11 hours ago
ናሽናል አቪዬሽን ኮሌጅ ከ1ሺህ በላይ ተማሪዎችን አስመረቀ
#ethiopia | ናሽናል አቪዬሽን ኮሌጅ በ13ኛ ዙር 1,102 ተማሪዎችን በዛሬው እለት አስመረቀ። ከተመራቂዎቹ መካከል ከ400 በላይ የሚሆኑት በአቪዬሽን ዘርፍ የሰለጠኑ ባለሙያዎች መሆናቸው ተገልጿል።
ኮሌጁ በአውሮፕላን ጥገና፣ በበረራ ኦፕሬሽን፣ በበረራ አስተናጋጅነትና በሌሎች የአቪዬሽን ሙያዎች ሥልጠና ለመስጠት ከኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ፈቃድ ማግኘቱን ገልጿል። ከዓለም አቀፉ የአየር ትራንስፖርት ማኅበር እና ከእንግሊዙ የኮሜርሻል ማኔጅመንት ተቋም እውቅናዎችን ማግኘቱም ተመልክቷል።
የናሽናል ኢንቨስትመንት ግሩፕ አባልና የናሽናል ኤርዌይስ እህት ኩባንያ የሆነው ተቋሙ፣ ከኮሌጅ ወደ ኤሮስፔስ ዩኒቨርሲቲነት ለመሸጋገር የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን ማጠናቀቁንም አስታውቋል።
ሽግግሩ የተቋሙን የትምህርትና የሥልጠና አቅም ከማሳደግ ባለፈ፣ በኢትዮጵያና በአፍሪካ የአቪዬሽንና የኤሮስፔስ ዘርፎች ብቁ የሰው ኃይል ለማፍራት፣ ምርምርን ለማስፋፋትና የፈጠራ ሥራዎችን ለማበረታታት ያለመ መሆኑ ተገልጿል።
#nationalaviationcollege #aviation #aerospaceuniversity #ethiopia #aviationtraining #graduationceremony #aerospace #aviationindustry #highereducation

Comments