1 month ago
“በእምነታችን የተለያየን ብንሆንም፣ ሰውነታችን እና የጋራ ሀገራችን አንድ ያደርጉናል” - ሊቀ ትጉኃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ
***********
15ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን፥ “እምነትን በተግባር፡ ሰላምን ለሁለንተናዊ ልማት በኢትዮጵያ” በሚል መሪ ቃል ያከበረው የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ፤ በተጓዳኝ 18ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውንም አካሂዷል።
የጉባኤው ዋና ጸሐፊ ሊቀ ትጉኃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ በዚሁ ወቅት፣ ኢትዮጵያ የበርካታ እምነቶች፣ ባህሎች እና ቋንቋዎች የጋራ ቤት መሆኗን አንስተዋል።
አክለውም፣ የሃይማኖቶች ስምምነት በጋራ ማዕድ ከመቋደስ አልፎ የሀገርን ዳር ድንበር ለማስከበር እስከ መስዋዕትነት የጸና ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያዊነት እና ሃይማኖት ልክ እንደ ውብ የጥበብ ሸማ የተሰናሰሉ መሆናቸውን ተናግረዋል።
የተለያዩ ቀለማት ያሏቸው ክሮች ተዋህደው ውብ ልብስ እንደሚሆኑ ሁሉ፤ ሃይማኖቶችም ሰላምን በመስበክ እና ትውልድን በመቅረጽ በጋራ ሀገርን ይገነባሉ ነው ያሉት።
አያይዘውም፣ “እኛ በእምነታችን የተለያየን ብንሆንም፣ ሰውነታችን እና የጋራ ሀገራችን አንድ ያደርጉናል፤ ሃይማኖት የግላችን፣ ኢትዮጵያ ደግሞ የጋራ ቤታችን ናት” ሲሉ ገልጸዋል።
ይህን ወርቃማ እሴት ጠብቆ ለትውልድ ማስተላለፍ እንደሚገባም አደራ ብለዋል።
አሁን ያለው ትውልድ ልዩነትን እንደ ስጋት ሳይሆን እንደ ውበት የሚያይ፣ በሀገር ብሔራዊ ጥቅም የማይደራደር እና ለሰላም ዘብ የሚቆም መሆኑንም መስክረዋል።
በአብሮነት ጉዞ ውስጥ ልዩነቶችን በመጠቀም ግጭት ለመፍጠር የሚደረጉ ሙከራዎች እንደነበሩ ያነሱት ዋና ጸሐፊው፤ ማኅበራዊ ሚዲያ ከሰላም ይልቅ የግጭት መስበኪያ ሆኖ እንዳይቀጥል ከመንግሥት ጋር በትብብር መሥራት እንደሚገባ ጠቁመዋል።
የሃይማኖት አባቶችም በኅብረተሰቡ ዘንድ ያላቸውን የላቀ ተቀባይነት ተጠቅመው የተጣላን በማስታረቅ እና የተራራቀን በማቀራረብ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።
መከባበር ጥሩ ቢሆንም፣ በቂ አይደለም፤ ረሃብ እና በሽታ ሃይማኖት ስለማይመርጡ፣ ከመከባበርም አልፎ በመተባበር እና አብሮነትን በማሳደግ በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ መሥራት ይገባናል ሲሉም ለመላው ኢትዮጵያውያን መልዕክት አስተላልፈዋል።
በሔዋን ጌታቸው
#ethiopia #interreligiouscouncilofethiopia #socialcohesion #peacebuilding #ebc

Comments