4 months ago
ሀሪ ማጓየር በኦልድትራፎርድ ለመቆየት ተስማማ፤ ውሉንም እስከ 2027 አራዘመ!
#ethiopia | የማንችስተር ዩናይትዱ ተከላካይ ሀሪ ማጓየር በክለቡ ያለውን ቆይታ የሚያራዝም አዲስ ስምምነት በይፋ ተፈራርሟል። እንደ ክለቡ መግለጫ ከሆነ፣ እንግሊዛዊው የመሀል ተከላካይ እስከ 2027 ድረስ በኦልድትራፎርድ የሚያቆየውን ውል ነው ያደሰው።
ማጓየር በክለቡ ያለውን ውል ለተጨማሪ አንድ ዓመት ያራዘመ ሲሆን፣ ይህም እስከ 2027 በክለቡ እንዲቆይ ያደርገዋል።
ክለቡ እንደ አስፈላጊነቱ የሀሪ ማጓየርን ውል ለተጨማሪ አንድ ዓመት (እስከ 2028) ማራዘም የሚችልበት አንቀጽ በስምምነቱ ውስጥ ተካቷል።
"ማንችስተር ዩናይትድን ወክሎ መጫወት ትልቅ ክብር ነው። በዚህ አስደናቂ ክለብ ቢያንስ ለ8 ዓመታት ለመቆየት በመስማማቴ እና በደጋፊዎቻችን ፊት መጫወቴን በመቀጠሌ በጣም ደስተኛ ነኝ" ሲል ስሜቱን ገልጿል።
የክለቡ የእግር ኳስ ዳይሬክተር ጄሰን ዊልኮክስ ስለ ማጓየር ሲናገሩ፦
> "ሀሪ ለማንችስተር ዩናይትድ ለመጫወት የሚያስፈልገውን ጠንካራ ስነ-ልቦና እና ፅናት በተግባር የሚያሳይ ተጫዋች ነው" ብለዋል።
>
በ2019 በ80 ሚሊየን ፓውንድ የተከላካዮችን የዝውውር ክብረ-ወሰን በመስበር ከሌስተር ሲቲ ነበር የተቀላቀለው።
እስካሁን ለቀያይ ሰይጣኖቹ 266 ጨዋታዎችን አድርጓል።
ከክለቡ ጋር የሊግ ካፕ (Carabao Cup) እና የኤፍ ኤ ካፕ (FA Cup) ዋንጫዎችን ማሳካት ችሏል።
ክለቡን ከተቀላቀለ በ5 ወራት ጊዜ ውስጥ በኦሌ ጉናር ሶልሻ አምበል ሆኖ መሾሙ ይታወሳል።
የ33 ዓመቱ ተከላካይ አሁን በፈረመው አዲስ ውል መሰረት፣ ልምዱን ለክለቡ ወጣት ተከላካዮች በማካፈል እና የተከላካይ ክፍሉን በማጠናከር ረገድ ትልቅ ሚና ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #harrymaguire #mufc #manchesterunited #contractextension #oldtrafford #footballnews #premierleague

Comments