2 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) ሴፕቴምበር 23, 2026 (እ.ኤ.አ) ኳስ ለመጫወት ከቤቱ የወጣው የ23 ዓመቱ የሚኒሶታ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ቅዱስ ደረጀ (ፍቅረማርያም)፣ ከቤቱ 7 ደቂቃ ብቻ ርቀት ላይ በጭንቅላቱ ላይ በተተኮሰ ጥይት ህይወቱ አልፎ ተገኝቷል። ትልቅ ህልም የነበረው፣ ማህበረሰቡን አክባሪ እና ህፃናትን ኳስ የሚያሰለጥነው ቅዱስ፣ 24ኛ ዓመት ልደቱን ለማክበር እና የፕሮጀክት ማናጀር ሆኖ ለመመረቅ በዝግጅት ላይ ነበር።
ሆኖም የፖሊስ አካላት በአጭር ሰዓታት ውስጥ "ምንም ዓይነት የወንጀል ድርጊት የለበትም (no foul play)" የሚል መደምደሚያ በመስጠት ቤተሰቡን አሳዝነዋል። በሚኒሶታ የሚገኙ የአ*ስከሬን ምርመራ (autopsy) ማዕከላት ጥያቄያቸውን ባለመቀበላቸው፣ ቤተሰቡ ለገለልተኛ ምርመራ የልጃቸውን አስከሬን እስከ ካንሳስ ግዛት ድረስ ለመላክ ተገደዋል።
የቅዱስ ቤተሰቦች ይህን አሳዛኝ ገጠመኛቸውን ሲያካፍሉ፣ "ይህ በኛም ቤተሰብ ላይ ደርሶ ነበር" የሚሉ፣ ልጆቻቸውን በድንገተኛ እና ባልተብራራ ሁኔታ ያጡ በርካታ ወገኖች እንዳሉ ታዝበዋል። በመሆኑም በሚኒሶታ ለሚኖሩ የኢትዮጵያ፣ የኤርትራ እና መላው የአፍሪካ ማህበረሰብ ክፍሎች ክፍት ደብዳቤ አውጥተዋል።
ቤተሰቦቹ ማህበረሰቡን እና የህግ አካላትን የሚጠይቁት መሰረታዊ የፍትህ ጥያቄዎች፦
1ኛ. የማንኛውም ወጣት ሞት መንስዔ ከመረጋገጡ እና ከመዘጋቱ በፊት ጥልቅ እና ተገቢ ምርመራ ይደረግ።
2ኛ. ቤተሰቦች የልጃቸውን አስከሬን የማየት፣ በክብር የመያዝና መረጃ በፍጥነት የማግኘት መብታቸው ይጠበቅ።
3ኛ. የህክምና ሪኮርዶችን የማግኘት እና የገለልተኛ ምርመራ (Independent autopsy) የማድረግ መብት ለቤተሰቦች በግልፅ ይነገር።
ማስረጃዎች በአግባቡ ይጠበቁ፤ የቤተሰብ ጥያቄዎችም ግልፅ ምላሽ ያግኙ።
ቤተሰቦቹ "በቃ! ዝምታ ይሰበር! ማንም ቤተሰብ ብቻውን መቆም የለበትም!" በማለት፣ በተመሳሳይ ሁኔታ ልጆቻቸውን ያጡ እና ያልተመለሰ ጥያቄ ያላቸው ቤተሰቦች አደባባይ እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።
ይህንን መልዕክት በቤተክርስቲያን፣ በመስጊድ እና በማህበረሰብ ስብስቦች እንድታጋሩት፣ እንዲሁም ሀዘን ከደረሰባቸው ቤተሰቦች ጎን ቆማችሁ ለፍትህ ድምፅ እንድትሆኑ ቤተሰቦቹ ጠይቀዋል። በተመሳሳይ ሁኔታ ፍትህ ያጣችሁ ወገኖች፣ መረጃችሁን (የሟቹን ስም፣ ከተማ፣ የሞተበትን ቀን እና ያልተመለሱ ጥያቄዎችን) በሚከተለው የቤተሰቡ ኢሜል አድራሻ በምስጢር ማጋራት ትችላላችሁ፦
kidusefamily @ gmail .com #justiceforkidus #habeshaunited #protectouryouth

Comments