19 days ago
ቴክኖ ኢትዮጵያ ለተለያዩ ዘርፍ የጥበብ ባለሙያዎች አዲስ የሥራ ዕድል ይፋ አደረገ
#ethiopia | ቴክኖ ኢትዮጵያ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎችን የሚያሳትፍ አዲስ መርሐ ግብር ይዞ ቀርቧል።
ተቋሙ ባለፈው ዓመት ከቦርድ ሴልፎን ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር በካሞን ስልክ ሞዴል የተነሱ የፎቶግራፍ ምስሎችን በመላው ኢትዮጵያ ሲያሳይ መቆየቱ ይታወሳል።
ዘንድሮ ደግሞ አዲስ ለገበያ ባቀረበው የካሞን 50 ሲሪየስ ስልክ አማካኝነት ይበልጥ ደመቅ ያለ የፎቶ ኤግዚቢሽን ለማዘጋጀት አቅዷል።
ለዚህ ዝግጅት ስኬትም ቴክኖ ሞባይል ከተለያዩ የጥበብ ዘርፎች ጋር በጋራ ለመሥራት ጥሪ አቅርቧል።
በዚህ የሥራ ዕድል ላይ መሳተፍ የሚፈልጉ የቅርጻ ቅርጽ ባለሙያዎች፣ የዲጂታል እና የሞሽን ግራፊክስ ባለሙያዎች፣ የጨርቃ ጨርቅና ፋሽን ዲዛይነሮች፣ የግድግዳ ላይ ስዕል ሠዓሊያን፣ ባህላዊ የዕደ ጥበብ ባለሙያዎች እንዲሁም በተለያዩ የፈጠራ ዘርፎች የተሰማሩ ግለሰቦችም ሆኑ ቡድኖች መመዝገብ ይችላሉ።
ፍላጎቱ ያላችሁ ባለሙያዎች ከታች የተያያዘውን የቅጽ መሞያ ማስፈንጠሪያ በመጠቀም ዝርዝር መረጃ ማግኘትና ማመልከት የምትችሉ መሆኑን ድርጅቱ ገልጿል።
የማመልከቻ ሊንክ፦
https://docs.google.com/fo...
#tecnoethiopia #artandtechnology #creativeopportunity #photographyexhibition #artinethiopia #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

Comments