20 days ago
በአዲስ አበባ የተከናወነው የከተማ ልማት ሥራ ለዓለም ትምህርት የሚሰጥ ነው - ጋዜጠኛ ዳኒኤል ካርል
*************************
በአዲስ አበባ የተከናወነው የከተማ ልማት ሥራ ከተሞችን ለዜጎች ምቹ አድርጎ መሥራት እንደሚቻል ለዓለም ትምህርት የሚሰጥ ነው ሲል እንግሊዛዊው ጋዜጠኛ ዳኒኤል ካርል ተናገረ።
አዲስ አበባ ከተማ በዚህ ልክ ውብ ሆና እንድትለማ የመሪዎች ቁርጠኝነት ወሳኝ መሆኑንም ገልጿል።
የትናንት አቧራዋን አራግፋ ስሟን በግብሯ ልትገልጥ የተነሳችው አዲስ አበባ ከክልል ከተሞች ምሳሌነት አልፋ ስሟ አድማስን ተሻግሮ በሁሉም መስክ ፊት ከቀደሙ ሐገራት አስተጋብቷል።
ለዚህም ይመስላል ያቺ በመኪና ጥርቅም ከቆሻሻ ጋር ለረጅም ዓመት ተወዳጅታ የዘለቀችው አዲስ አበባ በአጭር ጊዜ እንደምን ስሟን መጥና ተገኘች? ሲሉ ዓለም አቀፍ ምሁራን ጭምር ጥናት ማድረግ የጀመሩት።
መቀመጫቸውን በእንግሊዝ ሀገር ባደረጉ ስምንት ምሁራን እና ጋዜጠኞችም በጋራ ታትሞ የተመረቀው መጽሐፍም ለዚህ ማሳያ ሆኗል።
በጥናቱ ከተሳተፉት ሰዎች መካከል አንዱ የሆነው ጋዜጠኛ ዳኒኤል እንደሚለው ታዲያ ከጥቂት ዓመታት በፊት የምናውቃት አዲስ አበባ በአጭር ጊዜ ውስጥ ያከናወነችው የከተማ ልማት ግንባታ ዓለም ሁሉ ሊያያቸው ከሚጓጓላቸው ከተሞች ተርታ አሰልፏታል።
እንደ ጋዜጠኛ ዳኒኤል ገለጻ ከሆነ ታላቅ ራዕይን ያነገበ፣ ከዛሬ አልፎ ለቀጣይ ትውልድ ወረትን ለመጣል የሚተጋ መሪ መኖር ለከተማዋ በዚህ ልክ መቀየር ማርሽ ቀያሪ ሆኖ ተገኝቷል።
“የተከናወኑት የከተማ ልማት ሥራዎች አሁን ስሟን በግብሯ የገለጠች አዲስ አበባን ለዓለም ገልጦ አሳይቷል” የሚለው ጋዜጠኛ ዳኒኤል፣ በተለይም የአፍሪካ መሪዎች ከተሞቻቸውን እንዴት ዜጎችን በሚመጥን ልክ መሥራት እንደሚችሉ በተሞክሮነት የምትቀርብ ሆናለች ማለቱን ኤኤምኤን ዘግቧል።
#ebc #ethiopia #addisababa #development #horizonofhope

Comments