15 days ago
"ዘርፉ ሙሉ በሙሉ የህዝብ አመኔታ እንዲያገኝ ነው የምንሰራው"
#ethiopia | በኢትዮጵያ የሪል ስቴት ዘርፍ የህዝብን አመኔታ በመገንባት፣ ለሀገር ውስጥና ለውጭ ኢንቨስተሮች ምቹ የኢንቨስትመንት ሁኔታ ለመፍጠር ያለመ ሁለት ስትራቴጂያዊ የመግባቢያ ሰነዶች ዛሬ በይፋ ተፈራርመዋል።
ስምምነቱን የተፈራረሙት የኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር (EREDA) እና ዶክሳ ቢዝነስ ትሬዲንግ ሲሆኑ፣ ትብብሩ በዘርፉ የተከማቹ የፖሊሲ፣ የፋይናንስ፣ የኢንቨስትመንት እና የትስስር ክፍተቶችን በመቅረፍ ዘርፉን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር እንደሚያግዝ ተገልጿል።
በስምምነቱ መሠረት የሪል ስቴት አልሚዎች፣ የፋይናንስ ተቋማት፣ የፖሊሲ አውጪዎችና የቴክኖሎጂ አቅራቢዎች በአንድ መድረክ በማገናኘት እስካሁን በዘርፉ የታየውን የተቆራረጠ የሥራ አሰራር ለማስቀረት ይሰራል።
እንደ መነሻ ሁለቱ ተቋማት በቅርቡ በሚካሄዱ ዓመታዊ የሪል ስቴት ጉባኤዎችና የኤክስፖ መድረኮች ላይ በጋራ በመሳተፍ የኢንዱስትሪውን ተወዳዳሪነት ለማጠናከር ተስማምተዋል።
ተቋማቱ በጋራ ባወጡት መግለጫ፣ ትብብሩ በግልጽ የኃላፊነት ክፍፍል፣ የሥራ ጊዜ ሰሌዳ እና የሚጠበቁ ውጤቶች ላይ የተመሰረተ በመሆኑ ዘርፉን በሳይንሳዊና በተጠያቂነት መርህ ለመምራት ያግዛል ብለዋል።
በዚሁ ወቅት የኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ ሚካኤል ጆርጅ፣ "ዘርፉ ሙሉ በሙሉ የህዝብ አመኔታ እንዲያገኝ ነው የምንሰራው" ሲሉ ገልጸዋል። እንደ እሳቸው ገለጻ፣ ሙያዊ መመዘኛዎችን ማስከበር፣ ግልጽነትን ማጠናከር እና የባለድርሻ አካላትን ትብብር ማሳደግ የማህበሩ ዋና ትኩረቶች ናቸው።
ዶክሳ ቢዝነስ ትሬዲንግ በበኩሉ ዓለም አቀፍ ኢንቨስተሮችን በመሳብ፣ አዳዲስ የንግድ ትስስሮችን በመፍጠር እና የኢትዮጵያን የሪል ስቴት ዘርፍ ከአህጉራዊ ገበያ ጋር በማስተሳሰር የድርሻውን እንደሚወጣ ተገልጿል።
ተፈራራሚዎቹ እንደገለጹት፣ ይህ ስምምነት በዘርፉ የሚታዩትን የመሠረተ ልማት፣ የፋይናንስ አቅርቦትና የኢንቨስትመንት ችግሮች ለመቅረፍ ወሳኝ መሠረት እንደሚሆን እና የኢትዮጵያን የቤት ልማት ከአህጉራዊና ከዓለም አቀፍ የንግድ ትስስሮች ጋር ለማቀናጀት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ጠቁመዋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
ፎቶ፦ ከበደ መክብብ
#ethiopia #getutemesgen #getunews

የኢትዮጵያን የሪል እስቴት ገበያ ለአለም አቀፍ ኢንቨስተሮች የሚያስተዋውቅ አዲስ ስምምነት ተፈረመ!
#fastmereja I የኢትዮጵያ ሪል እስቴት አልሚዎች ማህበር (EREDA) እና ዶክሳ ቢዝነስ ትሬዲንግ ኃ.የተ.የግ.ማ. በኢትዮጵያ የሪል እስቴት ዘርፍን በሀገር ውስጥ እና በአለም አቀፍ ደረጃ ለማጠናከር የሚያስችሉ ሁለት ስትራቴጂካዊ የመግባቢያ ሰነዶችን በዛሬዉ እለት ተፈራረሙ፡፡
ስምምነቱ የሪል እስቴት ዘርፉን ትብብር ለማሳደግ፣ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ኢንቨስትመንት እድሎችን ለማስፋፋት እንዲሁም የዲያስፖራውን ተሳትፎ ለማሳደግ ያለመ መሆኑ ተገልጻል፡፡
በስምምነቱ መሠረት በሀገር ውስጥ የኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበርን ተቋማዊ አቅም ማጠናከር፣ የአባልነት መስፋፋትን መደገፍ፣ በመንግስት እና በግል ዘርፍ መካከል ያለውን ትብብር ማሳደግ እና የዕውቀት ልውውጥ መድረኮችን በጋራ ማዘጋጀት ዋና ዋና ትኩረቶች ሲሆኑ በዚህም ዶክሳ ቢዝነስ ትሬዲንግ ለተመረጡ መርሃግብሮች የኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር (EREDA) ተመራጭ የኢቨንት አስተባባሪ አጋር ሆኖ እንደሚሰራም ነዉ የተገለፀዉ።
በሌላ በኩል ስምምነቱ የዲያስፖራ ኢንቨስትመንትን ለማበረታታት እና የውጭ ምንዛሬ ገቢን ለማሳደግ ያለመ ሲሆን፣ የመጀመሪያዎቹ አለም አቀፍ የሪል እስቴትና ኢንቨስትመንት ትስስር ፕሮግራሞች በሪያድ (ሳውዲ አረቢያ)፣ በጆሃንስበርግ (ደቡብ አፍሪካ) እና በእስራኤል እንደሚካሄዱ ተጠቅሷል፡፡
ሁለቱ ተቋማት ቀደም ሲል እንደ "Addis Africa Real Estate Expo 2026" ያሉ ትልልቅ መድረኮችን በጋራ ማዘጋጀታቸው የሚታወስ ሲሆን፣ በቀጣይም የሚተገበሩ ፕሮጀክቶች በግልጽነት እና በተጠያቂነት መመሪያዎች የሚመሩ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡
ዶክሳ ቢዝነስ ትሬዲንግ ኃ.የተ.የግ.ማ. በቢዝነስ ልማት፣ በስትራቴጂካዊ ግንኙነት፣ በኢቨንት ማስተባበር፣ በማርኬቲንግ ኮሙኒኬሽን እና በባለድርሻ አካላት ትስስር ላይ የተሰማራ ድርጅት ሲሆን፣ ቢዝነሶችን፣ ባለሀብቶችን፣ መንግስታዊ ተቋማትን እና ማህበረሰቡን የሚያገናኙ ዘላቂና ፈጠራ ያላቸው መድረኮችን በመፍጠር ለኢኮኖሚያዊና ለኢንዱስትሪ ልማት አስተዋፅኦ ያደርጋል::

4 months ago
ጃምቦ ሪል እስቴት በአዲስ-አፍሪካ ሪል እስቴት ኤክስፖ 2026 ይጠብቃችኋል!
የህልም ቤትዎን ባለቤት ለመሆን ወይንም አስተማማኝ የሪል እስቴት ኢንቨስትመንት ለመጀመር እቅድ ካለዎት፣ "ጃምቦ ሪል እስቴት" (Jambo Real Estate) በአዲስ-አፍሪካ ሪል እስቴት ኤክስፖ 2026 ላይ ልዩ አማራጮችን ይዞ ይጠብቅዎታል።
የኤክስፖው መረጃ፦
ቀናት፦ ከዛሬ ሚያዝያ 15 እስከ ሚያዝያ 18/2018 ዓ.ም (April 23-26, 2026)።
ቦታ፦ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሙዚየም (ከመናገሻ ሆቴል ፊት ለፊት)።
ምን ያገኛሉ?፦ ጥራታቸውን የጠበቁ የመኖሪያ ቤት አማራጮች፣ የባለሙያ ምክርና ልዩ የኤክስፖ ቅናሾች።
ጃምቦ ሪል እስቴት በዘርፉ ባለው ጠንካራ ስም የሚታወቅ በመሆኑ፣ ወደ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ሙዚየም ጎራ ብለው የጃምቦን ዳስ በመጎብኘት ለወደፊት ህይወትዎ ጠንካራ መሰረት የሚጥሉበትን እድል እንዲጠቀሙ እመክራለሁ።
📞 ለበለጠ መረጃ፦
📱 0901 66 00 00
🌐 addis-africarealestateexpo2026.com
"የነገውን ኑሮዎን በጃምቦ ሪል እስቴት ዛሬ ያቅዱ!" 🏠🔑
#getu #jamborealestate #ereda #addisafricarealestateexpo2026 #ethiopiarealestate #addisababahousing #investinethiopia #homeexhibition #ጃምቦሪልእስቴት #ቤትግዥ #አዲስአበባ #ሪልእስቴትኤክስፖ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

Sponsored by
Surafel
Comments