28 days ago
ከነባር ዕሴት እስከ ዘመናዊ አስተዳደር፡ የመደመር ዕይታ እና የሰው ተኮር ልማት አዲስ ምዕራፍ
*******************
ኢትዮጵያ በብዙ የፈተና እና የለውጥ ማዕበሎች ውስጥ አልፋ ዛሬ ላይ የጸናችው በሕዝቦቿ መካከል ባሉ ጥንታዊ የማኅበራዊ ትስስር ገመዶች አማካኝነት ነው።
የመረዳዳት ባህላዊ ተቋሞቻችን የችግር ጊዜ ማለፊያዎች ብቻ አይደሉም፤ ይልቁንም የሕዝቡ የእርስ በርስ መደጋገፍ እና የጋራ ዕጣ ፈንታን አብሮ የመቅረፅ ጥበብ ማሳያ ታሪካዊ መሠረቶች ጭምር ናቸው።
የመደመር ዕሳቤ እነዚህን ነባር ማኅበራዊ ሀብቶች እና ጥበቦች ከዘመናዊ የመንግሥት አስተዳደር ፍልስፍና ጋር በማጣመር፣ ልማትን ከመሠረተ ልማት ዝርጋታ ባለፈ የሰውን ልጅ ሁለንተናዊ ሕይወት በማሻሻል ላይ ያተኮረ ሰፊ ሥራ አድርጎ ይመከታል፤ ይተገብራል።
በመደመር ዕሳቤ የሚከናወኑ ሰው ተኮር የልማት ሥራዎች በዋናነት የዜጎችን የዕለት ተለት ሕይወት በተጨባጭ የሚቀይሩ የማኅበራዊ ደህንነት ፕሮግራሞች ናቸው።
የቆየውን "ያለንን የማጋራት" ባህል ወደ ተደራጀ የመንግሥት እና የማኅበረሰብ መዋቅር በመቀየር፣ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ዜጎችን፣ አረጋውያንን እና አቅመ ደካሞችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የማዕድ ማጋራት እና የመኖሪያ ቤት ዕድሳት ሥራዎች በስፋት እየተከናወኑ ይገኛሉ።
ከዚህ በተጨማሪ ህጻናት በምግብ እጥረት ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው እንዳይቀሩ የተዘረጋው የትምህርት ቤት ምግባ መርሐ ግብር፣ በነገው ትውልድ ላይ የሚደረግ ትልቅ የሰው ሀብት ልማት ኢንቨስትመንት ሲሆን፣ ይህም የድሃ ወላጆችን ሸክም ከማቃለሉም በላይ የትምህርት ተሳትፎ እና ጥራትን ማሳደግ አስችሏል።
በተመሳሳይ የከተሞች የኮሪደር ልማት እና የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎችም የሰው ልጅን ምቾት እና ጤና ማዕከል ያደረጉ ናቸው። የመሠረተ ልማት ዝርጋታው የአሽከርካሪዎችን ብቻ ሳይሆን የእግረኞችንም ምቾት ታሳቢ ያደረገ ነው።
ሰፋፊ የእግረኛ እና የብስክሌት መንገዶች፣ የህጻናት መጫወቻዎች እና የህዝብ መዝናኛ ስፍራዎች የከተሞችን ገጽታ ከመቀየር በተጓዳኝ የዜጎችን አዕምሯዊ እና አካላዊ ጤና የሚያጎለብቱ ሆነዋል።
በሌላ በኩል ጥንታዊው ጉልበትን አስተባብሮ በጋራ የማረስ እና የመገንባት የደቦ (ጅጌ) ባህል ዛሬ በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ችግኞችን በመትከል ለአካባቢ ጥበቃ እና ለምግብ ዋስትና በሚደረገው ሀገራዊው የአረንጓዴ ዐሻራ ንቅናቄ ላይ ተመልሶ በጥቅም ላይ ውሏል።
በመሆኑም ባህላዊ ዕሴቶቻችንን ሳንለቅ ከዘመናዊ የልማት አስተሳሰብ ጋር አጣጥሞ መጓዝ ልማቱን ማፋጠን ብቻ ሳይሆን፣ እያንዳንዱን ዜጋ የልማቱ ባለቤት እና ተጠቃሚ ያደርጋል።
ይህ ሰው ተኮር የልማት አቅጣጫ ሀገራችንን በጽኑ መሠረት ላይ በመገንባት ለቀጣዩ ትውልድ የተሻለች እና የበለጸገች ኢትዮጵያን ለማስረክብ የሚያስችል ታላቅ ሀገራዊ ራዕይ ነው።
በሔዋን ጌታቸው
#ethiopia #humancentereddevelopment #urbancorridor #greenlegacy #traditionalvalues #socialcohesion #ebc

Comments