26 days ago
ኢትዮጵያ በህክምና መሳሪያዎች ቁጥጥር ከአፍሪካ የመጀመሪያዋ ለመሆን እየተጋች ነው
#ethiopia | የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን በሀገር ውስጥ የሚመረቱና ከውጭ የሚገቡ የህክምና መሳሪያዎችን ጥራትና ደህንነት ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ዘመናዊ አሰራሮችን ተግባራዊ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ አስታወቀ።
በባለስልጣኑ የህክምና መሳሪያ ጥራት ምርመራ ላብራቶሪ መሪ ስራ አስፈጻሚ የሆኑት አቶ ቃልአብ ተስፋዬ ወርቁ እንደገለጹት፣ ላብራቶሪው በአዲስ መዋቅር ከተደራጀ በኋላ በህክምና መሳሪያዎች ጥራት ምርመራ፣ በምዝገባ፣ ከገበያ በኋላ በሚደረግ የጥራት ክትትልና ጥርጣሬ የወደቀባቸውን ምርቶች በመመርመር ረገድ ሰፊ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል።
ላብራቶሪው በአሁኑ ወቅት ኮንዶም፣ (ሄፐታይተስ) ቢ እና ሲ እንዲሁም የወባ መመርመሪያዎችን ጨምሮ በርካታ የህክምና መሳሪያዎችን በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ባገኘበት አግባብ እየመረመረ መሆኑን አቶ ቃልአብ አብራርተዋል።
ከእነዚህም በተጨማሪ የወንድና የሴት ኮንዶሞች፣ የቀዶ ህክምናና የላብራቶሪ ጓንቶች፣ መርፌ፣ የሴቶች የንጽህና መጠበቂያዎችና ማስኮችን ጥራት በተደራጀ መልኩ የመመርመር አቅም መገንባቱን ገልጸዋል። ይህ የጥራት ምርመራ አሰራር በዘፈቀደ የሚከናወን ሳይሆን፣ በመንግስት ላይ የሚባክን ወጪን ለመቀነስና የህብረተሰቡን ጤና ይበልጥ ለመጠበቅ ሲባል በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጠና የችግር ዳሰሳ ጥናትን መሰረት ያደረገ "በስጋት ላይ የተመሰረተ አቀራረብ" የተከተለ መሆኑን አስረድተዋል።
የናሙና አወሳሰድ ሂደቱን በተመለከተ አቶ ቃልአብ እንደገለጹት፣ የህክምና መሳሪያዎች ወደ ሀገር ውስጥ በሚገቡባቸው የድንበር ኬላዎችና ወደቦች ላይ ዓለም አቀፍ የአይሶ (ISO 2859-1) ስታንዳርድን የተከተለ ጥብቅ የናሙና አሰባሰብ ይከናወናል።
ከዚህም በተጨማሪ ምርቶች አንዴ ወደ ሀገር ውስጥ ከገቡ በኋላ በትራንስፖርትና በክምችት ወቅት ሊያጋጥሙ የሚችሉ መበላሸቶችን ለመቆጣጠር ሲባል፣ በዓመት ሁለት ጊዜ ከገበያ ላይ ራንደምሊ ናሙናዎች ይሰበሰባሉ።
ይህ የገበያ ቅኝት ጥናትም እጅግ ሞቃታማ የሆኑትን እንደ አፋርና ጋምቤላ ያሉ አካባቢዎችን እንዲሁም ቀዝቃዛ የሚባሉትን እንደ ደብረብርሃን ያሉ አካባቢዎችን በማካተት ምርቶቹ በተለያዩ የአየር ንብረቶች ውስጥ ያላቸውን ጥንካሬ ለማረጋገጥ እንደሚረዳ ጠቁመዋል።
በባለስልጣኑ አቅም የማይሰሩ እንደ እርግዝና መመርመሪያ ዩሪን ስትሪፕ ያሉ ምርቶች ላይ የጥራት ጉድለት ጥርጣሬ ሲፈጠርም በአስቸኳይ ወደ ውጭ ሀገር በመላክ ምርመራ ተደርጎ ፈጣን የእርምት እርምጃ እንደሚወሰድ አብራርተዋል።
የመንግስትን የዜጎች ቻርተር መሰረት በማድረግ የደንበኞችን የአገልግሎት አሰጣጥ ጊዜ ለማሳጠር ሰፊ ማሻሻያ መደረጉን መሪ ስራ አስፈጻሚው ጠቅሰዋል። ቀደም ሲል ለአንድ የኮንዶም ባች ምርመራ 15 ቀናት ይፈጅ የነበረ ቢሆንም፣ አሁን ላይ ሰራተኞች ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ በትርፍ ሰዓትና በምሽት ጭምር እንዲሰሩ በማድረግ የምርመራ ጊዜውን እስከ 50 በመቶ በመቀነስ ወደ 7 እና 8 ቀናት ዝቅ ማድረግ ተችሏል።
በተለይም በሀገር አቀፍ ደረጃ የአቅርቦት እጥረት የሚያጋጥምባቸው አጋጣሚዎች ሲኖሩ ሂደቱን ይበልጥ በማፋጠን በ3 ቀናት ውስጥ ብቻ ምርመራውን አጠናቆ ለህብረተሰቡ ተደራሽ የማድረግ አሰራር መዘርጋቱን አቶ ቃልአብ ጠቁመዋል።
ኮንዶሞች ወደ ገበያ ከመውጣታቸው በፊት እንደ አየር መያዝ አቅም (ከ18 ሊትር በላይ መቻል ያለበት)፣ የግፊት መቋቋም (ከ1 ኪሎ ፓስካል በላይ) እና የቀዳዳ መኖርና አለመኖር (ሆል ቴስት) ምርመራዎች መቶ በመቶ እንደሚሰሩባቸው በማረጋገጥ፣ በግንኙነት ወቅት የሚፈጠሩ መቅረትና መበላሸቶች በአብዛኛው ከአጠቃቀምና ከተጨማሪ ሉብሪካንት አጠቃቀም ችግሮች ጋር የተያያዙ መሆናቸውንና ህብረተሰቡ በጥቅሉ ላይ ያለውን መመሪያ መከተል እንዳለበት አሳስበዋል።
በመጨረሻም፣ ባለስልጣኑ የላብራቶሪውን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት ለማሳደግ የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) የደረጃ ሶስት (Maturity Level 3) እውቅናን ለማግኘት በትጋት እየሰራ መሆኑን አቶ ቃልአብ አብስረዋል።
በአሁኑ ወቅት በአፍሪካ ደረጃ በህክምና መሳሪያዎች ዘርፍ ይህንን የደረጃ ሶስት እውቅና ያገኘ ሀገር የሌለ በመሆኑ፣ ኢትዮጵያ ይህንን ማሳካት ከቻለች የመጀመሪያዋ ሀገር ትሆናለች።
በቅርቡ በባለስልጣኑ በተደረገ ምርመራ የዓለም ጤና ድርጅት እውቅና (ፕሪኳሊፋይድ) በሰጠው የውጭ ፋብሪካ የተመረተ የማላሪያ መድኃኒት የጥራት ጉድለት ተገኝቶበት ውድቅ መደረጉንና ይህም የባለስልጣኑን የአስፈጻሚነት አቅም ያስመሰከረ ትልቅ ስኬት መሆኑን ገልጸዋል።
ይህ ተግባር የዓለም ጤና ድርጅትን ትኩረት የሳበ ሲሆን፣ በቀጣይ የኢትዮጵያ የህክምና መሳሪያ ጥራት ምርመራ ላብራቶሪ የዓለም ጤና ድርጅት እውቅና ያገኘ እና ለምስራቅ አፍሪካ (ኢጋድ) ሀገራት እንዲሁም ለአፍሪካ መድኃኒት ኤጀንሲ ዋነኛ የማመሳከሪያ ሆኖ እንዲያገለግል ታስቦ ሰፊ የልማት ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኝ አቶ ቃልአብ ተስፋዬ አረጋግጠዋል።
በጌትነት ተመስገን
#getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ
#efda #ethiopia #healthinnovation #qualityassurance #medicalstandards #africanpublichealth

Comments