3 months ago
የኢትዮጵያ አየር መንገድ፦ የሀገረ መንግሥት ግንባታ ምሰሶና የአፍሪካ አቪየሽን የልህቀት ማማ
*****************
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሀገር ግንባታ ሂደት ካለው ጉልህ ሚና ባለፈ፣ ብሔራዊ ኩራትን በመፍጠር ረገድ የአፍሪካ አቪየሽን የልህቀት ተምሳሌት መሆኑን የመንግሥት ከፍተኛ አመራሮች ገለጹ።
አየር መንገዱ የተመሠረተበትን 80ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ፣ ከደንበኞችና ከአጋሮች ጋር የልምድ ልውውጥ የሚደረግበት "የደንበኞች ተሞክሮ መድረክ" እየተካሄደ ይገኛል።
በዚሁ መርሐ ግብር ላይ የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ፣ የፕላንና ልማት ሚኒስትሯ ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር)፣ የገንዘብ ሚኒስትር ድኤታው ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች ተገኝተዋል።
በዕለቱ በተካሄደው የፓናል ውይይት ላይ የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ እንደገለጹት፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የላቀ ውጤት ያስመዘገበና ለረጅም ዓመታት ስኬቱን ማስቀጠል የቻለ ግዙፍ የመንግሥት የንግድ ተቋም ነው።
አየር መንገዱ ለኢትዮጵያ ሀገረ መንግሥት ግንባታ እንዲሁም ለፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝም አክለው ገልጸዋል።
በተለይም ኢትዮጵያ ከሌሎች ሀገራት ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትና የሀገር ውስጥ ትስስርን ለማጠናከር ተቋሙ የማይተካ ሚና እንዳለው አስገንዝበዋል።
የፕላንና ልማት ሚኒስትሯ ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ አየር መንገዱ የሀገር ኩራትና ሁሉም ዜጋ "የእኔ" የሚለው የጋራ ማንነት መገለጫ የሆነ ብሔራዊ ድርጅት መሆኑን ገልጸዋል።
ተቋሙ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለመላው አፍሪካ "የመቻል" እና የልህቀት ማሳያ መሆኑን ጠቅሰው፤ ይህም የሀገራችንን የማድረግ አቅም ለዓለም የሚያሳይ መሆኑን ተናግረዋል።
አየር መንገዱ ለአገልግሎት ዘርፍ ወጪ ንግድ (Export) ካለው ከፍተኛ ድርሻ በተጨማሪ፣ ለንግድ ሥርዓቱ መሳለጥና ለሥራ ዕድል ፈጠራ ትልቅ አቅም እየሆነ እንደሚገኝም አስረድተዋል።
የገንዘብ ሚኒስትር ድኤታው ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ አየር መንገዱ ግዙፍ የሎጅስቲክስ መሠረተ ልማት አቅም መገንባቱን ገልጸው፤ ለወጪ ንግድና ለዲፕሎማሲ ስኬት ቁልፍ ሚና ያለው ተቋም መሆኑን እንደጠቆሙ የዘገበው ኢዜአ ነው።
#ethiopianairlines #flyethiopian #80yearsofexcellence #timelesslegacy #aviationhistory

Comments