1 month ago
ከጠብመንጃ ወደ ጠረጴዛ ውይይት ሀገራዊ ምክክር እና የመደመር መንግሥት የመግባባት ዴሞክራሲ ታሪካዊ ድል
***************************
ሀገር የሚገነባው እንዲሁም ዘላቂ ሰላም እና የተረጋጋ ዴሞክራሲ የሚረጋገጠው ዜጎች ያለስጋት በነጻነት ተወያይተው፣ ልዩነቶቻቸውን አክብረው በሚፈጥሩት ጠንካራ የጋራ መግባባት ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ሂደት ስኬት የመደመር መንግሥት አንግቦት የተነሳውን የመግባባት ዴሞክራሲ ፍልስፍና በተግባር ያረጋገጠ ታሪካዊ ክስተት ነው።
የመደመር አስተሳሰብ አንዱ እና ዋነኛው ምሰሶ ሀገራዊ ጉዳዮችን በኃይል ወይም በጥቂት ወገኖች ድርድር ሳይሆን በጋራ መግባባት እና በሰለጠነ ውይይት መፍታት በመሆኑ፣ ይህ መርህ በሀገራዊ ምክክሩ ሂደት እውን ሆኖ ታይቷል።
የሀገር አስተማማኝ መሠረት የሚጣለው በዜጎች ንቁ ተሳትፎ በመሆኑ፣ ዜጎች ስለ ሀገራቸው ያለፈ ታሪክ፣ የአሁኑ ፈተና እና የመጪው ጊዜ ራዕይ በነጻነት የመምከር እና የመወያየት መብታቸው ሲጠበቅ የባለቤትነት ስሜት የሚፈጠር ሲሆን፣ ሕጎችና የወደፊት አቅጣጫዎች በሕዝብ የጋራ ውሳኔ ሲቃኙ የሁሉም ብሔር፣ ሃይማኖትና ጾታ ድምፅ በእኩልነት ተሰምቶ የመገለል ስሜት ይወገዳል።
ኃይል የሚያስገኘው ጊዜያዊ ስምምነት ዘላቂ ሰላም ማምጣት ስለማይችል፣ በውይይት የሚገነባ መግባባት ቂምና ቁስሎችን በመካስ፣ በሕዝቦች መካከል መተማመንን በመፍጠር ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ የመፍታት ባህልን ያዳብራል።
ኢትዮጵያ ለዘመናት የዘለቁ ስልታዊ እና መዋቅራዊ ልዩነቶች፣ የፖለቲካ አለመግባባቶች እንዲሁም የታሪክ ትርክት ክፍተቶች ያሏት ሀገር እንደመሆኗ፣ የተቋቋመው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች የተጣጣጡ ድምፆችና ሐሳቦች የሚደመጡበት ሰፊ ሜዳ በመፍጠር በሕገ-መንግሥታዊ ማሻሻያዎች፣ በሀገራዊ ምልክቶች፣ በፌዴራሊዝም ቅርጽ እና በታሪክ ትርክቶች ላይ የጋራ መግባባት ለመፍጠር መንገድ ከፍቷል።
ኮሚሽኑ ባለፉት ዓመታት በየደረጃው ባከናወናቸው መድረኮች እንዲሁም በመጨረሻው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ከየአካባቢው ከተወከሉ 4 ሺህ ተመካካሪዎች ጋር ያካሄደው ውይይት፣ ከጠመንጃ ይልቅ ውይይት፣ ከውግዘት ይልቅ ማዳመጥ የሚነግስበትን አዲስ የፖለቲካ ባህል በማስረጽ ረገድ ታይቶም ሆነ ተሰምቶ የማይታወቅ እጅግ ግዙፍ ሀገራዊ ድል አስመዝግቧል።
ሀገርን ማቅናት እና አስተማማኝ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መገንባት በአንድ ጀምበር የሚፈጸም ባይሆንም፣ ትክክለኛው መንገድ ግን በዜጎች ነፃ ውይይት የሚገኝ የጋራ መግባባት እንደሆነ የመደመር አስተሳሰብ ያስተምራል።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ያስመዘገበው ውጤት የመደመር መንግሥት የተከተለው የመግባባት ዴሞክራሲ ፍልስፍና ፍሬ ማፍራቱን በተግባር ያረጋገጠ ሲሆን፣ የፖለቲካ ኃይሎች፣ የሲቪክ ማኅበራት እና ሙሉው ሕዝብ ሂደቱን በጥቅል ባለቤትነት ተረክበው ለተግባራዊነቱ ሲቆሙ በውይይት የተገነባች፣ ሰላምና ፍትሕ የሰፈነባት ጽኑ ኢትዮጵያ እውን መሆኗ አይቀሬ ነው።
በአድማሱ አራጋው
#ebc #nationaldialogue #medemerthought #consensusdemocracy #ethiopianunity #peaceanddemocracy

2 months ago
የሀገራዊ ምክክሩ ወሳኝ ምዕራፍ፣ የዘላቂ ሀገራዊ መግባባት ፋይዳ
#nationaldialogue #consensusdemocracy #ethiopianunity #peacefulresolution
" target="_blank" class="inline-link">https://new-en.yenevibe.co...

Comments