1 month ago
የአርዳይታ እንግዶች
* ከበርካታ አሥርታት በኋላ የሚገናኙበት ታላቅ መርሃ ግብርና የበጎ አድራጎት ማህበር ምስረታ ይፋ ሆነ
#ethiopia | በምዕራብ አርሲ ዞን የሚገኙ የአርዳይታ ተወላጆች ከአሥር፣ ከሃያ እና ከሠላሳ ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚገናኙበትን ልዩ መርሃ ግብር እና የአርዳይታና አካባቢዋ በጎ አድራጎት ማህበር የተሰኘ ሀገር በቀል ድርጅት መመሥረታቸውን ይፋ አድርገዋል።
ይህ በአካባቢው ተወላጆች የተቋቋመው ማህበር የማህበረሰቡን አቅም በትምህርት፣ በጤና፣ በአካባቢ ጥበቃ እና በኢኮኖሚ ግንባታ የማሳደግ ዓላማ ያለው ሲሆን፣ ለችግር ተጋላጭ የሆኑ ህፃናትን እና አረጋውያንን የመንከባከብ ስራዎችንም ያከናውናል።
ማህበሩ በአርዳይታ የተወለዱ፣ ያደጉ፣ የተማሩና የኖሩ ከአጠባበቅ በላይ ኢትዮጵያውያንን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን ያቀፈ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ከ900 በላይ አባላት አሉት።
ድርጅቱ በቅርቡ ህጋዊ እውቅና ያገኘ ሲሆን፣ ፈቃድ የማውጣት ሂደቱ እስከሚጠናቀቅ ድረስም የህክምና እርዳታ እና የትምህርት ቁሳቁሶች ድጋፍን ጨምሮ በርካታ የበጎ አድራጎት ስራዎችን ሲያከናውን ቆይቷል።
ማህበሩ የተቋቋመው ለአካባቢው ህዝብ ቢሆንም ሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎችንም ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ተገልጿል።
መጪው ቅዳሜ ነሐሴ 23 እና እሁድ ነሐሴ 24 ቀን በተዘጋጀው ታላቅ የምስረታ መርሃ ግብር ላይ የወረዳ አመራሮች፣ የኮሌጅ ዲን፣ የምርጥ ዘር እርሻ ልማት ኃላፊ፣ አባ ገዳዎች፣ ሀደ ሲንቄዎች፣ እንዲሁም ከአገር ውስጥ እና ከውጭ አገራት የተወጣጡ የአርዳይታ ተወላጆች ይገኛሉ።
በእነዚህ ዕለታት የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ፣ የሩጫ ውድድር፣ እንዲሁም የመምህራን እና የተማሪዎች የእውቅና አሰጣጥ ሥነ ሥርዓቶች ይካሄዳሉ።
በ1970ዎቹ መጀመሪያ አካባቢ የተቆረቆረችው አርዳይታ፣ በአሁኑ ወቅት በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ስር በሚተዳደረው አርዳይታ ግብርና ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ እና በኢትዮጵያ ግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ስር በሚገኘው የምርጥ ዘር ድርጅት የሚታወቅ ቀጣና ነው።
ፈትያ ሁሴን
#ardaita #ardaitacollege #westarsi #oromia #charity #ethiopia #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

Comments