2 months ago
ኢትዮጵያውያን መከሩ፤ ኢትዮጵያም አሸነፈች! - የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
***********
ኢትዮጵያ የኃይልና የግጭት ፖለቲካን በቃ በማለት ልዩነቶቿን በሰለጠነ የምክክር መድረክ ለመፍታት የወሰደችው እርምጃ፣ የሀገራችንን የፖለቲካ ምህዳር በአዲስ መሠረት ላይ የጣለ ታሪካዊ ድል ሆኗል ሲል የኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገለጸ።
የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የመዝጊያ ሥነ-ሥርዓቱ ዛሬ የተከናወነውን የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ በተመለከተ በፌስቡክ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ባጋራው መልዕክት፥ በኢትዮጵያ የጥቂት ልሂቃን የጥቅም ድርድር የነበሩ የዝግ በር ልማዶችን የቀየረና፣ ሰፊውን ሕዝብ የውሳኔው ቀጥተኛ ባለቤት ያደረገ አዲስ ምዕራፍ ተከፍቷል ብሏል።
በዚህም ዜጎች ለዘመናት ያጋጠሟቸውን ታሪካዊ ስብራቶች፣ ጥልቅ አለመግባባቶችና የሐሳብ ልዩነቶች በኃይል ሳይሆን በመደማመጥና በጋራ ጥበብ መፍታት እንደሚችሉ በተግባር አስመስክረዋልም ብሏል አገልግሎቱ።
በሁሉም ክልልሎች ከቀበሌ እስከ ፌደራል በተወከሉ የኅብረተሰብ ክፍሎች ሴቶች፣ ወጣቶች፣ አርሶ/ አርብቶ አደሮች፣ አረጋውያን፣ አካል ጉዳተኞች፣ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የብሔር-ብሔረሰቦችና እምነቶች ተወካዮች እንዲሁም ምሁራንና ሊቃውንት በስምንት አጀንዳዎች ላይ ባደረጉት ሁሉን አቀፍ ውይይት የ130 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንን ድምፅ ማድመጣቸውን ገልጿል።
በዚህም ዘላቂ ሰላም የሚረጋገጠው በንግግር ብቻ መሆኑን ፍጹም አካታች በሆነ አርዓያነት አረጋግጠዋል ነው ያለው።
አገልግሎቱ አክሎ እንዳለው፣ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ከባንዳዎቸ ጋር ተጣምረው በዲጂታል ሚዲያ የሐሰት መረጃና ውዥንብር ለመፍጠር ቢሞክሩም፣ የምክክር ኮሚሽኑ ተቋማዊ ገለልተኝነቱን በጥብቅ ዲስፕሊን በመመራት በጽናት አስከብሯል።
ከ54 በላይ የሚዲያ ተቋማትና 461 ጋዜጠኞች ሂደቱን በቀጥታ ሽፋን በመስጠት ትክክለኛ መረጃን ለህብረተሰቡ ተደራሽ ማድረግ መቻላቸውን ጠቅሷል።
በልጆቿ ፍጹማዊ ፅናት በተከናወነው በዚህ ታሪካዊ ክንውን፣ ኢትዮጵያ የራሷን ዕድል በገዛ እጇ መወሰን እንደምትችል በተግባር አሳይታለች፤ ኢትዮጵያውያን መከሩ፣ ኢትዮጵያም አሸነፈች ብሏል የኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት።
#ethiopia #nationaldialogue #peacebuilding #historicconsensus #ethiopiawins #ebc

"ከዚህ በኋላ የኢትዮጵያ ጉዞ የሚሆነው መስቀለኛ ሳይሆን ቀጥ ያለ ርቱዕ፣ ብርቱ የዕድገት እና የኅብረት መንገድ ብቻ ነው።"
ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ
#ethiopia #nationaldialogue #historicconsensus #ethiopiawins #ebc
ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ
#ethiopia #nationaldialogue #historicconsensus #ethiopiawins #ebc
2 months ago
"እየተማከርን ሀገር እንገነባለን፣ ሀገር እየገነባንም እንማከራለን" - ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ
******************
የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ በሀገራዊ ምክክር ጉባኤ የመዝጊያ ሥነ-ሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር፣ በኢትዮጵያውያን መካከል የታየው የመከባበር እና የመደማመጥ እሴት ለነገ ተስፋችን ትልቅ ጸጋ መሆኑን ገለጹ።
ፕሬዚዳንቱ ለጉባኤው ተሳታፊዎች ባስተላለፉት መልዕክት፣ ተመካካሪዎች ሀሳብ ለሀሳብ መለዋወጣቸውን እና ከሁሉም በላይ ደግሞ ፍላጎታቸውን እንዲሁም መንፈሳቸውን ማጋመዳቸውን ገልጸዋል።
ይህ ሂደት በኢትዮጵያ የፖለቲካ ባህል ውስጥ አዲስ ጎዳና መሆኑን የጠቆሙት ፕሬዚዳንት ታየ፣ በዚህ አዲስ ጎዳና ለሕዝብ እና ለእውነት መታመን ያለው የሞራል ኃላፊነት ከፍተኛ መሆኑን አሳስበዋል።
ተሳታፊዎች ሕዝብ የሰጣቸውን አደራ በአክብሮት በመወጣታቸውም ፕሬዚዳንቱ ምስጋና አቅርበዋል።
በጉባኤው የቀረበው ምክረ-ሀሳብ በአንድ ጀምበር የሚጠናቀቅ ሳይሆን ኢትዮጵያን በማጽናት በየትውልዱ እያደገ፣ እየበለጸገ እና እየጎመራ የሚሄድ ሕያው እሳቤ መሆኑን ገልጸዋል።
"ዛሬ ያስመሰከርነው ጉዳይ ቢኖር እኛ ኢትዮጵያውያን ሁልጊዜም መምከር እንደምንችል ነው" ያሉት ፕሬዚዳንቱ፣ ምክክር እና የሀገር ግንባታ የማይነጣጠሉ እና ቀጣይነት ያላቸው ሂደቶች መሆናቸውን ተናግረዋል።
በምክክሩ የተገኙት ምክረ-ሀሳቦች በቀጣይ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ለአስፈጻሚ አካላት እና ለሌሎችም ባለድርሻ አካላት እንደሚቀርቡ አንስተዋል።
አያይዘውም፣ እነዚህን ምክረ-ሀሳቦች የሚረከቡ አካላት የሀሳቦቹ ግለት እና ራዕይ ሳይቀዘቅዝ የኢትዮጵያን እርምጃ ወደ ብሩህነት እንደሚያሻግሩት ያላቸውን የላቀ ተስፋ ገልጸዋል።
አክለውም፣ "የሀሳባችሁ፣ የዕውቀታችሁ፣ የላባችሁ እና የትጋታችሁ ሁሉ ዳኛ የኢትዮጵያ ሕዝብ መሆኑን አውቃችሁ፣ ሕዝባችን የሰጣችሁን አመኔታ በአክብሮት በመወጣታችሁ ምስጋናዬ ከፍተኛ ነው!" በማለት ለተሳታፊዎች የምስጋና መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
በለሚ ታደሰ

Sponsored by
Surafel
Comments