9 days ago
#debremarkosuniversity
ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በትምህርት ሚኒስቴር የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የፕሬዝዳንቶች አሰያየም መመሪያ ቁጥር 1146/2018 መሰረት ለፕሬዝዳንት እና ለሦስት ምክትል ፕሬዝዳንት የአመራርነት ሥራ መደቦች ላይ ልምድ ያላቸውን አመልካቾች አወዳድሮ መመደብ ይፈልጋል፡፡
ለውድድር ክፍት የሆኑ የአመራርነት ሥራ መደቦች፦
➻ ፕሬዝዳንት
➻ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት
➻ የምርምርና ማኅበረሰብ ጉድኝት ምክትል ፕሬዝዳንት
➻ የአስተዳደርና ቢዝነስ ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት
ከላይ በተያያዘው ምስል የተቀመጡትን መስፈርቶች የምታሟሉ አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 22 ተከታታይ የስራ ቀናት በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ቴዎድሮስ በካፋ ህንጻ የብቃትና ሰው ሃብት አስተዳደር ስራ አስፈጻሚ ቢሮ ቁ. 106 ወይም በአዲስ አበባ በሚገኘው የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ቀርባችሁ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡
(ዝርዝር ማስታወቂው ከላይ ተያይዟል፡፡)
@tikvahuniversity

13 days ago
#debremarkosuniversity
ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በፎክሎር የ3ኛ ዲግሪ ፕሮግራም ለማስጀመር የስርዓተ ትምህርት ግምገማ አካሂዷል፡፡
ፕሮግራሙ ከጀርመኑ ሃምቡርግ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የሚጀመር መሆኑ ተገልጿል።
በመርሐግብሩ ላይ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና ከጅማ ዩኒቨርሲቲ የተጋበዙ ምሁራን በገምጋሚነት ተሳትፈዋል፡፡
በፎክሎር ዘርፍ ጥናትና ምርምር በማድረግ የአካባቢውን ማኅበረሰብ ተጠቃሚ ለማድረግና ባህሉን ለማበልፀግ የፕሮግራሙ መከፈት የጎላ ፋይዳ እንዳለው ተገልጿል፡፡

Comments