7 months ago
የፍቅር ድልድይ ከቤልጂየም ወደ ድሬዳዋ! 🇧🇪❤️🇪🇹
#ethiopia | የኢትዮ-ቤልጂየም ማኅበር ለህጻናት ማቆያ ማዕከል የ500 ሺህ ብር የገና ስጦታ አበረከተ
የኢትዮ-ቤልጂየም ማኅበር (Ethio-Belgium Association) ለድሬዳዋ አስተዳደር የሴቶች፣ ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የህጻናት ማቆያ ማዕከል ግምታቸው 500 ሺህ ብር የሚያወጣ የገና በዓል ስጦታ አበርክቷል።
ስጦታውን የተረከቡት የድሬዳዋ ከተማ ከንቲባ ከድር ጁሃር፤ "የሚሰጡ እጆች ሁልጊዜም የተባረኩ ናቸው" በማለት፣ ድጋፉ በገና ዋዜማ መከናወኑ ወላጅና አሳዳጊ ለሌላቸው ህጻናት በዓሉን ልዩ እንደሚያደርግላቸው ገልጸዋል።
🎁 የተበረከቱት ቁሳቁሶች፦
✅ የልብስ ማጠቢያ ማሽን፣
✅ የኤሌክትሪክ ምድጃ (ኦቭን)፣
✅ የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች፣
✅ ዳይፐር እና አልባሳት ናቸው።
"ሁለት አገሮችን በልብ የሚያገናኝ ድልድይ"
የኢትዮ-ቤልጂየም ማኀበር መሥራችና ዳይሬክተር፣ የድሬዳዋ ተወላጅ የሆነችው ሞዴል ፈቲያ መሐመድ፤ ስለ ድጋፉ ፋይዳ እና ስለ ከተማዋ ጥልቅ መልዕክት አስተላልፋለች፡-
"ዛሬ ይህን ድጋፍ በድሬዳዋ ከተማ ማቅረባችን ለእኛ በጣም ትልቅ ትርጉም አለው። ድሬዳዋ የልዩነት እና የአብሮነት ከተማ ናት፤ ዛሬ ደግሞ የፍቅር እና የተስፋ መድረክ ሆናለች። ...
... ይህ ድጋፍ ለልጆቻችን ብቻ ሳይሆን፣ በኢትዮጵያ እና በቤልጂየም መካከል ያለውን የሰውነት፣ የፍቅር እና የእርስ በእርስ መተሳሰብ የሚያጠናክር ድልድይ ነው። ማኅበራችን ሁለት አገሮችን በርቀት ሳይሆን በልብ የሚያገናኝ ድርጅት ነው። ዛሬ በድሬዳዋ ያየነው ፍቅር፣ በቤልጂየም የተጀመረ ነው፤ ይህም ፍቅር ድንበር እንደሌለው ያሳያል።"
ሞዴል ፈቲያ አያይዛም "ልብስ ማልበስ" ስላለው ትልቅ ትርጉም እንዲህ ብላለች፡-
"ልጅን ልብስ ማልበስ ማለት ቀላል ነገር ሊመስል ይችላል፤ ነገር ግን ለእነርሱ የሚተላለፈው መልዕክት ታላቅ ነው። 'ታይተሃል፣ ተወዳጅ ነህ፣ ክብር አለህ!' የሚል ትርጉም ይይዛል። ልጆች ሲለብሱ ልባቸውም ይሞላል፤ ዓይናቸውም ተስፋ ያበራል። እኛ ልጆቻችንን ስንንከባከብ፣ የነገ ኢትዮጵያን እየተንከባከብን ነው።"
መልካም የገና በዓል! 🎄
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#diredawa #charity #ethiobelgiumassociation #lovehasnoborders #bridgeoflove #genna #ethiopia #hope

Comments