1 month ago
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በደቡብ ሱዳን የቤት ግንባታ ለማከናወን ስምምነት ፈጸመ
***********************
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በደቡብ ሱዳን ጁባ ከተማ በቤት ግንባታ ዘርፍ ለመሰማራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል።
ይህ ስምምነት በሁለቱ ሀገራት መሪዎች ደረጃ የተደረሰውን የጋራ ልማት ትብብር ተከትሎ የመጣ ሲሆን፣ በኮርፖሬሽኑ እና በደቡብ ሱዳን ማዕከላዊ ኢኳቶሪያል ግዛት መካከል በቤት ልማትና አስተዳደር ዘርፎች በጋራ ለመሥራት የሚያስችል መሠረት ጥሏል።
ስምምነቱን የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ረሻድ ከማል (ዶ/ር) እና በደቡብ ሱዳን ማዕከላዊ ኢኳቶሪያል ግዛት አስተዳዳሪ ሚስተር ኢማኑኤል አዲል ፈርመውታል።
በዚህ ውል መሠረት ኮርፖሬሽኑ ያለውን የረጅም ጊዜ ልምድና የቴክኒክ አቅም በመጠቀም በጁባ ከተማ ዘመናዊ የመኖሪያ ቤቶች፣ የንግድ ሕንፃዎችና የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ግንባታን ያከናውናል።
ዋና ሥራ አስፈጻሚው ረሻድ ከማል (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ ኮርፖሬሽኑ በምሥራቅ አፍሪካና በመላው አህጉሪቱ ገበያዎች ለመሰማራት ሲያደርግ የቆየው ዝግጅት አሁን ወደ ተግባር ምዕራፍ ተሸጋግሯል።
ስምምነቱ የሁለቱን ሀገራት የኢኮኖሚ ትስስር ከማጠናከር ባለፈ፣ ኮርፖሬሽኑ ያለውን ውጤታማ ተሞክሮ ለግዛቱ ባለሙያዎች የሚያጋራበትንና የአቅም ግንባታ ሥልጠና የሚሰጥበትን ዕድል ያመቻቻል።
የማዕከላዊ ኢኳቶሪያል ግዛት አስተዳዳሪ ሚስተር ኢማኑኤል አዲል በበኩላቸው፣ በኢትዮጵያ ያለው ፈጣን የከተሞች ለውጥና የቤት ልማት ተሞክሮ ለአፍሪካውያን ተምሳሌት መሆኑን ጠቅሰው፣ ይህንኑ ስኬት በጁባ ከተማ ተግባራዊ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የስምምነቱን አፈጻጸም በቅርበት የሚከታተልና ዝርዝር የፕሮጀክት ሰነዶችን የሚያዘጋጅ የጋራ ቴክኒክ ኮሚቴ እንዲቋቋም የተወሰነ ሲሆን፣ ይህም የኢትዮጵያን የቤቶች ልማት ተሞክሮ ወደ ጎረቤት ሀገራት ለማስፋፋት ትልቅ መነቃቃትን ይፈጥራል ተብሏል።
Ethiopian Broadcasting Corporation #ethiopia #southsudan #juba #federalhousingcorporation #realestatedevelopment

Comments