2 months ago
ዩኒቨርሲቲው በራስ አቅም የምርት ሥራዎችን ማምረት ጀመረ
07/ 08 /2018 ዓም
****
የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ትምህርትን ከተግባር ጋር በማዋሃድ የተማሪዎችን ክህሎት ለማሳደግ እና የተቋሙን የራስ አቅም ለማጠናከር የሚያስችሉ የተለያዩ የምርቶችን በራሱ አቅም ማምረት ጀምሯል።
ዩኒቨርሲቲው በባለሙያ መምህራንና ተማሪዎች አቅም ተጠናክሮ፣ ጥራት ያለው የፈሳሽ ሳሙና፣ የተቀነባበሩ የእንስሳት መኖ ምርቶች፣ የግንባታ ብሎኬት እና የፋይበር ግላስ ምርቶችን በተግባር በማምረት ለተጠቃሚዎች በማከፋፈል ላይ ይገኛል።
እነዚህ የምርት ሂደቶች ተማሪዎች የተግባር ልምምድ እንዲያደርጉ ፣ የስራ ክህሎታቸውን እና ከትምህርት ያገኙትን እውቀታቸውን እንዲያሳድጉ ያስቻሉ ናቸው። በተጨማሪም ኢኮኖሚያዊ ጥቅምን ለማሻሻል ትልቅ ሚና ይጫወታሉ።
የሚመረቱት የፈሳሽ ሳሙናዎች የተፈለጉ የጥራት መመዘኛ መስፈርቶችን ያሟሉ ናቸው። የመኖ ማቀነባበሪያ ምርቶቹም ለግብርናው ዘርፍ ምርታማነት ተግባራዊ እና ጥራት ያላቸው መሆናቸው ተገልጿል። የግንባታ ብሎኬቶችና የፋይበር ግላስ ምርቶችም በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ተመርተው ለግንባታና ለቴክኖሎጂ አገልግሎቶች ዝግጁ ናቸው።
“ከትምህርት ወደ ምርት፣ ከሀሳብ ወደ አቅም” ዩኒቨርሲቲው ከምንጊዜውም በላይ ስንቅ አድርጎ እየተከተለው ያለ መርህ ነው።
የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ተቋማት ለሀገር እድገት በተግባር በርካታ አስተዋፅኦችን ሊያበረክቱ እንደሚችሉ የሚያሳይ ትልቅ ምሳሌ ነው። #ethiopian Defence University #bishoftu #benaol_event_and_promotion
#cleanpower #ጥራት #የአገር_ምርት #benaolevent
Comments