጅግ ወሳኝ በመሆናቸው፣ ደም መፍሰስንና ኢንፌክሽንን ቀድሞ ለመከላከል ጥብቅ ክትትል ሊደረግላቸው ይገባል።
በኢትዮጵያ ተግባራዊ እየሆነ ያለው የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም የማህበረሰቡን ግንዛቤ በማሳደግና እናቶች አገልግሎቱን በቅርበት እንዲያገኙ በማድረግ ረገድ ትልቅ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።
ፕሮግራሙ በተለይ በጤና ትምህርት፣ በክትትልና በሪፈራል ስራዎች ላይ ትኩረት በማድረግ የእናቶችን ሞት ለመቀነስ እየሰራ መሆኑ ዶክተር ሠራም ተካ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ የማህጸን እና ጽንስ ስፔሻሊስት ዶክተር ጠቅሰዋል።
#safemotherhood #ethiopiahealth #maternalhealth #healthymotherhood #endmaternalmortality #postnatalcare #healthextension

Comments