1 day ago
#debreberhanuniversity
በ2019 ዓ.ም ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች እና በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ተከታትላችሁ ወደ 1ኛ ዓመት ያለፋችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 11 እና 12/2019 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
ከጥቅምት 13-15/2019 ዓ.ም ልዩ ስልጠናና ኦሬንቴሽን የሚሰጥ ሲሆን፣ ጥቅምት 16/2019 ዓ.ም ትምህርት ይጀመራል ተብሏል፡፡
የ2018 ሪሚዲያል ትምህርት በዩኒቨርሲቲው ተከታትላችሁ ያለፋችሁ ተማሪዎች ምዝገባ የሚካሔደው ትምህርቱን ስትከታተሉ በነበረበት ካምፓስ እንደሆነ ተገልጿል።
ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦
● የ8ኛ ክፍል ሚኒስትሪ ውጤት ዋናውና ኮፒው፣
● የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
● ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
● አራት 3x4 መጠን የሆኑ ፎቶግራፎች፣
● አንሶላ፣ የለሊት ልብስ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ልብስ።
@tikvahuniversity

8 months ago
🏆 የዩኒቨርሲቲዎች ስፖርት ፌስቲቫል በጅማ ዩኒቨርሲቲ አጠቃላይ አሸናፊነት በድምቀት ተጠናቀቀ!
⚽️🏃🏽
#ethiopia | የትንሿ ኢትዮጵያ ምሳሌ የሆነው መድረክ በሰላም ፍፃሜውን አግኝቷል
ለተከታታይ 15 ቀናት በጅማ ዩኒቨርሲቲ አስተናጋጅነት ሲካሄድ የቆየውና ከ47 ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ ከ500 በላይ ተማሪዎች የተሳተፉበት የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች ስፖርት ፌስቲቫል ዛሬ ተጠናቋል።
የውድድሩ አበይት ውጤቶች:
🏆 አጠቃላይ አሸናፊ: አስተናጋጁ ጅማ ዩኒቨርሲቲ የውድድሩ አጠቃላይ አሸናፊ በመሆን የዋንጫ ሽልማት ተበርክቶለታል።
⚽️ የእግር ኳስ ፍፃሜ (ወንዶች):
የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርስቲ ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲን በመለያ ምት በማሸነፍ ሻምፒዮን ሆኗል።
⚽️ የእግር ኳስ ፍፃሜ (ሴቶች):
ደብረብርሃን ዩኒቨርስቲ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲን በመለያ ምት በመርታት የዋንጫው ባለቤት ሆኗል።
በመዝጊያው ላይ የተገኙት የትምህርት ሚኒስቴር ዴኤታ አቶ ኮራ ጡሹኔ እና የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጀማል አባፊጣ፤ ውድድሩ ኢትዮጵያዊ አንድነት፣ አብሮነት እና ወንድማማችነት ጎልቶ የታየበት መሆኑን ገልጸዋል።
ለአሸናፊዎች እና ለተሳታፊዎች በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ!
#jimmauniversity #universitysportfestival #ethiopia #defenseuniversity #debreberhanuniversity #sports #unity #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

Comments