2 days ago
አሜሪካ አውስትራሊያን 2-0 በማሸነፍ ታሪካዊ ድል አስመዘገበች
#ethiopia | አሜሪካ አውስትራሊያን 2-0 በማሸነፍ ከ96 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በተከታታይ የዓለም ዋንጫ ጨዋታዎችን ማሸነፍ የቻለችበትን ታሪካዊ ድል አስመዝግባለች። በዋና ዳኛው Felix Zwayer የተመራው ጨዋታ ከመጀመሪያው ደቂቃ ጀምሮ በአሜሪካ የበላይነት ተካሂዷል።
ፈጣን ግቦች ውጤቱን ወሰኑ
አሜሪካ በ11ኛው ደቂቃ መሪነቱን ያዘች። Folarin Balogun በጀመረው ጥቃት የአውስትራሊያው ተከላካይ Cameron Burgess በራሱ መረብ ላይ ኳሱን በማስገባት አሜሪካን 1-0 አስቀደመ።
ከእረፍት በፊት በ43ኛው ደቂቃ ደግሞ Sergiño Dest ከርቀት የላከውን ኳስ ወጣቱ ተጫዋች Alex Freeman በግንባሩ በማስቆጠር ውጤቱን 2-0 አደረገው። ግቧ በመጀመሪያ ከጨዋታ ውጭ ተብላ ብትሻርም በVAR ምርመራ ተፈቅዳለች።
አሜሪካ በስታቲስቲክስም የበላይ ነበረች
በመጀመሪያው አጋማሽ አሜሪካ 70 በመቶ የኳስ ቁጥጥር አስመዝግባ 88 በመቶ የፓስ ስኬት አሳይታለች። ቡድኑ 259 ፓሶችን ሲያቀብል አውስትራሊያ 78 ብቻ ማድረስ ችላለች፤ ይህም በሜዳው ላይ የአሜሪካን ሙሉ ብልጫ አሳይቷል።
የአሰልጣኞች ታክቲካዊ ቅያሬ
የአውስትራሊያ ቡድን በሁለተኛው አጋማሽ ጫናውን ለመጨመር በርጌስ፣ ቱሬ እና ቬሉፒላይን አውጥቶ ጌሪያ፣ ኢራንኩንዳን እና ሜትካፌን አስገብቷል።
በሌላ በኩል የአሜሪካው አሰልጣኝ Mauricio Pochettino ውጤቱን ለማስጠበቅ የመከላከል ቅያሬዎችን በማድረግ ቡድኑን አጠናክሯል።
የመጨረሻ ደቂቃዎች ውጥረት
አውስትራሊያ በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች ልዩነቱን ለመቀነስ በርካታ ሙከራዎችን ብታደርግም አልተሳካላትም። Matthew Leckie ከርቀት የሞከረው ኳስ ለጥቂት ሲወጣ፣ Harry Souttar በ85ኛው ደቂቃ ያገኘው የወርቅ ዕድል ሳይሳካ ቀርቷል።
በ88ኛው ደቂቃ በባሎገን እና ሱታር መካከል የተፈጠረ ግጭት ወደ ቢጫ ካርድ አምርቶ ሁለቱም ተጫዋቾች ማስጠንቀቂያ ተመልክተዋል።
የጨዋታው አስደናቂ ክስተት
በጨዋታው ወቅት ዋናው ዳኛ ፊሊክስ ዝዋየር በጡንቻ መኮማተር ምክንያት በሜዳ ላይ ህክምና ተደርጎላቸው ጨዋታውን ቀጥለው መምራታቸው ከተለዩ ክስተቶች አንዱ ሆኖ ተመዝግቧል።
በአጠቃላይ አሜሪካ በጨዋታው ሙሉ 90 ደቂቃዎች የተሻለ አቋም በማሳየት ተገቢውን ድል ስታሳካ፣ ፎላሪን ባሎገን ደግሞ በቡድኑ ታሪካዊ ውጤት ውስጥ ወሳኝ ሚና በመጫወት ተጫራች ኮከብ ሆኖ ተወድሷል።

4 months ago
'ሌላ እውነት የለኝም' በቨርጂኒያ ተመረቀ
#ethiopia | የአርቲስት ሜሮን ጌትነት ‘ሌላ እውነት የለኝም’ የግጥም መድበል እጅግ ባማረና የሚገባውን ክብር ባገኘ መልኩ እዚህ ቨርጂኒያ ውስጥ ተመርቋል። ግጥሞቿ በሞያ አጋሮቿ ተነበዋል፣ ሙያዊ ዳሰሳም ተደርጎባቸዋል። የሜሪ ግጥሞች በስሜት ማዕበል ሲያወዛውዙን፣ ሲያስደምሙን፣ ሲያስለቅሱን፣ ሲያስቁን፣ ሲመስጡን አመሹ። ነገሮችን የምታይበት መነጽር አዲስ፣ የምትገልጽበት መንገድ ደግሞ የነፍሳችንን አስኳል የሚነካ ሃይል ያለው አለው።
ላይ ላዩን የሚጋልቡ ሳይሆን ሁለንተንችንን የሚነዝሩ፣ ውስጥ ድረስ ዘልቀው የሚሰሙና ጥያቄ የሚያጭሩ ሃሳቦች ግዘፍ ነስተው፣ ነፍስ ዘርተው ግጥሞቿ ውስጥ ይተነፍሳሉ፤ ይናገራሉ። ጥልቅ፣ መሰረታዊ፣ እናም ደግሞ ልዩ ትርጉም ያላቸው ሃሳብ፣ ምልከታና ሙግቶች ‘ሌላ እውነት የለኝም’ ውስጥ ሞልተዋል። ያልታዩ፣ ያልተስተዋሉና ያልታሰቡ የህይወት አቅጣጫወች በሜሪ ግጥሞች ውስጥ ፍንትው ብለው ተገለጠዋል። እናም ሁላችንም ወደ ውስጥ እንድናይ፣ ከራሳችን ጋ እንወዛገብ ዘንድ በር ይከፍታሉ። ይህን ሁሉ የሚያደርጉት ደግሞ በማያልቀው የሜሪ የቋንቋ ውበት፣ የአጻጻፍ ብቃት እና የፈጠራ ክህሎት ታጅበው፣ ጉዞው በማያልቅበት የምናቧ ጥልቀትና ስፋት ተቃኝተው ነው።
ሜሮን እንደ ሁልጊዜው ሁለገብ ከያኒነቷን ግጥሞቿን እየተወነች አሳየችን።ግጥም መጻፍ ብቻ ሳይሆን ማንበብም ጥርት ያለ ጥበብ መሆኑን አስመሰከረች። ግጥምና ጃዝ ዳግም ተጣመሩ። መድረኩ በትወና፣ በሙዚቃ እና በግጥም ደምቆ አመሸ። ግጥሞቿን አምጣ ወልዳ፣ አሳድጋ፣ አሳትማ፣ አስመርቃ ለወግ ለማዕረግ አበቃች። በምሽቱ ስራውቿን በማቅረብ፣ የራሳቸውን የኪነጥበብ ውጤቶችን በማቋደስ፣ የመጽሐፉን ዳሰሳ በማድረግ ለዝግጅቱ ግብዓት የሆኑት የሞያ አጋሮቿ የድግሱ ድምቀቶች ነበሩ። ለታይታና ደረስ ብሎ ለመመልስ ሳይሆን፣ ሙሉ ዝግጅቱን በሙሉ ልብ ለመቋደስ የታደመው የDMV ነዋሪም ለሜሪና ለስራወቿ አፍቃሪና አክባሪ መሆኑን በተግባር አሳይቶ ምሽቱን ምሉዕ አድርጎታል። ለዝግጅቱ መሳካት ሽር ጉድ ሲሉ የነበሩ አስተባባሪወችና ሁል ጊዜም እንዲህ ያሉ ዝግጅቶችን በመደገፍ የሚታወቁ አጋር ድርጅቶች ከሜሮን ጎን በመቆም የማህበራዊ ሃላፊነታቸውን ተወጥተዋል።
የሜሮን ስብዕና፣ ብቃት፣ ለሞያው ያላት መሰጠት እጅግ ይገርማል፣ ያስደምማል፣ ያስደስታል፣ ያኮራል። ሜሪ ሁሌ ጻፊ። እንኳን ደስ አለሽ።
Via Abebe Feleke
Photo Credit: Eagle Photography Nathnael Damtew
Meron Ghetnet Hiwot Tadesse followers #addisababa #ethiopia #dmv

🇺🇸 "ሌላ እውነት የለኝም" መጽሐፍ ይመረቃል
የመጽሐፍ ምርቃት
ክቡራትና ክቡራን፣ የጥበብ ወዳጆች
ሌላ ዕውነት የለኝም By Meron Getnet
ተወዳጇ ሜሮን ጌትነት በልዩ ስሜትና ጥልቀት የከተበችው “ሌላ እውነት የለኝም” የተሰኘው አዲስ መጽሐፏ ሊመረቅ ነው። የሜሮንን የቃላት ስዕልና ግልጽ “እውነት” ለመጋራት ይህን ልዩ ቀን ይጠብቁ።
ቦታ፦ Waterford Event Center
ሰዓት፦ ከሰዓት 3:00 PM ጀምሮ
የጥበብን ብርሃን አብረን እንኩል።
በቦታው ተገኝታችሁ ለደራሲውና ለሥራው ያላችሁን አክብሮት እንድትገልጹ በአክብሮት ተጋብዛችኋል።
SAVE THE DATE
Date : Sunday, February 22, 2026
3:00 PM
Address: Waterford Event Center
6715 Commerce St, Springfield, VA 22150
#meron Ghetnet
https://addisbooks.com/eve...

10 months ago
በአዲስ ሥራ እየመጣች ነው
#ethiopia | ገጣሚና ተዋናይት ሜሮን ጌትነት አዲስ ስራ ይዛ ልትመጣ እንደሆነ ባሳለፍነው ሳምንት በማህበራዊ ሚዲያ ገልፃለች። የራሷን ትክክለኛውን የፌስቡክ ገፅ አስፍራም ወዳጆቿ እንዲከተሏትና እንዲያጋሩላት ጠይቃለች። ስራዎቿን የምትወዱ እነሆ ትከተሏት ዘንድ።
https://www.facebook.com/m...

Sponsored by
Surafel
Comments