1 month ago
የከንፈርና ላንቃ መሰንጠቅ (ክፍተት) ላለባቸው ሕፃናትና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ነጻ ሕክምና እየተሰጠ ነው
*****************
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሕክምናና ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል “ኦፕሬሽን ስማይልስ” ከተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በመቀናጀት የከንፈርና ላንቃ መሰንጠቅ (ክፍተት) ላለባቸው ሕፃናትና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ነጻ ሕክምና እየሰጠ ነው።
በሆስፒታሉ ተገኝተው የሕክምና አሰጣጡን የተመለከቱት የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ፥ እንደ ሀገር ከከንፈርና ላንቃ መሰንጠቅ ጋር የሚወለዱ ሕጻናት ቁጥር በዓመት ከ4 ሺህ በላይ እንደሚሆኑ በጥናት መለየቱን ተናግረዋል።
የከንፈርና ላንቃ መሰንጠቅ በሕጻናትም ሆነ በአዋቂዎች ላይ የሚያስከትለውን ማህበራዊ ጫና ለማስወገድ የሕክምና አገልግሎቱን ተደራሽነት ለማሳደግ በቅንጅት እየተሠራ መሆኑን ዶክተር ደረጀ ገልጸዋል።
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሕክምናና ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል፣ ኦፕሬሽን ስማይልስ ከተባለው ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በመቀናጀት አሁን እየሰጠው ያለው ሕክምናም የዚሁ አካል መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።
የከንፈርና ላንቃ መሰንጠቅ ያለባቸው ሕጻናትን ቤት ለቤት የመለየት ሥራ ተሠርቶ፤ በሆስፒታሉ ሕክምናው በነጻ የሚሰጥበት ማዕከል በመክፈትና ባለሙያዎችን በማሰልጠን ወደ ሥራ መገባቱ ተገልጿል።
በተደረገው ዳሰሳም የከንፈርና ላንቃ መሰንጠቅ ያለባቸው ከ150 የሚበልጡ ሕጻናት ተለይተው እስከአሁን 60 ሰዎች ቀዶ ሕክምናው እንደተሠራላቸው የተናገሩት ደግሞ የኦፕሬሽን ስማይል ካንትሪ ማኔጀር መብራቱ በጅጋ (ዶ/ር) ናቸው።
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሕክምናና ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የከንፈርና ላንቃ መሰንጠቅ ሕክምና በተሟላ ሁኔታ መስጠት መጀመሩና አገልግሎቱም በዘመቻና በሳምንት ለሁለት ቀናት በቋሚነት እየተሰጠ መሆኑ ተገልጿል።
#hawasauniversity #hucsh #operationsmile #cleftlip #cleftpalate #ebc