3 months ago
ልዕለ አጀንዳችን፡ ምክክር!
******************
በዚህ ታሪካዊ የለውጥ ምዕራፍ፣ ከምንም በላይ ገዝፎ የሚወጣው እና ሀገራችንን ከገባችበት ውስብስብ ማነቆ የሚያወጣት ትልቁ እና ብቸኛው ሀገራዊ ጉዳይ ቢኖር "ሀገራዊ ምክክር" ነው! ኢትዮጵያችን ይህን የብርሃን ዘመን ለማየት፣ የጥይት ድምፅ በሀሳብ ልዕልና የሚሸነፍበትን ዕለት ለመመስከር፣ እንዲሁም ልዩነቶቿን በሰለጠነ የጠረጴዛ ዙሪያ ውይይት ለመፍታት በትዕግስት እና በናፍቆት ረጅም ጊዜ ጠብቃለች። ይህን የተቀደሰ እና የሰለጠነ የምክክር መድረክ እውን ለማድረግ፣ ሀገርን ሊገነቡ የሚችሉ አያሌ ትውልዶች በከንቱ ባክነዋል፤ ኢትዮጵያም በእርስ በርስ ፍጅት እና በጦርነት አዙሪት ውስጥ ገብታ በዋጋ የማይተመን እጅግ ከባድ መስዋዕትነትን ከፍላለች።
እንሆ፣ ያ ያለፈው ትውልድ በፅኑ የተመኘው፣ ውድ ህይወቱን የገበረለት፣ ነገር ግን በህይወት ዘመኑ ሊያየው ያልታደለው ታላቅ የምክክር ዕድል ዛሬ በዘመናችን እውን ሆኗል። ይህ በአጋጣሚ የተገኘ ተራ የፖለቲካ ኩነት ወይም የዕለት ተለት ክስተት ሳይሆን፣ በታሪክ አጋጣሚ በቀላሉ ሊገኝ የማይችል፣ የኢትዮጵያን የነገ ዕጣ ፈንታ በፅኑ መሠረት ላይ የሚያቆም ወርቃማ ዕድል ነው። ዛሬ ላይ የገዛ የፖለቲካ ቁስላችንን በገዛ እጃችን አክመን፣ የቆዩ ልዩነቶቻችንን በሰለጠነ መንገድ አቻችለን፣ ብዝኃነትን የሚያከብር አዲስና ጠንካራ ማህበራዊ ውል የምናስርበት ይህ ሀገራዊ ምክክር፣ ከምንም ነገር በላይ ቅድሚያ የምንሰጠው "ልዕለ አጀንዳችን" ነው!
በዚህ ወሳኝ እና ታሪካዊ ወቅት፣ ሀገራችንን ከማፅናት፣ ከመምከር እና ከመደማመጥ በላይ ሌላ ትልቅ አጀንዳ ፈፅሞ የለም። እናም፣ ይህ ታሪካዊ ልዕለ አጀንዳችን ከግብ ደርሶ ኢትዮጵያን ወደ ብሩህ ተስፋ እንዲያሻግር፣ የጥቂት የፖለቲካ ልሂቃንን ሩጫ ብቻ ሳይሆን፣ የመላው ኢትዮጵያውያንን የነቃ፣ የተባበረ እና ያልተቋረጠ ርብርብ ይጠይቃል። ሁላችንም ይህን ወደር የለሽ ዕድል ተጠቅመን፣ ተመካክረን፣ ተደማምጠን እና ተባብረን ሀገራችንን ወደ አዲስ የሰላም እና የብልጽግና ከፍታ ማሸጋገር ትልቁ ታሪካዊ ግዴታችን ነው!
በአዶኒያስ ወልደአረጋይ
#ethiopia #natinaldialogue #nationalconsensus #socialcontract #ebc

Comments