4 months ago
#ፊንላንድ፦ የዓለማችን ደስተኛዋ ሀገር ለ8 ተከታታይ ዓመት! 🌍🌿
#ethiopia | ጨለማና ረጅም ክረምት ቢኖርባቸውም፣ በደስታ ግን የዓለምን ብርሃን መሆን ችለዋል!
ፊንላንድ የ2025 የዓለም የደስታ ሪፖርት (World Happiness Report) ለ8ኛ ተከታታይ ዓመት በመሪነት አጠናቃለች። ይህ ውጤት በአጋጣሚ የተገኘ ሳይሆን "በእቅድ የተገነባ" እንደሆነ ባለሙያዎች ይናገራሉ።
የፊንላንድ የደስታ ሚስጥሮች ምንድን ናቸው?
የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰሮችና ተመራማሪዎች ለዚህ ስኬት አራት ዋና ዋና ምክንያቶችን ያስቀምጣሉ፦
1. ጥልቅ ማህበራዊ ትስስር፦ሰዎች እርስ በእርሳቸው ያላቸው ግንኙነት በጣም ጠንካራ ነው።
2. በተቋማት ላይ ያለው እምነት፦ ዜጎች በመንግስት እና በማህበራዊ ተቋማት ላይ ያላቸው እምነት ከፍተኛ ነው።
3. ከተፈጥሮ ጋር መተሳሰር፦ ፊንላንዳውያን ከተፈጥሮ ጋር ያላቸው ጥልቅ ቁርኝት ለአእምሮ ሰላማቸው ትልቅ አስተዋፅኦ አለው።
4. የእኩልነት ስሜት፦የጤና እና የደህንነት አገልግሎቶች ለሁሉም እኩል መዳረሳቸው።
"ደስታ ይገነባል እንጂ አይገዛም!
ፊንላንድ "የደስታ መሰረተ-ልማት" (Infrastructure of Happiness) የምንለውን ስርዓት መገንባት ችላለች። ይህም ግለሰቦችና ማህበረሰቡ እንዲበለጽጉ የሚያደርግ ባህልና ጠንካራ ተቋማትን ያካትታል።
*ለዓለም ማስጠንቀቂያ የሆነው መረጃ፦
በተቃራኒው እንደ አሜሪካ ያሉ ሀገራት በደስታ ደረጃቸው ዝቅ ብለዋል። ላለፉት 20 ዓመታት ብቻውን የሚመገብ (Dining alone) ሰው ቁጥር በ53% መጨመሩ፣ ማህበራዊ መገለል ለደስታ ማጣት ትልቁ ምክንያት መሆኑን ያሳያል።
ትምህርቱ፦
እውነተኛ ደስታ የሚመጣው ከሀብት ብቻ ሳይሆን እርስ በእርስ ከመተማመን፣ ከተፈጥሮ ጋር ከመታረቅ እና ጠንካራ ማህበራዊ ግንኙነት ከመፍጠር ነው። ይህ ፊንላንድ ለዓለም እያስተማረች ያለችው ታላቅ የቤት ስራ ነው።
ባምላኩ ነኝ, ከጅማ ህክምና ማዕከል
ምንጭ፦
የ2025 የዓለም የደስታ ሪፖርት (ኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ፣ ጋለፕ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት)
#happiestcountry #finlandlife #worldhappinessreport #publichealth #wellbeing #socialconnection #ethiopia #jimma

Comments