2 months ago
በፊላዴልፊያ የምድር ውስጥ ባቡር ጣቢያ ሰዎችን ሲያስደነግጥ የነበረው ጭንብል ለባሹ
#ethiopia | በአሜሪካ ፔንስልቬንያ ግዛት ፊላዴልፊያ ከተማ ባቡር ጣቢያዎችና መንገዶች ላይ አስፈሪ የህፃን አሻንጉሊት (Chucky-style) የፊት ጭንብል በማድረግ መንገደኞችን ሲያስደነግጥ፣ ሲያሳድድ እና ስጋት ሲፈጥር የነበረ ግለሰብ ያልተጠበቀ የመልስ ምት ገጥሞታል።
በኒውዮርክ ታይምስ እና በበርካታ የዓለም አቀፍ ዜና አውታሮች ሽፋን በተሰጠው በዚህ ክስተት፣ ተጠርጣሪው በከተማዋ ለጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ በርካታ ሰዎችን ለማስፈራራት ቢሞክርም፣ በመጨረሻ ግን ያልተጠበቀ ድፍረት ካሳየች ሴት ጋር ተፋጧል።
ተጠርጣሪው የሞባይል ስልኩን መብራት በማብራት ድርጊቱን በቪዲዮ እየቀረጸ ሰዎችን ሲያሳድድ እና "ልትሞች ዝግጁ ነሽ?" የሚሉ የማስፈራሪያ ቃላትን ሲናገር እንደነበር የፊላዴልፊያ ፖሊስ ገልጿል።
ጃሜካ ቪልሰን (Jameka Wilson) የተባለችው ሴት ግለሰቡ ሊያሳድዳት ሲሞክር ከመሸሽ ይልቅ ፊቷን ወደ እሱ በመመለስ "እሺ፣ እንጋጠም!" በማለት የውጊያ ዝግጅት አድርጋለች።
በመቀጠልም ደረቱ ላይ በርግጫ በመምታቷ ተጠርጣሪው ተሰናክሎ ወደ ኋላ በማፈግፈግ ከአካባቢው ለማምለጥ ተገዷል።
የፊላዴልፊያ ፖሊስ መምሪያ (Philadelphia Police Department) ክስተቱን በCCTV ካሜራዎች በመከታተል ተጠርጣሪውን ዚማየር ሂውስ (Zymire Hughes) በማለት የለየው ሲሆን፣ በህዝብ ደህንነት ላይ ስጋት በመፍጠር፣ ህገ-ወጥ ማስፈራራት እና ጥቃት በመሰንዘር ወንጀሎች ህጋዊ እርምጃ እየወሰደበት ይገኛል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getutemesgenmedia #philadelphia #phillynews #usnews #breakingnews #subwayincidents #selfdefense #crimenews #philadelphiapolice #nytimes #worldnews #trendingnews

በውቅያኖስ ማዶ የፈነጠቀው የኢትዮጵያ ኩራት! #ethiopiancuisine #sekelakitchen #philadelphia #readingterminalmarket #inspiration
1 year ago
ጤናማ እምቢታ!
#ethiopia | አንዱ ምርጫህ ሰዎችና ሁኔታዎች “እንዲህ ነህ” ብለው የሰጡህን ስምና ማንነት ተቀብለህ አቀርቅሮ መኖር ነው፡፡ ሌላኛው ምርጫህ ግን ያልሆንከውን ማንነትና የማይመጥንህ ስምና ሕይወት ላለመቀበል የሚያስፈልገውን መስዋእትነት መክፈል ነው፡፡ በሕይወትህ እሺ የምትላቸው መልካም ሰዎችና መልካም ነገሮች እንዳሉህ ሁሉ እምቢ ልትላቸው የሚገባህ ሰዎችና ጤና-ቢስ ሁኔታዎች ሊኖሩ የግድ ነው!
ሄንሪ (Henry Brown) በሰዎችም ሆነ በታሪክ የሚታወቀው “ቦክስ” ከሚል ቅጽል ስም ጋር ነው (Henry “Box” Brown)፡፡ በሰሜን አሜሪካ በቪርጂንያ ግዛት ውስጥ በ1815 ዓ/ም በባርነት ነው የተወለደው፡፡ በ15 ዓመቱ በትንባሆ እርሻ የጉልበት ስራ እንዲሰራ፡፡ እድሜው ደርሶ የሚወዳትን ሴት ቢያገባም፣ የባርነት ዘመን አሰራር ናንሲ (Nancy) ከምትባለዋ የትዳሩ ጓደኛው ለይቶት ነበር፡፡ ናንሲ ባሪያዎችን በመሸጥና በመግዛት ስራ የተሰማራ የአንድ ጌታ ንብረት ሆና በአቅራቢያው በሚገኝ እርሻ ጉልበት ስራ ትሰራለች፡፡ አራተኛ ልጇን ለመውለድ ደርሳ ነበር፡፡
አንድ ቀን ሄንሪ አንድ አሳዛኝ ዜና ደረሰው፡፡ ዓመተ ምህረቱ 1848 ነው፡፡ ናንሲና ልጆቿ ወደ ሌላ ግዛት በሽያጭ ሊጋዙ ነው፡፡ በመንገድ ላይ ቆሞ እንባ ከአይኖቹ እየፈሰሱ 350 ሃምሳ የሚሆኑ ባሪዎች በሰንሰለት ታስረው ሲወሰዱ ተመለከተ፡፡ በዚያ መካከል ነፍሰ-ጡር የሆነችው ሚስቱና ልጆቹ ይገኙበታል፡፡ ሁኔታውን ለመለወጥ ምንም አቅም አልነበረውም፡፡
በተከሰተው ሁኔታ እጅግ ያዘነው ሄንሪ ከባርነት ለማምለጥ ቁርጥ ውሳኔ አደረገ፡፡ ፊላደልፊያ በተሰኘች ከተማ ውስጥ የጥቁር ባርነትን ስርዓት የሚቃወም አንድ ነጭ እንደነበረ ስለሰማ ወደ እርሱ ለመድረስ ወሰነ፡፡ ከአንድ ጄምስ (James) ከሚባል በጊዜው ከባርነት ነጻ ከሆነ ወዳጁ ጋር በመማከር ራሱን በሳጥን ውስጥ ከደበቀ በኋላ ይህ ጓደኛው አድራሻ በሳጥኑ ላይ በመጻፍና ወደ ፖስታ ቤት በመውሰድ በፖስታ እንዲልከው ተማከረ፡፡
ሄንሪ የተደበቀበትን ሳጥን ወደ ነጻ አውጪው ሳሙኤል (Samuel Alexander Smith) ወደተሰኘው ነጭ እንዲልከው ከጓደኛው ከጄምስ ጋር ተማክሯል፡፡ እቅዱ ጥሩ የፈጠራ ብቃትን የሚያሳይ ቢሆንም፣ እጅግ አደገኛ ውሳኔ ነበር፡፡ በእቅዳቸውም መሰረት ማርች 23፣ 1849 ዓ/ም ሄንሪ ራሱን የደበቀበትን ሳጥን ጓደኛው ጄምስ በፖስታ ቤት ላከው፡፡
ሄንሪ አየር እንዲያገኝ ያህል ሳጥኑ ላይ ትንሽ ቀዳዳ ፈጥረዋል፡፡ ከውኃና ከጥቂት ብስኩት በስተቀር የያዘው ነገር የለም፡፡ ጉዞው በጋሪ፣ በባቡርና በጀልባ ነበር፡፡ በመጨረሻም በፊላደልፊያ (Philadelphia) በሚገኘው የጸረ-ባርነት ማሕበር አድራሻ ሳጥኑ ደረሰ፡፡ በዚህ 27 ሰዓታት በፈጀ ጉዞ ሄንሪ የተደበቀበት ሳጥን በብዙ ውጣ ውረድ ውስጥ አልፏል፡፡
ያለፈበትን ሁኔታ ሄንሪ ሲገልጽ፣ “አይኖቼ አብጠው ሊፈነዱ ጥቂት ቀርቷቸው ነበር፡፡ በጭንቅላቴ ላይ ከነበረው ውጥረት የተነሳ የደም ስሮቼ ተወጥረው ነበር፡፡” በአንድ ወቅት ሳጥኑ ተዘቅዝቆ በነበረበት ጊዜ ሄንሪ ከነበረበት ሁኔታ የተነሳ የሚሞትም መስሎት ነበር፡፡ ሁለት ሰዎች የሚቀመጡበት ስፍራ ሲፈልጉ በሳጥኑ ላይ ለመቀመጥ ሲሉ ገለበጡትና ለሄንሪ ጥሩ ገጠመኝ ሆነለት፡፡
በመጨረሻም ሄንሪ ተደብቆበት የነበረው ሳጥን ዊልያም፣ ጃምስ፣ ፕሮፌሰር ሲዲ እና ልዊስ ወደተሰኙ ሰዎች እጅ ገባ፡፡ ሳጥኑም ሲከፈት ሄንሪ፣ “እንደምን አላችሁ፣ ክቡራን?” በማለት ከሳጥኑ ውስጥ ብቅ አለ፡፡ በዚህም ውሳኔው በፍጹም ሊቀበለው ከማይችለው የባርነት ሕይወት ወደ ነጻነት ተሸጋገረ፡፡
አንድ ሰው መሆንና ማድረግ ከሚፈልገው መልካም ነገር የሚገታውን ነገር ለማሸነፍ እስካልተነሳ ድረስ ሙሉ ሰው መሆን ያስቸግረዋል፡፡ እንዲህ አይነቱ ሁኔታ ደግሞ ከራሱ አልፎ ለትውልድ የሚተርፍ መዘዝ አለው፡፡ ሰው ጤና ቢስ ለሆነው ነገር “እምቢ” ማለት ሲጀምር ለብዙዎች ከእርሱ በኋላ ለሚመጡ ሰዎችም ሳይቀር የነጻነትን ፈር ይቀዳል፡፡
የሰው ዘር ከፈጣሪው ከተቀበላቸው ስጦታዎች አንዱ የምርጫ ስጦታ ነው፡፡ ለማንነቱ የማይመጥነውን ነገር ለይቶ በማወቅ በምርጫ ሲኖር ያንን ነጻነቱን መለማመድ ይጀምራል፡፡ ሆኖም፣ “እምቢ” ማለት የሚገባንን ማወቅ ቀላል፣ ያንን ማድረግ ግን ከባድ ነው፡፡
መመለስ ያለባቸው ጥያቄዎች . . .
• ከማንነቴ በታች ለመኖር ራሴን የሰጠሁበት ሁኔታና ልማድ ምንድን ነው?
• ከማንነቴ በታች እንድኖር እያስገደደኝ ያለ ሰው ማን ነው?
• ከማንነቴ በታች እንድኖር የሚጎትተኝ ያለፈ ታሪኬ ምንድ ነው?
• ከማንነቴ በታች እንድኖር የሚጎትተኝ ፍርሃት ምንድ ነው?
• አንድን ነገር ከፍላጎቴ ውጪ እንዳደርግ እያስገደደኝ ያለ ሰው ማን ነው?
Dr eyob mamo

Sponsored by
Surafel
Comments