13 days ago
"20 ትሪሊዮን ዶላር በየአመቱ ለጥፋት እየዋለ ነው!"
#ethiopia | ለጦርነት ከሚወጣው 20 ትሪሊዮን ዶላር ውስጥ ረሀብ ለማጥፋት 10 በመቶ ብቻ እንደሚበቃ ተጠቆመ።
በየዓመቱ በጦርነትና በግጭት ምክንያት የዓለም ኢኮኖሚ 20 ትሪሊዮን ዶላር ያጣል።
በመላው በሚደረጉ ጦርነቶች ሰብአዊ ጥፋት ብቻ ሳይሆን የኢኮኖሚ ውድመታቸው ማህበረሰቡ ከሚያስበው በላይ እጅግ ግዙፍ መሆኑን መረጃዎች አመላክተዋል።
በየዓመቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ በጦርነት፣ በግጭት እና በሁከት ምክንያት አለማችን 20 ትሪሊዮን ዶላር ታወጣለች።
ዓለም አቀፉ የሰላም አመልካች (Global Peace Index) በሚያዘጋጀው የምጣኔ ሀብትና የሰላም ጥናት ላይ ነው ይህ የተገለፀው።
ተቋሙ የጦርነትና የግጭትን የኢኮኖሚ ተፅዕኖ ሲያሰላ ዋና ዋና ወጪዎች አካቷል።
ከእነዚህ ወጪዎች መካከል በጦር መሳሪያ ግዢ፣ በመከላከያ በጀቶች፣ በወታደራዊ አገልግሎት እና የጉዳት ጥገና ላይ የሚወጡት ቀጥተኛ ወጪዎች ይገኙበታል።
በጥናቱ የተካተቱ ሌሎች ተዘዋዋሪ ወጪዎች ደግሞ በግጭት ምክንያት የሚጠፋው የሰው ህይወት፣ የአካል ጉዳቶች፣ የስነ-ልቦና ጉዳቶች፣ የምርታማነት ማጣት እና የተቋረጡ የንግድና የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴዎች ናቸው።
የተፈናቀሉ ዜጎችን የማቋቋም እና የሰብአዊ ድጋፍ ማቅረቢያ ወጪዎች ተጠቃሽ ናቸው።
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት መረጃ መሠረት በዓለም ዙሪያ ያለውን ረሃብ እስከ ፈረንጆቹ 2030 ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት በየዓመቱ የሚያስፈልገው 300 ቢሊዮን ዶላር ነው።
ይህም ከ20 ትሪሊዮን ዶላሩ 2 በመቶ ያነሰ ነው።
ከዚህ ወጪ 10 በመቶ ያህሉ እንኳን ቢቀነስ በዓለም ላይ የሚገኙ ሁሉንም ህፃናት ነፃ እና ጥራት ያለው ትምህርት ማስተማር ይቻላል።
እንዲሁም ለሁሉም ዜጎች የመጀመሪያ ደረጃ የጤና አገልግሎት ማዳረስ ይቻል ነበር ብሏል።
በየዓመቱ የሚባክነው 20 ትሪሊዮን ዶላር የቁጥር ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የሰው ልጅ የትምህርት፣ የጤና፣ የምግብ እና የሰላም ዕድል መታጣት መገለጫ መሆኑ ነው የተገለፀው።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #getutemesgen #globalpeaceindex #peacedividend #stopwar #globalnews #economicimpact #peaceforworld

Comments