3 months ago
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት በሪፎርሙ ምክንያት ዳግም ተወልዷል ማለት ይቻላል፡- አቶ ሰይፈ ደርቤ
************
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት "የሚዲያ እመርታ ለትርክት ግንባታ" በሚል መሪ ሐሳብ ሀገራዊ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሰይፈ ደርቤ በመድረኩ ባደረጉት ንግግር፣ ተቋሙ ከምስረታው ባልተናነሰ ሁኔታ በለውጡ መንግሥት በተከናወነው ዘርፈ ብዙ ሪፎርም ምክንያት ዳግም ተወልዷል ማለት እንደሚቻል ገልጸዋል።
እንደ ዋና ሥራ አስኪያጁ ገለጻ፤ የተከናወነው የእሳቤ፣ የሕግ፣ የአደረጃጀትና የአሠራር ለውጥ ተቋሙ በአፍሪካ ደረጃ አስተማማኝና ተፅዕኖ ፈጣሪ የዜና ምንጭ እንዲሆን ማስቻሉን ጠቁመዋል።
ይህ የሪፎርም እርምጃ ድርጅቱ ብሔራዊ ጥቅምን ለማስጠበቅና ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠር የሚያስችል ጠንካራ አቅም እንዲላበስ ማድረጉንም አቶ ሰይፈ አብራርተዋል።
በአሁኑ ወቅት ተቋሙ ተደራሽነቱን በማስፋትና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ራሱን በማደራጀት፣ ከኢትዮጵያ አልፎ የአፍሪካ ድምፅ በመሆን የወል ትርክት በመገንባት ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
#ethiopianbroadcastingcorporation #ena #ethiopia #mediareform #nationalnarrative #mediaexcellence

5 months ago
የሚዲያ ልህቀት ማዕከል ለመጀመሪያ ጊዜ በምርጫ ዘገባ ያሰለጠናቸውን 36 ጋዜጠኞች አስመረቀ
#ethiopia | የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን አዲስ ባቋቋመው የሚዲያ ልህቀት ማዕከል አማካኝነት፣ በምርጫ ዘገባ ላይ ለ21 ቀናት ልዩ ሥልጠና የወሰዱ 36 ጋዜጠኞችን መጋቢት 12 ቀን 2018 ዓ.ም በሒልተን ሆቴል አስመርቋል።
ሰልጣኞቹ ከተለያዩ የግልና የሕዝብ መገናኛ ብዙኃን የተውጣጡ ሲሆኑ፣ በዘርፉ ምሁራን የታገዙ 12 ልዩ ልዩ ኮርሶችን ወስደዋል።
የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራልና የባለሥልጣኑ የቦርድ ሰብሳቢ፣ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴንዐጋዜጠኞች በየትኛውም ሥርዓት ውስጥ ለሀገርና ለብሔራዊ ጥቅም የማያወላዳ አቋም ይዘው መሥራት እንዳለባቸው አጽንኦት ሰጥተዋል።
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር፣ ወይዘሮ ሃይማኖት ዘለቀ ጋዜጠኞች ያገኙትን ዕውቀት መሬት ላይ በማውረድ ለሀገር ግንባታና ለጋራ ትርክት ትኩረት ሰጥተው እንዲሠሩ ጥሪ አቅርበዋል።
"የሙያ ብቃት ለመገናኛ ብዙኃን ልህቀት" በሚል መሪ ሐሳብ የተከናወነው ይህ መርኃ-ግብር፣ ጋዜጠኞች በምርጫ ወቅት ሊኖራቸው የሚገባውን ጥንቃቄና የዘገባ ጥራት ለማሻሻል ያለመ ነው።
በመድረኩ ላይ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ከበደ ዴሲሳ፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሳሙዔል ክፍሌና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ይህ የልዩ ትኩረት ዘርፍ ጋዜጠኝነት ሥልጠና በቀጣይም በተለያዩ ዘርፎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል።
#getu #ethiopia #mediaexcellence #journalismtraining #electionreporting #emaa #addisababa #የሚዲያልህቀት #ጋዜጠኝነት #ኢትዮጵያ #ምርጫዘገባ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

Comments