1 month ago
የሮተሪ ክለብ እና የአርቲስት ግርማ ይፍራሸዋ የበጎ አድራጎት አጋርነት ለመቄዶንያ ማህበር የገንዘብ ድጋፍ አስገኘ
#ethiopia | የምዕራብ አዲስ አበባ ሮተሪ ክለብ 35ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ሲያከብር ከታዋቂው የፒያኖ አርቲስት ግርማ ይፍራሸዋ ጋር በመሆን ለመቄዶንያ የአረጋውያንና የአእምሮ ሕሙማን መርጃ ማኅበር የ700 ሺህ ብር የገንዘብ እርዳታ አበርክቷል።
ይህ የገንዘብ ድጋፍ ባለፈው ግንቦት ወር በሸራተን አዲስ ሆቴል ሙዚቃ ለሰብአዊነት በሚል መሪ ቃል በተካሄደው የበጎ አድራጎት የፒያኖ የሙዚቃ ምሽት ከተሰበሰበው ገቢ የተገኘ መሆኑ ተገልጿል።
ሮተሪ ክለቡ ባለፉት 35 ዓመታት በተለያዩ የኅብረተሰብ ልማትና በጎ አድራጎት ሥራዎች ሲሳተፍ መቆየቱን የጠቀሱት የክለቡ ፕሬዝዳንት ብሩክ ተሾመ፣ ከአርቲስት ግርማ ይፍራሸዋ ጋር በመሆን የጥበብ ሥራን ለሰብአዊ አገልግሎት ማዋል በመቻላቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።
አርቲስት ግርማ ይፍራሸዋ በበኩሉ የሙዚቃ ሙያዉ ለእንዲህ ዓይነቱ የበጎ አድራጎት ተግባር በመዋሉ የላቀ እርካታ እንደተሰማው ገልጾ፣ ለዝግጅቱ ስኬት አስተዋጽኦ ላደረጉት የሮተሪ ክለብ አባላትና ለታዳሚዎቹ በሙሉ ምስጋና አቅርቧል።
መቄዶንያ የአረጋውያንና የአእምሮ ሕሙማን መርጃ ማኅበርም ለተደረገለት ይህ ጠቃሚ ድጋፍ ለአዘጋጆቹና ለተባባሪዎቹ ያለውን ምስጋና ገልጿል።
#macedoniahumanitarianassociation #rotaryclub #girmayifrashewa #charity #humanitarianaid #ethiopianmusic #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

Comments