1 day ago
ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በድጋሜ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተመረጡ
#ethiopia | ዶክተር ዐቢይ አህመድ ሀገሪቱን ለቀጣዮቹ አምስት ዓመታት በጠቅላይ ሚኒስትርነት ለመምራት ከአዲሱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሙሉ ድጋፍ አግኝተዋል።
ዛሬ ሰኞ፣ መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም. በተካሄደው የፓርላማ መደበኛ ስብሰባ የዶክተር ዐቢይ አህመድ የጠቅላይ ሚኒስትርነት ሹመት በምክር ቤቱ አባላት በደመቀ ጭብጨባ የጸደቀ ሲሆን፣ እርሳቸውም በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው የመሐላ ሥነ-ሥርዓት ፈጽመዋል።
ገዢው ብልጽግና ፓርቲ በቅርቡ በተካሄደው ሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ 438 የፓርላማ መንበሮችን በማሸነፍ የበላይነቱን ያረጋገጠ ሲሆን፣ አብላጫ ድምፅ ያለው በመሆኑም ዶክተር ዐቢይን ለጠቅላይ ሚኒስትርነት ዕጩ አድርጎ አቅርቧል።
ዶክተር ዐቢይ አህመድ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ሥልጣን የመጡት በመጋቢት 2010 ዓ.ም. አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝን በመተካት የነበረ ሲሆን፣ በ2014 ዓ.ም. ከተካሄደው ስድስተኛው ጠቅላላ ምርጫ በኋላም በድጋሚ የመንግሥት መሪ ሆነው መመረጣቸው ይታወሳል።
የዘንድሮው የመንግሥት ምሥረታ ሥነ-ሥርዓት ከአምስት ዓመታት በፊት በመስቀል አደባባይ በርካታ የውጭ ሀገራት መሪዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ከተካሄደው ደማቅ ሥነ-ሥርዓት የተለየ ሆኖ አልፏል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዚህ ቀደም በሰጡት አስተያየት አዲሱ መንግሥት ከተመሠረተ በኋላ ጊዜ ሳያባክኑ በቀጥታ ወደ ሥራ መግባት እንደሚገባ በመግለጽ፣ በዚህ ወቅት ተመሳሳይ ትልቅ ሥነ-ሥርዓት እንደማይዘጋጅ ማሳወቃቸው ይታወሳል።
በዚህም መሠረት ዶክተር ዐቢይ አህመድ በሀገሪቱ ታሪክ ለሦስተኛ ጊዜ የጠቅላይ ሚኒስትርነት ሥልጣንን ተረክበው አዲሱን የመንግሥት የሥራ ዘመን ጀምረዋል።
#pmabiy #abiyahmed #parliament #ethiopianpolitics #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa #ethiopia #abiyahmed #primeminister #getutemesgen

1 month ago
"ሠራተኞችን አታጉላሉ ከቤታቸው ሆነው ይስሩ!"
#ethiopia | የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ከቤት ሆኖ መስራትን እንደሚደግፉ ገለጹ።
የጃፓኗ ጠቅላይ ሚኒስትር ሳናኤ ታካኢቺ ሰራተኞች እና አመራሮች ከቤት ሆኖ መስራትን እንዲያበረታቱና ራሳቸውም የዚህ አሰራር ደጋፊ መሆናቸውን አስታውቀዋል።
ከቤት ሆኖ መስራት ሰራተኞች ለጉዞ የሚያጠፉትን ጊዜ በመቀነስ የስራ ምርታማነትን እንደሚያሳድግ እና የቤተሰብ ጊዜን እንደሚያስፋፋ ገልጸዋል።
መንግስታቸው የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በማሳደግ የመንግስት እና የሀገሪቱን የቢሮ አሰራሮች በዲጂታል መንገድ እንዲቃኙ ለማድረግ ያለመ መሆኑን አብራርተዋል።
አሰራሩ በተለይም ልጅ አሳዳጊ ወላጆች እና እንክብካቤ የሚሹ ቤተሰብ ያላቸው ሰራተኞች ከስራ ገበታቸው ሳይገለሉ ውጤታማ እንዲሆኑ ትልቅ እድል እንደሚፈጥር ጠቁመዋል።
አዲሱ የጠቅላይ ሚኒስትሯ የስራ ዕቅድ በጃፓን የቢሮ አሰራር ላይ አዲስ ምዕራፍ ሊከፍት እንደሚችል እየተነገረ ይገኛል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #japan #primeminister #works #homes #teleworking #workers

Comments