9 days ago
''ኢሬቻ የሰላም፣ የአንድነት እና የአብሮነት'' የዋዜማ ድግስ
#ethiopia | ኢስት አፍሪካ ኢንተርቴይንመንት እና ኢቨንትስ የመስከረም 22ቱን ''ኢሬቻ የሰላም፣ የአንድነት እና የአብሮነት'' በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው የዘንድሮው የፊንፊኔ ኢሬቻ ዋዜማ ፌስቲቫል፣ በዓል ዝግጅት አስመልከቶ በሰጠው መግለጫ፣ በጊዮን ሆቴል ግቢ ውስጥ ከጠዋት እስከ ማታ በሚካሄደው ፕሮግራም ላይ ከሩጫና ከሙዚቃ ኮንሰርቱ በተጨምሪ የ «ሚስ ዩኒቲ» የቁንጅና ውድድር እንደሚኖሩ አስታወቀ።
በዚህ በዓል ላይ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተወጣጡ ታዋቂ አርቲስቶች የሚሳተፉ ሲሆን አዘጋጆቹ ለታዳሚዎች ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር በርካታ ቅድመ ዝግጅቶችን አድርገናል ብለዋል።
የዝግጅቱ ትኬት በአዲስ አበባ፣ በሸገር ከተማ እና በተለያዩ የክልል ከተሞች በኤጀንቶች በኩል እየተሸጠ የሚገኝ ሲሆን፣ በተጨማሪም በቴሌብር አፕሊኬሽን «East Africa Entertainment and Event Ticket» በሚለው ክፍል ገብቶ መግዛት ይቻላል ተብሏል።
ከክልል ከተሞች ለሚመጡ ታዳሚዎች ትኬት በሚገዙበት ወቅት የተዘጋጀ የትራንስፖርት አማራጭ ስላለ፣ ትኬት ከሚሸጡላቸው ወኪሎች መረጃውን በመጠየቅ በአንድነት ወደ ዝግጅቱ ቦታ መጓዝ የሚችሉ ሲሆን ፤ ታዳሚዎች ምግብና መጠጥ ለመፈለግ ከግቢ ውጭ በመውጣት ለተጨማሪ እንግልትና ወጪ እንዳይዳረጉም በግቢው ውስጥ በተመጣጣኝ ዋጋ የምግብና የመጠጥ አገልግሎት ተዘጋጅቷል።
በተጨማሪም ከሩቅ ለሚመጡና ታዳሚዎች የሚሆኑ ሰፋፊ የማረፊያ ድንኳኖች መተከላቸዉን የገለጹት አዘጋጆቹ ይህ በዓል ታዳሚዎች ከሚወዷቸው አርቲስቶች ጋር በመሆን ዘና የሚያሉበትና የማይረሱትን መልካም ትዝታ የሚያስቀሩበት እንዲሆን ተደርጎ የተዘጋጀ በመሆኑ ሙሉ የህብረተሰብ ክፍል በዝግጅቱ ላይ እንዲታደምና በዓሉን በአንድነት እንዲያከብር ጥሪ አቅርበዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu
#irrecha #finfinnee #irrecha2019 #ethiopia #peaceandunity #irrechafestival #eastafricaentertainment

22 days ago
የኢሬቻ ዋዜማ በደማቅ ዝግጅቶች ሊከበር ነው
#ethiopia | «ኢሬቻ የሰላም፣ የአንድነት እና የአብሮነት» በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው የዘንድሮው የፊንፊኔ ኢሬቻ ዋዜማ ፌስቲቫል፣ ባህልን፣ ስፖርትን፣ ኪነ-ጥበብንና ማህበራዊ ትስስርን በሚያጣምር መልኩ እንደሚከናወን ተገልጿል።
ዝግጅቱን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና ከኦሮሚያ ክልል መንግሥት ጋር በመተባበር እያዘጋጀ ያለው ኢስት አፍሪካ ኢንተርቴመንት እና ኤቨንት ኦርጋናይዘር በዘርፉ ከ10 ዓመታት በላይ ልምድ ያለው ተቋም መሆኑም ኹነቱን አስመልክቶ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተገልጿል።
ፌስቲቫሉ መስከረም 22 ቀን 2019 ዓ.ም በጊዮን ሆቴል የሚካሄድ ሲሆን፣ ከታቀዱት ዋና ዋና መርሃ ግብሮች መካከል እስከ 50 ሺህ ተሳታፊዎችን የሚያሳትፈው የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ይገኝበታል። ሩጫው ለሰላም፣ ለወንድማማችነት፣ ለመቻቻልና ለአንድነት መልዕክት የሚያስተላልፍ እንደሚሆን አዘጋጆቹ ገልጸዋል።
የበዓሉ ሌላው ልዩ መርሃ ግብር የ10 ሺህ ሲኒ የቡና ሥነ-ሥርዓት ነው። በጊዮን ሆቴል ከ8 እስከ 10 ሜትር ርዝመት ባለው ግዙፍ እረከቦት ላይ የሚከናወነው ይህ መርሃ ግብር የሃይማኖት አባቶችን፣ የመንግሥት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችን፣ ዲፕሎማቶችን፣ የሴቶችና የወጣቶች ተወካዮችን በማሳተፍ የሰላም ውይይት የሚካሄድበት ይሆናል።
በዋዜማው ሌሊቱን ሙሉ የሚቆየው ታላቅ የሙዚቃ ኮንሰርትም በዓሉን ከሚያደምቁ ዝግጅቶች መካከል ተጠቅሷል። ከቀኑ 12 ሰዓት እስከ ንጋቱ 12 ሰዓት ድረስ በሚቆየው ኮንሰርት በርካታ ታዋቂ አርቲስቶች የሙዚቃ ሥራዎቻቸውን እንደሚያቀርቡ ተገልጿል።
የ«ሚስ ዩኒቲ» የቁንጅና ውድድርም የፌስቲቫሉ አካል ሲሆን፣ የተለያዩ ባህሎችንና የሕብረ-ብሔራዊ አንድነትን ለማጉላት የታቀደ መሆኑ ታውቋል።
ከእነዚህ ዝግጅቶች በተጨማሪ የኦሮሚያ ባህላዊ የምግብና መጠጥ ፌስቲቫል፣ የከተማዋን የኮሪደር ልማት ለማስተዋወቅ የሚደረግ ጉብኝት እና ከሰላም ውይይቶች ጋር የሚቀናጁ መርሃ ግብሮች እንደሚካሄዱ ተገልጿል።
ለሙዚቃ ኮንሰርት የመግቢያ ትኬት ዋጋ መደበኛ 1,000 ብር፣ ቪአይፒ 10,000 ብር እና ቪቪአይፒ 20,000 ብር መሆኑም ተገልጿል።

Comments