13 days ago
ከ600 በላይ ተማሪዎችን የረዳው “አንድ እሽግ ለአንድ ተማሪ” የበጎነት መርሃ ግብር
#ethiopia | በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ዳውሮ ዞን ታርጫ ከተማ፣ ከ600 በላይ ተማሪዎችን የሚደግፍ የትምህርት ቁሳቁስ ተሰብስቧል።
የትምህርት ቁሳቁሶቹ የተሰበሰቡት “አንድ እሽግ ለአንድ ተማሪ” በሚል መርህ በNew Dawro Foundation በ2019 ዓ.ም. የተካሄደው የበጎነት መርሃ ግብር አካል ነው።
የመርሃ ግብሩ ማጠናቀቂያና የNew Dawro Foundation 5ኛ ዓመት ክብረ በዓል በታርጫ ከተማ ተካሂዷል።
በዝግጅቱ ላይ የዳውሮ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ እጩ ዶ/ር ታማኝ እንደገለጹት፣ የትምህርት ሥራ የሁሉም ባለድርሻ አካላት የጋራ ኃላፊነት ነው። በጎ አድራጎትን በማጠናከርም ማህበረሰቡን የሚጠቅሙ በርካታ ተግባራትን ማሳካት እንደሚቻል ጠቁመዋል።
የተሰበሰቡት የትምህርት ቁሳቁሶች በእጥረት ምክንያት ሕፃናት ከትምህርት ገበታ እንዳይቀሩ የሚያግዙ መሆናቸውን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አባተ ኡቃ ተናግረዋል።
አቶ አባተ እንዳሉት፣ በመርሃ ግብሩ ከ600 በላይ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ በማግኘት ወደ ትምህርት ገበታ እንዲገቡ ማገዝ ተችሏል። በመሆኑም New Dawro Foundationንና በመርሃ ግብሩ የተሳተፉ አካላትን አመስግነዋል።
በተጨማሪም የትምህርት ቁሳቁስ እጥረት ሳቢያ ተማሪዎች ከትምህርት እንዳይቀሩ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ጠይቀዋል።
የNew Dawro Foundation መስራችና ባለቤት አቶ በሀይሉ ማቲዎስ በበኩላቸው፣ ባለፉት አምስት ዓመታት “አንድ እሽግ ለአንድ ተማሪ” በሚል መርሃ ግብር የተለያዩ የትምህርት ቁሳቁሶችን በማሰባሰብ በዳውሮ ዞን ከ2 ሺህ 400 በላይ ተማሪዎችን መደገፍ መቻሉን ገልጸዋል።
በመርሃ ግብሩ በርካታ ግለሰቦች፣ የመንግሥት አካላት፣ ወጣቶችና የሥራ ኃላፊዎች በበጎነት ተሳትፎ ማድረጋቸውን ጠቅሰው፣ ለተሳተፉ ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል።
አቶ በሀይሉ ማቲዎስ ማህበራዊ ሚዲያን ለበጎ ዓላማ በመጠቀም ሕብረተሰቡን የሚጠቅሙ በርካታ ተግባራትን ማከናወን እንደሚቻልም አመልክተዋል።
Foundationኑ በቀጣይ ከትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ባሻገር በንጹሕ የመጠጥ ውሃና በሌሎች የማህበረሰብ ጥቅም መስኮች ላይ በመሥራት ሕብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ ማቀዱንም ገልጸዋል።
“አንድ እሽግ ለአንድ ተማሪ” የበጎነት መርሃ ግብር የትምህርት ቁሳቁስ እጥረት ያለባቸውን ተማሪዎች በመደገፍ በትምህርት ተሳትፎና ውጤታማነት ላይ አስተዋጽኦ ለማድረግ የታለመ መሆኑ ተገልጿል።
በመርሃ ግብሩ የክልልና የዞን የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች፣ የታርጫ ከተማ አስተዳደር አመራሮች፣ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች፣ ወላጆችና ተማሪዎች ተገኝተዋል።
#newdawuromedia

1 month ago
‘ቶኪ-በዓ’፦ የዳውሮ ብሔረሰብ የረቀቀ የዘመን አቆጣጠር ዕውቀት የሚገለጥበት የዘመን መለወጫ በዓል!
*********************
ሀገራችን ኢትዮጵያን በዓለም መድረክ ልዩ ከሚያደርጓት ጸጋዎች መካከል አንዱ የብዝኃ ማንነቶች ማማ መሆኗ ነው።
በዚህች ውብ ሀገር ውስጥ የሚገኙ ብሔር ብሔረሰቦች የየራሳቸውን የማንነት መገለጫ የሆኑ ባህላዊ እና ታሪካዊ እሴቶችን ጠብቀው ከትውልድ ወደ ትውልድ እያሸጋገሩ ይገኛሉ።
ከእነዚህ ደማቅ ሀገራዊ ጌጦች መካከል አንዱ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የሚገኘው ነባሩ የዳውሮ ብሔረሰብ፣ በየዓመቱ በወርኃ ነሐሴ መጨረሻ በድምቀት የሚያከብረው የዘመን መለወጫ ‘ቶኪ-በዓ’ በዓል ነው።
‘ቶኪ-በዓ’ የቀን መቁጠሪያ ሽግግር ብቻ አይደለም። የቀደሙት የዳውሮ አባቶች የነበራቸውን ጥንታዊ የከዋክብት እና የጨረቃ ዑደት መነሻ ያደረገ የረቀቀ የዘመን አቆጣጠር ዕውቀት፣ ከባህላዊ ዕሴቶች እና ትውፊታዊ ክዋኔዎች ጋር አጣጥሞ የያዘ ድንቅ ሥርዓት ነው።
የዳውሮ ብሔረሰብ ይህንን በዓል ሲያከብር ዘመንን ለትውልድ ቀምሮ ከማሻገር ባለፈ፣ የጥንታዊ ሥልጣኔ መፍለቂያነቱን ለዓለም በኩራት የሚያሳይበት ታላቅ ቀኑ ነው።
ይኸውም፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቀውን እና በድንቅ የሕንፃ ጥበብ የታነጸውን የድንጋይ ክምር መከላከያ ግንብ (ሃላላ ኬላን) በገነቡት በንጉሥ ሃላላ (ካዎ ሃላላ) የሚመራው ታሪካዊ ማንነታቸው ሕያው ሆኖ የሚታሰብበት በመሆኑ ነው።
ይህ ታላቅ ቀን በዳውሮ ብሔረሰብ ዘንድ የምስጋና እና የተስፋ ዓርማ ነው። በዓሉ አሮጌውን ዓመት በሰላም፣ በጤና እና በደስታ ላሻገረው ፈጣሪ በጋራ ምስጋና የሚቀርብበት፣ መጪው አዲስ ዓመት ደግሞ የሰላም፣ የፍቅር፣ የምርታማነት እና የብልጽግና ዘመን እንዲሆን የጋራ ጸሎት እና መልካም ምኞት የሚሰማበት መንፈሳዊ ከፍታ ያለው ሥርዓት ነው።
ከዚህም ባሻገር ‘ቶኪ-በዓ’ ያለው ለሌለው የሚያካፍልበት፣ የተቸገሩ እና አቅም ያነሳቸው ወገኖች የሚጠየቁበት የጥጋብ በዓል ነው። የዳውሮ ሕዝብ መለያ የሆነው ድንቅ የእንግዳ ተቀባይነት ባህል እና የአብሮነት እሴት ፍንትው ብሎ የሚታየውም ማንም ሰው ሳይራብ ማዕድ በሚጋራበት በዚህ ታላቅ ዕለት ነው።
የ‘ቶኪ-በዓ’ ሌላው አንጸባራቂ ገጽታ ማኅበራዊ መስተጋብርን የሚያስጠብቅበት የራሱ የሆነ ጥልቅ የዳኝነት ሥርዓት መኖሩ ነው። በበዓሉ ወቅት ባህላዊ ዳኝነት እና የግጭት አፈታት ሥርዓት ይካሄዳል። የተጣላ ይታረቃል፣ ቂም ይረሳል፣ በበደል የተራራቀ ይቅርታ ተባብሎ በአዲስ መንፈስ ይቃቀፋል። ይህ ተግባራዊ የእርቀ-ሰላም ሥርዓት በዓሉን የሰላም፣ የእርቅ እና የአንድነት ሕያው መገለጫ ያደርገዋል።
በ‘ቶኪ-በዓ’ ውስጥ የታመቁት እነዚህ የወንድማማችነት፣ የእህትማማችነት እና የአብሮነት እሴቶች ለዳውሮ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን፣ ለኢትዮጵያ የሰላም ባህል ግንባታ እና ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መጎልበት ያላቸው ሚና እጅግ የጎላ ነው።
የሕዝቦችን አንድነት በሚገነባ መልኩ በጋራ የሚከበረው ይህ በዓል፣ ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተሸጋገረ ይበልጥ የሀገራችን ውበት እና ጥንካሬ ሆኖ እንዲቀጥል ኃላፊነታችንን ልንወጣ ይገባል።
በዓሉ በዛሬው ዕለት በተለያዩ ባህላዊ ክዋኔዎች በታላቅ ድምቀት እየከበረ ይገኛል። እንኳን ለዳውሮ ሕዝብ የዘመን መለወጫ ‘ቶኪ-በዓ’ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! አደረሰን!
በዮናስ በድሉ
#ethiopia #ebc #toki_ba’a #dawro #newyear

Comments