8 months ago
"ረመዳንን በመረዳዳት፣ በሰላም እና በዱዓ እናሳልፍ"
📍ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ
#ethiopia | የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ፣ 1447ኛው የታላቁ የረመዳን ወር መቃረቡን አስመልክቶ ለመላው የእምነቱ ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ፕሬዚዳንቱ በመግለጫቸው የረመዳን ወር መንፈሳዊ ፋይዳው የጎላና ሙስሊሙ ማኅበረሰብ በተለየ ትጋት ሊያሳልፈው የሚገባ ወር መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።
ከፌደራል ሸሪዓ ፍርድ ቤት በተገኘው መረጃ መሠረት፣ የጾሙ መጀመሪያ ቀን በጨረቃ መታየት ላይ የተመሠረተ ሲሆን ጨረቃ ማክሰኞ የካቲት 10 ምሽት ከታየች ረቡዕ የካቲት 11 ቀን የመጀመሪያው የጾም ቀን ይሆናል።
ጨረቃ ማክሰኞ ምሽት ካልታየች ጾሙ ሐሙስ የካቲት 12 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚጀምር ተገልጿል።
ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ በወሩ ሊከናወኑ በሚገባቸው ተግባራት ላይ የሚከተሉትን ዋና ዋና ነጥቦች አሳስበዋል ረመዳን የልግስና ወር በመሆኑ፣ አቅመ ደካሞችን በመርዳትና ማዕድን በማካፈል (ኢፍጣር) ማኅበራዊ ኃላፊነትን መወጣት እንደሚገባ ገልጸው አማኙ ከማንኛውም ግጭትና ፀብ በመራቅ በሰላም፣ በይቅርታና በእዝነት ወሩን ሊያሳልፍ ይገባልብለዋል።
መንፈሳዊ ልዕልና የሚኖረው ሰላም ሲኖር ነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ፣ ለሀገራችን ኢትዮጵያ ሰላም፣ ለሕዝባችን ደኅንነትና ምእመኑ በጾም ወራት አጥብቆ ዱዓ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።
ረመዳን ከአምስቱ የእስልምና ማዕዘናት አንዱ እንደመሆኑ፣ ሁሉም ሕዝበ ሙስሊም የአላህን ትዕዛዝ በመፈጸም በአምልኮ (ኢባዳ) እና በበጎ ሥራዎች ተጠምዶ እንዲቆይ አደራ ተብሏል።
#ramadan1447 #ramadaninethiopia #peaceandunity #ethiomuslims #hajiibrahimtufa #ramadankareem #ethiopia

Comments