26 days ago
የኢትዮጵያውያን ካናዳውያን ቀን በቶሮንቶ በድምቀት ተከበረ
#ethiopia | የኢትዮጵያውያን ካናዳውያን ቀን በካናዳ ቶሮንቶ ከተማ በመስከረም 5 እና 6 ቀን በድምቀት ተከብሯል።
የዝግጅቱን ድባብ የኢትዮ ፊደል የዩቲዩብ ቻናል በአማርኛ አቀላጥፋ በምትናገር በትውልድ ቻይናዊት በሆነች ታዳጊ አማካኝነት በአዝናኝ ሁኔታ ዘግቧል።
በካናዳ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በዝግጅቱ ላይ የሀገር ናፍቆታቸውን፣ የልጅነት ትውስታቸውን እንዲሁም ለሀገራቸው ያላቸውን መልካም ምኞት ሲገልጹ ውለዋል።
በዝግጅቱ የኢትዮጵያ በዓል ድባብ የተላበሰ ድባብ ተፈጥሯል፤ የባህል ልብስ የለበሱ ታዳሚዎች፣ ቡና የሚያፈሉ እንስቶች፣ የባህላዊ ምግብ ዝግጅትና የሙዚቃ ድግስ ዝግጅቱን አድምቀውታል።
የቶሮንቶ ከንቲባ ኦሊቪያ ቻው መስከረም ወር የኢትዮጵያ የቅርስ ወር መሆኑን በማስታወስ፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ካናዳውያን ቡና በጠጡ ቁጥር የቡና መገኛ የሆነችውን ኢትዮጵያን ማሰብ እንዳለባቸው ገልጸዋል።
እንዲህ ያሉ ዝግጅቶች የኢትዮጵያን ባህል፣ ታሪክና ቅርስ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ ከፍተኛ ሚና ይጫወታሉ።
ዝግጅቱን ያዘጋጀው የኢትዮጵያ ማህበር በቶሮንቶ እና አካባቢው ነው።
መልካም አዲስ ዓመት!
ሙሉ ቪዲዮውን በኢትዮ ፊደል የዩቲዩብ ቻናል ለመመልከት፦https://youtu.be/JK7T3QeJB...
#ethiopia #canada #toronto #ethiopiannewyear #ethiopianheritage #ethiofidel #ኢትዮጵያ #ካናዳ #ቶሮንቶ #መልካምአዲስአመት

Comments