2 months ago
በተጨባጭ ልማት የተረጋገጠው የጸረ-ሙስና እና መዋቅራዊ ሌብነት ትግል ቁርጠኝነት
***********************
ከለውጡ በፊት በነበሩት ዓመታት የሀገራችን ቁሳዊ፣ ተፈጥሯዊ እና የፋይናንስ ሀብት በግልጽነት እጦት እና በኮንትሮባንድ ንግድ የጥቂት የጥቅም ትስስር ኔትወርኮች መበልጸጊያ የነበረ በመሆኑ፣ ሀገራዊ ዕድገታችን ተገትቶ ቆይቷል።
ነገር ግን ባለፉት የለውጥ ዓመታት የመንግሥት የላይኛው አመራር ባሳየው ጠንካራ ቁርጠኝነት፣ መዋቅራዊ ሌብነትን በመበጠስ ሀብትን ወደ ልማት የመመለስ አዲስ ምዕራፍ ተከፍቷል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በይፋዊ ማብራሪያዎቻቸው ደጋግመው እንደገለጹት፣ በከፍተኛ የሥልጣን እርከን ደረጃ የነበረውን የሀብት ምዝበራ እና ገንዘብ ወደ ውጭ የማሸሽ ተግባር መንግሥት በቁርጠኝነት ማስቀረት ችሏል።
የሀገራችን የበላይ አመራር ሀብት የማያሸሽ እና ለሕዝብ ጥቅም የቆመ በመሆኑ፣ ቀደም ሲል ወደ ግለሰቦች ኪስ ይጎርፍ የነበረው ከፍተኛ ሀብት አሁን በቀጥታ ወደ መንግሥት ካዝና በመግባት ለተጨባጭ ልማት መዋል ጀምሯል።
✅በወርቅ እና በኤክስፖርት ዘርፍ የታየው መዋቅራዊ ድል
የዚህ መዋቅራዊ ለውጥ ትልቁ ማሳያ በወርቅ ኤክስፖርት እና በጠቅላላ የወጪ ንግድ የተመዘገበው ታሪካዊ ውጤት ነው። ከለውጡ በፊት በነበሩት 27 ዓመታት ኢትዮጵያ ከወርቅ ኤክስፖርት ያገኘችው ጠቅላላ ገቢ 3.7 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ብቻ የነበረ ሲሆን፣ አሁን ግን በአንድ ዓመት ውስጥ ብቻ 5.5 ቢሊዮን ዶላር ከወርቅ ማግኘት ተችሏል።
አሁን ይህን ያህል ገቢ የተመዘገበው አዲስ ክምችት ተገኝቶ ሳይሆን፣ በወርቅ ንግድ ላይ የነበረው የመዋቅራዊ ሌብነት እና የኮንትሮባንድ ሰንሰለት በመበጣጣሱ ነው።
ይህ የሀብት ማዳን እርምጃ በወርቅ ብቻ አላበቃም። ሀገራችን በቅርቡ ያስመዘገበችው የ11 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሸቀጦች እና አገልግሎት ኤክስፖርት ገቢ የተፈጥሮ ሀብታችን በድንገት ጨምሮ ሳይሆን፣ ቀደም ሲል በሕገ-ወጥ መንገድ ይባክን የነበረው ገቢ በቀጥታ ወደ ብሔራዊ ባንክ ካዝና መግባት በመጀመሩ የተገኘ ውጤት ነው።
✅የሕዝብን ሀብት ለሀገር ውስጥ ልማት ማዋል
መንግሥት ያዳነውን ሀብት ምን ላይ አዋለው ለሚለው ጥያቄ በአዲስ አበባ እና በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች እየታየ ያለው ፈጣን የኮሪደር ልማት በቂ እና ተጨባጭ ማሳያ ነው።
የእነዚህ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ልዩ ባሕሪ ምንም ዓይነት የውጭ ብድር ሳይጠየቅ በሀገር ውስጥ አቅም ብቻ መከናወናቸው ነው። ለአብነትም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከሚሰበስበው ገቢ ውስጥ 72 ከመቶውን በቀጥታ ለከተማዋ ሁለንተናዊ ልማት እያዋለ ይገኛል።
በዚህም መሰረት 48 ኪሎ ሜትር የተሽከርካሪ መንገድ፣ 96 ኪሎሜትር የእግረኛ መንገድ፣ እንዲሁም 100 ኪሎ ሜትር የሳይክል መንገድ ተገንብቷል።
በተጨማሪም 32 ዘመናዊ የመኪና ማቆሚያዎች፣ 9 የአውቶቡስ እና ታክሲ ተርሚናሎች፣ 430 ስማርት ፖሎች እና ከ50 ሄክታር በላይ የሚሸፍን አረንጓዴ ልማት ተጠናቅቆ ለአገልግሎት በቅቷል።
ይህ አፈጻጸም የሚያሳየው፣ የከተማ መሬት እና ማዘጋጃ ቤታዊ ገቢዎች ከመዋቅራዊ ሙስና ሲጸዱ በአጭር ጊዜ ከተማን መቀየር እንደሚቻል ሲሆን፣ አሁን ላይ ይህ ተሞክሮ ከ75 በላይ ወደሚሆኑ የሀገራችን ከተሞች በመስፋፋት ላይ ይገኛል።
✅ዲጂታላይዜሽን እና የሕግ ማስከበር እርምጃዎች
መንግሥት ሌብነትን በዘላቂነት ለመከላከል የሰው ንክኪን የሚቀንሱ ዲጂታል አሠራሮች ወሳኝ መሆናቸውን በማመን ዘርፈ ብዙ ሥራዎችን እያከናወነ ነው። የኤሌክትሮኒክስ ግዢ ሥርዓት (e-GP) በሁሉም የፌዴራል እና የክልል መሥሪያ ቤቶች በመተግበሩ፣ የጨረታ ምዝበራን እያስቀረ ይገኛል።
በተጨማሪም ፋይዳ ዲጂታል ብሔራዊ መታወቂያ የሐሰተኛ ሠራተኞች ስምን (Ghost workers) ከደመወዝ መክፈያ ሰነድ ላይ በማጽዳት፣ እንዲሁም የሀብት ምዝገባ ሥርዓቱ (e-registration) ምንጩ ያልታወቀ ሀብትን በማጋለጥ በኩል ትልቅ መዋቅራዊ ድርሻ እየተወጡ ነው።
በላይኛው መዋቅር የተገኘውን ስኬት ወደ ታችኛው የአስተዳደር እርከን ለማውረድም ጠንካራ የሕግ ማስከበር እርምጃዎች ተወስደዋል። በሌብነት የተሳተፉትን የማጥራት ሥራ ቀጥሎ በቅርቡ በተደረገ ማጣራት በፋይናንስ እና ባንክ ሰንሰለት ዝርፊያ የተሳተፉ 91 ግለሰቦች በሕግ ቁጥጥር ስር ውለዋል።
ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ የተጠቀሙ በርካታ ባለሙያዎች እና አመራሮች ላይ እርምጃ መወሰድ መጀመሩም የዚሁ አካል ሲሆን፣ የመሬት ምዝበራ ቁጥጥርም በተጠናከረ ሁኔታ ቀጥሎ በርካታ የሕዝብ ሀብት ማዳን እያስቻለ ነው።
የመንግሥትን የልማት ስኬቶች ዘላቂ ለማድረግ እና የሕዝቡን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ፣ የዜጎችን የዕለት ተለት እንግልት የሚፈጥሩ የቀሩ የሌብነት ሰንሰለቶችን የመበጣጠሱ ዘመቻ በተጠናከረ ሁኔታ ይቀጥላል።
በለሚ ታደሰ
#ethiopia #anticorruption #economicgrowth #goodgovernance #ethiopiareform

Comments