7 days ago
በዳውሮ ዞን የተገነቡ ሞዴል የገጠር መንደሮች ተመረቁ
******************
መንደሮቹን መርቀው ለተጠቃማዎች ያስተላለፉት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ሞዴል የገጠር መንደሮች የግብርና እና የገጠር ሽግግርን ከማፋጠን ጎን ለጎን የአርሶ አደሩን የኑሮ ዘይቤ የሚያስዘመኑ ናቸው ብለዋል።
አርሶ አደሮች ማኅበራዊ ሕይወታቸውን የበለጠ እንዲያጠናክሩ ዕድል ከመፍጠሩም በላይ መሠረታዊ አገልግሎቶችን በአቅራቢያቸው እንዳያገኙም አስችሏቸዋል።
በክልሉ ውጤታማነቱ እያደገ ለመጣው የሌማት ትርፋት መርሐ ግብር የመንደሮቹ ግንባታ ዓይነተኛ አስተዋጽኦን እያበረከተ እንደሚገኝ እና ለምግብ ዋስትና መረጋገጥም ድርሻው የላቀ መሆኑን አስገንዝበዋል።
የመንደሮቹ ግንባታ የአርሶ አደሩን ሕይወት በመቀየር የክትመት ጽንሰ ሐሳብ መሠረት እንዲይዝ ማስቻሉንም ርዕሰ መስተዳድሩ አመላክተዋል።
የዳውሮ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳዊት ገበየሁ በበኩላቸው፣ የመደመር መንግሥት የዜጎችን ሕይወት በተጨባጭ የሚቀይሩ ፕሮጀክቶችን ነድፎ ውጤታማ ሥራዎችን እየሠራ ይገኛል ብለዋል።
በዞኑ የተገነቡ ሞዴል የጠር መንደሮች ለዚሁ ውጤት አብነት ይሆናሉ ያሉት ዋና አስተዳዳሪው፣ በሂደቱም የተፈጠረው የሥራ ዕድል በርካታ የወጣቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑ አስችሏል ብለዋል።
አርሶ አደሩ የኢኮኖሚ አቅሙን በዘላቂነት እንዲያጎለብት እና የምግብ ዋስትናውን እንዲያረጋግጥ የተጀመሩ ጥረቶችን የበለጠ ለማጠናከር የዞኑ አስተዳደር ጥረቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አብራርተዋል።
የሞዴል ገጠር መንደሮች ግንባታ በክልሉ ሁሉም ወረዳዎች እየተከናወነ የሚገኝ ሲሆን በ16 ወረዳዎች በተሟላ ሁኔታ መፈጸሙ ተመላክቷል።
በምረቃው ሥነ ሥርዓት ርዕሰ መሰተዳድሩን ጨምሮ የክልሉ መንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ ፍቅሬ አማን እና ሌሎችም ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ታድመዋል።
በሰለሞን ባረና
#ትልቅ_ሀገር #ትልቅ_ሕዝብ #ታላቅ_ርዕይ
#ethiopia #ebc #southwestethiopia #ruraldevelopment #modeldistricts

Comments