6 months ago
ባስኬቶ
1,052 መዝገቦች በ9 ወራት ውሳኔ አገኙ
#ethiopia | የባስኬቶ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የ9 ወራት የሥራ አፈፃፀሙን ይፋ አድርጓል። ፍርድ ቤቱ የዳኝነት አገልግሎቱን ቀልጣፋና ተደራሽ ለማድረግ በሰራቸው ስራዎች አስደናቂ ውጤት ማስመዝገቡን የፍርድ ቤቱ ፕሬዚዳንት አቶ ታጋይ ኩምሳ ገልጸዋል።
ከቀረቡ 1,101 መዝገቦች ውስጥ 1,052 (95.54%) ውሳኔ አግኝተዋል።
ከተወሰኑት ውስጥ 85% የሚሆኑት (895 መዝገቦች) ከ2 ወር ባነሰ ጊዜ ውስጥ የተቋጩ ናቸው።
የሴቶችና ህፃናት ቀለብ ጉዳይ (53 መዝገቦች) እና የኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ ዕዳ አመላለስ (25 መዝገቦች) ሙሉ በሙሉ ውሳኔ አግኝተዋል።
በኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ በኩል ብር 201,759.45 ለመንግስት ተመላሽ እንዲሆን ተደርጓል።
ለ4,162 ተገልጋዮች የህግ ምክርና ንቃተ ህግ አገልግሎት ተሰጥቷል።
ለ86 አቅመ ደካማ ዜጎች (48 ወንድ እና 38 ሴት) ነፃ የህግ ድጋፍ ተደርጓል።
"ፍትህ መዘግየት ፍትህ መንሳት ነው" የሚለውን መርህ በተግባር እያሳየ ያለው የባስኬቶ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የላቀ ውጤት አስመዝግቧል።
#getu #basketozone #justiceethiopia #legalnews #courtperformance #ethiopia #legalaid #transparency #addisababamedia #ባስኬቶ #ፍትህ #የፍርድቤትዜና #ጌጡተመስገን #getutemesgen

Comments