2 months ago
ኢትዮጵያ የዓባይ ተፋሰስ ሀብቷን የማልማት ሙሉ ሉዓላዊ መብት እንዳላት ተገለጸ
#ethiopia | ሀገራችን ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ ያላትን የተፈጥሮ ሀብት የመጠቀምና የማልማት ሉዓላዊ መብቷ የተከበረ በመሆኑ ከየትኛውም ወገን ፈቃድ መሻት እንደማያስፈልጋት የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ሀብታሙ ኢተፋ አስታወቁ።
ሚኒስትሩ ከፐልስ ኦፍ አፍሪካ የብዙኃን መገናኛ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንደገለጹት፣ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ዓላማው የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ብቻ ሲሆን፣ የሚመነጨውን የኤሌክትሪክ ኃይል ለጎረቤት ሀገራት በማቅረብ ቀጣናዊ የኃይል ትስስርን የሚያጠናክር ትልቅ ሀብት ነው።
በተጨማሪም ኢትዮጵያ ለታችኞቹ የተፋሰሱ ሀገራት ጥቅም ካላት ከፍተኛ ግምት የተነሳ፣ ከግድቡ በታች ሊለሙ የሚችሉ ከ230 ሺህ ሄክታር በላይ የመስኖ መሬቶችን ከልማት ውጪ በማድረግ የላቀ ኃላፊነቷን ማሳየቷን አብራርተዋል።
በሌላ በኩል ሚኒስትሩ ግድቡን በጋራ ለማስተዳደር የሚቀርቡ ጥያቄዎችን ፈጽመው ውድቅ አድርገዋል።
በራሳቸው የገንዘብና የጉልበት አስተዋጽኦ የገነቡትንና የብሔራዊ ኩራታቸው ማሳያ የሆነውን ይህን ታላቅ ፕሮጀክት፣ ሲቃወሙት የነበሩ አካላት አሁን መጥተው በጋራ እናስተዳድር ማለታቸው ሙሉ በሙሉ ተቀባይነት የሌለውና ሊታሰብ የማይችል ጉዳይ መሆኑን አብራርተዋል።
በመሆኑም የተፋሰሱ ሀገራት የኢትዮጵያን የመልማት መብት ከመጋፋት ይልቅ በመከባበር፣ በውይይትና በጋራ ተጠቃሚነት መبدእ ላይ ተመስርተው መስራት እንደሚገባቸው አሳስበዋል።
#abay #gerd #ethiopia #drhabtamuitefa #waterenergy #eastafrica #energytrade #ethiopianews #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

Comments