6 months ago
ደማቁ የደርቢ ጨዋታ በአዲስ አበባ ስታዲየም
#ethiopia | በጉጉት የሚጠበቀው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ20ኛ ሳምንት ተስተካካይ መርሃ ግብር ዛሬ ተጠባቂውን ጨዋታ ያስተናግዳል። የሀገሪቱ ታላላቅ ክለቦች ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ኢትዮጵያ ቡና በአዲስ አበባ ስታዲየም ፊት ለፊት ይገናኛሉ።
🕒 የጨዋታው ዝርዝር
ተጋጣሚዎች :-ቅዱስ ጊዮርጊስ vs ኢትዮጵያ ቡና
ሰዓት፡ ዛሬ ቀን 9፡00 ሰዓት
ቦታ፡ አዲስ አበባ ስታዲየም
📊 የደረጃ ሰንጠረዥ ሁኔታ
ጨዋታው በደረጃ ሰንጠረዡ ላይ መጠነኛ ዝቅ ብለው ለሚገኙት ለሁለቱም ክለቦች ወደ ላይ ለመውጣት ወሳኝ ነው።
ኢትዮጵያ ቡና፡ በ38 ነጥብ 7ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
ቅዱስ ጊዮርጊስ፡ በ35 ነጥብ 10ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
በሌላ በኩል የሊጉን መሪነት ሲዳማ ቡና በ54 ነጥብ ሲመራ፣ መቻል እና ነገሌ አርሲ በ44 ነጥብ ተከታዩን ደረጃ ይዘዋል። ሀዋሳ ከተማ በ43 ነጥብ 4ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
🔥 የኮከብ ግብ አግቢዎች ፉክክር
የዛሬው ጨዋታ የቡድኖች ብቻ ሳይሆን የጎል አዳኞችም ፍልሚያ ነው።
አቤል ያለው (ቅዱስ ጊዮርጊስ)፦ በ14 ግቦች የሊጉን ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት እየመራ ይገኛል።
አዲስ ግደይ፦ በ10 ግቦች በቅርብ ርቀት ይከተላል።
በአዲስ አበባ ስታዲየም የሚደረገው ይህ ታላቅ ጨዋታ ማን የበላይነቱን ይወስድ ይሆን? ፈረሰኛው ወይስ ቡናማዎቹ? አብረን የምናየው ይሆናል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu
#ethiopianpremierleague #kidusgiorgis #ethiopiabunna #shegerderby #abelyalew #addisababastadium #ethiopianfootball

7 months ago
የአንድነት ጥሪ
🌎 በመላው ዓለም ለምትገኙ የፈረሰኞቹ ደጋፊዎች በሙሉ
#ethiopia | የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብን ታሪካዊ ክብር ለመታደግ የቀረበ አንድነት ጥሪ ከቀድሞ የክለቡ ተጫዋቾችና የክለቡ አሁናዊ ሁኔታ እጅግ ያሳሰባቸው ከክለቡ ደጋፊዎች የቀረበ ጥሪ ለክለቡ የቦርድ አባላት፣ ለስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ እና በመላው ዓለም ለምትገኙ የፈረሰኞቹ ደጋፊዎች በሙሉ፦
ለዘጠኝ አስርተ ዓመታት ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርታዊ ክለብ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያዊነት መለያ፣ የጽናት ተምሳሌትና የድል አድራጊነት ማማ ሆኖ ቆይቷል። ዛሬ ግን ይህ ታላቅ ተቋም ታሪካዊ በሆነ አስቸጋሪ ወቅት ላይ ይገኛል።
በደጋፊዎች መካከል የተፈጠረው አለመግባባት፣ የሚለዋወጡት አሳዛኝ ቃላት እና በክለቡ አመራሮች መካከል የተፈጠረው ቀውስ የክለቡን የቦርድ አስተዳደር በሕግ እንዲታገድ አድርጎታል። ይህ ሁኔታ የክለቡን ህልውና አደጋ ላይ ከመጣሉም በላይ ለውድቀት አፋፍ እያደረሰው ይገኛል።
እኛ የቀድሞ የክለቡ ተጫዋቾችና ደጋፊዎች፣ ክለባችን ሲፈርስ ዝም ብሎ ማየት የታሪክ ተጠያቂነት እንደሆነ እናምናለን። በመሆኑም፣ ክለባችንን ከመፍረስ ለመታደግና ሁሉንም ወገኖች አሸናፊ የሚያደርግ መፍትሄ ለማምጣት ይህንን የአንድነት ጥሪ በይፋ አቅርበናል።
የመፍትሄ ሀሳቦች
የክለባችንን ክብር ለመመለስ የሚከተሉት ሁለት ነጥቦች በአስቸኳይ እንዲተገበሩ ጥሪያችንን እናቀርባለን፦
፩. የቃላት ጦርነት ይቁም (ክብርን መልሶ ማግኘት)
በተለያዩ ወገኖች መካከል የሚደረጉ እርስ በርስ የሚያቃቅሩ፣ ለክለቡ ክብር የማይመጥኑና የጠላትነት መንፈስን የሚያንጸባርቁ የግንኙነት መንገዶች በአስቸኳይ ይቆሙ።
ቁርጠኝነት፦ ሁሉም ደጋፊዎችና አመራሮች በማህበራዊ ሚዲያም ሆነ በአካል የሚያደርጉትን የቃላት ምልልስ በመግታት፣ ለሰላማዊ ውይይት ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ እንጠይቃለን።
ግቡ፦ የሰለጠነና ለክለቡ እድገት የሚበጅ የውይይት ድባብ መፍጠር ነው።
፪. በጠቅላላ ጉባኤ አማካኝነት አጥኚና መፍትሄ አፍላቂ ኮሚቴ ይቋቋም
በክለቡ መተዳደሪያ ደንብና ሕግጋት መሠረት፣ የአመራር ክፍተቱን ለመሙላትና የሕግ ጥያቄዎችን ለመመለስ የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ በአስቸኳይ ይጠራ።
ተግባር፦ ጠቅላላ ጉባኤው ጉዳዩን በጥልቀት መርምሮ ለሁሉም ወገኖች ተቀባይነት ያለውና ክለቡን ወደ ቀድሞ ጥንካሬው የሚመልስ "አጥኚና መፍትሄ አፍላቂ ኮሚቴ" እንዲያቋቁም እንጠይቃለን።
ውጤቱ፦ የግለሰቦች ፍላጎት ሳይሆን የክለቡ ህልውና የበላይነት የሚረጋገጥበት የአሸናፊነት መንገድ መጥረግ ነው።
ማጠቃለያ
ቅዱስ ጊዮርጊስ የግለሰቦች ሳይሆን የሚሊዮኖች ኩራትና የሀገር ሀብት ነው። ዛሬ የምናደርገው ውሳኔ ለቀጣዩ ትውልድ የምናስተላልፈውን ክለብ ዕጣ ፈንታ ይወስናል።
ልዩነቶቻችንን በውይይት ፈተን፣ ታሪካዊውን ክለባችንን ከውድቀት እንታደግ!
ፈረሰኛው ዳግም ይጋልባል!
የቀድሞ ተጫዋቾችና የደጋፊዎች ጥምረት
ST George Former Players and Supporters Association in USA
አንድ ክለብ አንድ ቤተሰብ!

ምንልክ ያችን ሰዓት
(ጋሻው ደበበ አለሙ)
▫️መነሻ ሀሳብ -ፕሮፌሰር ማስረሻ ፈጠነ
▫️አርትኦት- አሰግደው ሽመልስ
የካቲት 23/ 1888 ማለዳ ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት እምዬ ዳግማዊ አጤ ምኒልክ አድዋ ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ያረጉት ፀሎት
ስብሐት ለእግዚአብሔር- ኅያው በመንበሩ
ሰላም ለዛቲ -ሃገሪትነ ቅድስት
ወሰላም ለህዝብየ- ዘይሔሉ ለምድሩ
ዘይመውት -ለክብሩ ፡፡
ምስጋና ለሕያው አግዚአብሔር
ሰላም ለዚህች -አንድ ቅድስት አገር
ሰላም ለደጉ ህዝቤ-አፈሬን ብሎ ለሚኖር
ክብር ላንተ-ሰማዕቱ የእናት የአባቴ ታቦት
ጊዮርጊስ መመኪያዬ-እንግዴህ ከፊቴ ዝመት
መንገድ ጥረግ ፈረሰኛው -ቀዳማዊው ሰራዊት
ተማርኩ ያለ አገር ሊዘርፍ-ውል አዛንፎ በለበጣ
የነገር ፈሩን ስንጨብጥ -ለሴራው ብልሐት ሲያጣ
ለጦር ልቡ ሸፍቶ -ዳር ድንበር ጥሶ ከመጣ
ፈርሐ-እግዜር የሌለው ጣሊያን -ህዝቤን በጅምላ ሲወር
በህዝቤ ተደምስሶ -አደዋ አረህ ውስጥ ሲቀር
በሟጥሽ ስር ተበትኖ -በአጋም ስራስር ሲሰባበር
እለቱ በደም ታፍኖ-ሰልስቱን በአሞራ ሲያከብር
ኪደነ-ምህረት ገሰሶ-ምንድብድብ ሸዊቶ ሜዳ
እማርክ ብሎ የመጣ -ሞቱ በአፍታ ቢረዳ
እኔ ክፉ እማይደለሁ -ልቤን ቅር እንዳይለው ነገር
መቼም ነፍሰ-እግዚሃር ነውና…
ክብር ለሃያሉ አምላክ -ቃሌን ቀድሜ ልናገር ፡፡
ቴወድሮስ ይሙት! ቃሌ ነው!!
እኔ ምኒልህ …
አይኑን ለጨፈነ ጠላት -እዝኑን ለደፈነ ጦረኛ
መልህቅ ቢያነሳ ብዬ እንጂ -ይሔ ነጭ ነውረኛ
አወድመው እንደሳት ሰደድ -እመታው እንደመጋኛ፡፡
እንዴት አይነት ጥጋብ ነው ? እንዴት አይነት መወፍነን?
ምኒልክን ለባርነት- ኢትዮጵያን ለቅኝ ግዛት
አሳብ ጠንስሶ መጅመንመን?
እንዴት አይነት ንቀት ነው -ምን የሚሉት ሰማይ ማከክ?
ጣሊያን ሱሪ የለበሰው ሐበሻን ለማንበርከክ?
......
አዬ ያገሬ ጀግና
አንጀተ ፅኑው ገበሬ
በማርያም መማፀኔን -ያገር አዋጄን ሰምቶ
ከመናገሻ እስከ ሀረር በጌምድር ተጠራርቶ
የአራት ማዕዘን -ጀግና ድፍን ኢትዮጵያ ተነስቶ
በሮቹን ባለህ ባይ ሳይኖር -ዝሪቱን ለተባይ ትቶ
ወንጭፉን ከማማ ሰቅሎ -ጦርና ጋሻ አንግቶ
ምኒልህ ጠራኝ ብሎ -በጭብጦ ተሸኝቶ
በእፍኝ ጥሬ-ከቤት ወጥቶ
ላመል ታህል በኮዳ ውሃ-ከምንጭ በቅል ጠጥቶ
ለእግሩ ከለላ ሳይኖረው -አሜኮላውን ጥሶ
ጫካውን በግር በፈረስ -ዥው አርጎት እንደኮሶ
ላገር ሟቹ ቃል ጠባቂው ይሔው አደዋ ከተመ
ለነፃነቱ እልፍ ሆኖ -ለክብሩ በአንድ ተመመ
የአብሮነት ቃልኪዳኑን -በባንዲራው ስም አተመ፡፡
እና ከዚህ በላይ -ምን ደስታ አለ?
ከህዝብና ከክብሩ- ሰው ካገሩ ከዋለ
እምነትና ጀብዱን ታጥቆ -አገሩን ብሎ ለመጣ ሰው
እስከ አፅናፍ የሚነገር -ድል ነው ፀዲቅ የሚቆርሰው፡፡
እንደ ቤተ-መቅደሱ -እንደ ሞገሩ ሽታ
እንደ ነጋሪቱ ድምፅ -መለከትና እምቢልታ
ተመስገን ያባቴ አምላክ -ልቤ ሃሴት ተሞልቷል
ሰማዕቱ በእለተ ቀንህ -ክንዴ እልፍ ጦር አንግቷል
ህዝቤ -አፎቱን ከፍቷል
ብቻ ህልም አየሁ በሰመመን…
አንጎለላ ኪዳነምህረት -ከደጅሽ የወይራ አፀድ
በቀስተዳመና ተከቦ- አንዱ ክንፍ ተቆርጦ ሲወርድ
ይሔ ሃሞተ መራር-ይሔ ልበ ተራራ
የሰው ምክር ግድ የለው-ትንሽ ለነፍሱ አይፈራ
ቀኝ እጄን እንዳላጣው- ክንዴን ገበየሁን አደራ::
ክብር ለአያቶቼ
ኢትዮጵያን ከነ-ስሟ -ከነ ክብሯ ላኖሯት
ጣሊያን ጉድጓዱ ይገባል -ዛሬም ማንም አይደፍራት።
የካሳ እልፍኝ ይታዘበኝ -ጦር ሰልጥኜ ያደኩበት
ልበ-ባህሩ ሸዋ -አባ መቻል-አባ መስጠት
ስም አልጠራም አባባ ብዬ -አይወልደኝም ሀይለመለኮት
እኔ ዳኘው ምኒልህ -ወገኔን ካሳፈርኩት !!
በቀዳማዊ ምኒልክ -በሳህለ ሥላሴ መንፈስ
በአያቴ ወንበር ዘውድ ስጭን -በጥንቶቹ አልጋ ስነግስ
እንዴት ተብሎ ቃል ቢዛነፍ-ጫፏ ይነካል አገሬ
አፍር ይሆናል እንጂ-ጠላት ይገባል መረሬ!!
እውነት ኪዳነ-ምህረት -በቀንሽ ቅጠል ሳልበጥስ
ዳዊት ከደጅሽ ደግሜ -ፀበል ጠጥቼ ሳልሰልስ
ቆመ-ብዕሴሽን ታሽቼ-ገራገራሽን ተሳልሜ
የኖርኩት የከበርኩት -ባንች እማዶለ አለሜ !
ፈገግተዋ የሚያጠግበኝ-የመኖር ውሃ ሙላቴ
እንግዲህ አንቺ ከልያት-ከፊት ቀድማለች ጣይቴ ፡፡
አሔሔ!
ኢትዮጵያዊነት ሥሙ -ሀይሉ ካድማስ የሚርቀው
የወገኔ እንኳን ጦሩ-ድምጡ ጠላት የሚንደው
ከወረይሉ እስከ ሶሎዳ - እየፎከረ የተመመው
እምቢ ብሎ እንደመጣ -የድል ጀንበር ሊያሳልፍ ነው፡፡
እንግዴህ ይህ ነው ፀሎቴ ...
ይህ ቀን -ታላቅ ነውና -
የኢትዮጵያ ሐያልነት በአደባባይ ይወሳ
ወራሪ አጥንቱ ደቆ- ከደሃ ላይ እጁን ያንሳ
አንበሳ አንበሳ ነውና- እንደትላንቱ ዛሬም ያግሳ
ጥቁርና የጥቁር ምድር- አንገቱ ቀና ይበል
የሐበሻን ጠንካራ ክንድ -አውሮጳም አምኖ ይቀበል ።
እኔ ምኒልህ
አይኑን ለጨፈነ ጠላት -እዝኑን ለደፈነ ጦረኛ
ልቦና ቢገዛ ብየ-እንጂ -ይሔ ነጭ ነውረኛ
አወድመው እንደሳት ሰደድ -እመታው እንደመጋኛ፡፡
ብቻ ህልም አየሁ በሰመመን…
አንጎለላ ኪዳነምህረት -ከደጅሽ የወይራ አፀድ
በቀስተዳመና ተከቦ -አንዱ ክንፍ ተቆርጦ ሲወርድ
ይሔ ሃሞተ መራር-ይሔ ልበ ተራራ
የሰው ምክር ግድ የለው-ትንሽ ለነፍሱ አይፈራ
ቀኝ እጄን እንዳላጣው ክንዴን ገበየሁን አደራ፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

⚽️ "ከአሸዋ ሜዳ እስከ አርጀንቲና"
የፈረሰኛውና የቡናው ኮከብ አሸናፊ ግርማ ታሪክ በድጋሚ ታተመ! 📚
#ethiopia | በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ ውስጥ ተወዳዳሪ የማይገኝለት የአማካይ ስፍራ ዝነኛው ተጫዋች አሸናፊ ግርማ፣ የሕይወት ታሪኩን የያዘውና በጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) የተጻፈው መጽሐፍ ማሻሻያዎች ተደርገውበት ለሁለተኛ ጊዜ ታትሞ ለንባብ በቅቷል።
በ350 ገፆች ተቀንብቦ በአማርኛና በእንግሊዝኛ (በአንድ ጥራዝ) የታተመ ሲሆን፣ በካናዳም ለንባብ በቅቷል።
ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ ሙሉ በሙሉ ለበጎ አድራጎት ሥራ እንደሚውል አሸናፊ ገልጿል።
በቀጣይ ታሪኩ በድምፅ ተተርኮ በዩቲዩብ እንደሚጫን ተነግሯል።
📅 የምርቃት ጥሪ፦
ቀን፦ ቅዳሜ የካቲት 21/2018 ዓ.ም
ሰዓት፦ ከቀኑ 11:00 ሰዓት ጀምሮ
ቦታ፦ ሆቴል ደ ሊኦፖል (Hotel De Leopol)
🏆 አሸናፊ ግርማ ማን ነው? (ለማስታወስ ያህል)
የሴካፋ ጀግና፦
ሦስት ጊዜ የሴካፋ ዋንጫን ያነሳ ብቸኛው ኢትዮጵያዊ ተጫዋች ነው።
የዓለም መድረክ፦
በ1993 ዓ.ም በአርጀንቲና በተካሄደው የዓለም ወጣቶች ዋንጫ (World Youth Championship) ሀገራችንን ወክሎ ተጫውቷል።
የቡናው ፈርጥ፦
በኢትዮጵያ ቡና ማሊያ ሁለት ጊዜ የዓመቱ ኮከብ ተጫዋች ሆኖ ተመርጧል።
በምርቃቱ ዕለት ከወጣቶች አካዳሚና ከአዲስ አበባ ለተውጣጡ 105 ወጣቶች መጽሐፉ በነፃ የሚበረከትላቸው ሲሆን፣ ይህም ለታዳጊዎች ትልቅ መነሳሳትን ይፈጥራል።
መጽሐፉን በ500 ብር ከጃዕፋር መፅሐፍት ቤት ማግኘት ይቻላል።
#አሸናፊግርማ #ከአሸዋሜዳእስከአርጀንቲና #ኢትዮጵያቡና #የኢትዮጵያእግርኳስ #መጽሐፍምርቃት #ethiopianfootball #ashanafigirma #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ምልክት "ፈረሰኛው" አደጋ ላይ ነው! 🐎⚽️
#ethiopia | ታሪካዊውና በስኬቶቹ አቻ የማይገኝለት ቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ፣ በከፋ የፋይናንስ እጥረት ምክንያት "የመፍረስ አደጋ" እንደተጋረጠበት ተሰምቷል።
የክለቡ ታሪክና ስም ከሚመጥነው በላይ አሁን ያለው እውነታ እጅግ አሳሳቢ ሆኗል።
🔍 ወቅታዊው የጥቁር አንበሳው ቀውስ፦
የደመወዝ እጥረት፦
ተጫዋቾች ላለፉት 4 ወራት ደመወዝ እንዳልተከፈላቸው ታውቋል።
የአምበሉ መልቀቂያ፦
የቡድኑ መሪና አምበል አቤል ያለው፣ በሁኔታው በመማረር የመልቀቂያ ደብዳቤ አስገብቷል።
የልምምድ መቋረጥ፦
ለሁለተኛው ዙር ዝግጅት ጥሪ ቢደረግም፣ ተጫዋቾች ባለመገኘታቸው ሰኞ ዕለት በወጣቶች ብቻ ልምምድ ተደርጓል።
📉 ከሜዳ ውጪ ያለው ፈተና፦
ክለቡ በሊጉ መጀመሪያ ላይ ለዋንጫ ተፎካካሪነቱን ቢያሳይም፣ አሁን ላይ ግን በውስጣዊ ችግሮች ምክንያት ውጤት እየራቀው ይገኛል።
አዲሱ ሥራ አስኪያጅ ነገሮችን ለማስተካከል "ታገሱን" የሚል ማግባባት እያደረጉ ቢሆንም፣ ደጋፊዎች ግን "የክለቡ ህልውና አደጋ ላይ ነው" የሚል ስጋታቸውን በአጽንኦት እየገለጹ ነው።
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ምልክት የሆነው ቅዱስ ጊዮርጊስ በፋይናንስ ጥንካሬው የሚታወቀውና በግዙፍ የደጋፊ መሰረት የታነጸ፤ የአሸናፊነት ታሪክ ያለው ታላቅ ክለብ ነው።
ዐቢይ ዘላለም
#ቅዱስጊዮርጊስ #ፈረሰኛው #ኢትዮጵያእግርኳስ #stgeorgesa #ethiopianpremier League #savestgeorge #sportethiopia #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

8 months ago
🐎አጅባር ከሜዳው ስር እትብቴ ተቀብሮ፣
ደብረ ታቦር ያድራል ልቤ ዞሮ ዞሮ
* ከአጅባር ሜዳ እስከ ዴንሳ ግርጌ... ሰማይና ምድሩ የደመቀበት የቅዱስ መርቆሬዎስ ንግሥ! ⛪️
#ethiopia | ዛሬ የደቡብ ጎንደር ምድር በልዩ ድምቀት ታጅባ ዋለች። በታሪካዊቷ ደብረ ታቦር (አጅባር) እና በአምሳለ-አንበሳው እስቴ (ዴንሳ) ግርጌ የተከበረው የቅዱስ መርቆሬዎስ በዓል፤ ኢትዮጵያዊነትን፣ ጀግንነትንና እምነትን አስተሳስሮ አሳይቷል።
📍 ደብረ ታቦር - አጅባር ሜዳ
ምድሩ በጀግኖቹ የፈረስ ግልቢያ ሲናወጥ፣ ሰማዩ በምስጋና እና በዘመናዊ የአየር ትርኢት ደምቆ ታይቷል። የበጌምድር መገለጫ የሆኑት ፈረሰኞች የሽምጥ ግልቢያ እና የጦር ውርወራ ጥበባቸውን ሲያሳዩ፤ የቀደሙት ነገሥታት ታሪክ በህያውነት ተመስሏል። ነዋሪዎቹም "እልፍኙ ተውቦ ነጭ ጤፍ እንጀራ እየተጋገረ" እንዲሉ፤ እንግዳን በክብር ተቀብለው አስተናግደዋል።
📍 እስቴ - የዴንሳ ግርጌ
"የአንች ሀገር ወዴት ነው የእኔስ ሀገር እስቴ" የተባለላት እስቴ መካነ ኢየሱስ፤ ከ8 የፈረስ ማኅበራት በተውጣጡና "ፈረስ እንደ አሞራ" በሚያበሩ ጀግኖች ተሞልታለች። ከባለግርማው ዴንሳ ተራራ ግርጌ የታየው ትዕይንት ለዓይን የሚማርክ ነበር።
ዛሬ ፈረሰኛው ፈረሰኛውን ሰማዕት (ቅዱስ መርቆሬዎስን) አጅቦ፤ ጥርን በድምቀት ሸኝቷል።
ይህቺ ናት አገሬ፤ ይህቺ ናት ኢትዮጵያ! 💚💛❤️
#debretabor #ajbar #este #densa #stmerkorios #gugs #culture #ethiopia #amhara #tourism #tradition #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

Sponsored by
Surafel
8 months ago
ፈረሰኛውና ፈረሶቹ በጥቅሻ የሚግባቡበት ምድር‼️
🐎🐎🐎🐎🐎🐎🐎🐎🐎🐎🐎🐎🐎🐎
#ethiopia | ምድሩ ለፈረሶች ተመርጦ የተፈጠረ ይመስላል፤ ሕዝቡም ፈረስን ከሰማይ በአደራ የተቀበለ ደገኛ ሕዝብ ። የአገው ታሪክ በፈረስ ኮቴ በለምለም ምድር የተጻፈ በትውልድ የሚነበብ ሕያው ብራና ነው። 🐎🐎🐎
የአገው ታሪክ እንደ አምፖል ከጣራ በታች ሳይሆን እንደፀሐይ ከሰማይ በታች የሚያበራ ብርሃናማ የተጋድሎ ታሪክ ነው። አክሱም ሲነሳ ፈረሰኛው አገውና ፈረሶቹ በዚያ ይነሳሉ ።
ላሊበላም ሲዘከር ከነ ዛጉዌ ሥርወ መንግስታቸው ንጉስም ቅዱስም፤ ካህንም አናጺም፤ መሪም ዘካሪም ኾነው
ፈረስ ጋላቢዎቹ አገዎች፣ ከተጋላቢዎቹ ፈረሶቻቸው ጋር በወርቅ ቀለም ተጽፈው በዚያ አሉ።
የፓን አፍሪካኒዝም የልደት ምስክር ወረቀት አድዋ ሲነሳም ፈረሰኞቹ አገዎችና ፈረሶች፤ በአይበገሬነት ታሪካቸው በደማቁ ድላቸው በዚያ አሉ። በአድዋ ተራራ ከተቀበሩ እልፍ አርበኞች አጽም ጋር የፈረሶች አጽምም በዚያ አለ። ፈረሰኛውና ፈረሶቹ በየታሪኩ ምዕራፍ ለሀገር ግንባታ ጡብ ደርድረዋል፤ የስማቸውንም ሐውልት አቁመዋል ። 🐎🐎🐎
የፈረስን ውለታ አገው ያውቀዋል፤ እንኳን ለባለውለታው ፈረስ፤ ነፍስ ላለው ፍጥረት ሁሉ የሚራራው የአገው ሕዝብ፤ ፈረስን እንደ ልጁ መርጦ ይመግበዋል። በሥርዓትና በማዕረግ ያሳድገዋል፣ በትጋትና በሥልጣኔ ይገራዋል፣ በግርማና በሞገስ በተዋቡ አልባሳትና ጌጦች ይሸልመዋል። ፈረሱን በልኩ እንዲሠራ በሚገባውም እንዲያርፍ ያደርገዋል። 🐎🐎🐎
ፈረሱም ለአባቱ ለአገው ሕዝብ እንደሚታዘዘው ለሌላው የሚገራና የሚታዘዝ አይመስልም ። በእርሻው በኩል በግራም በቀኝም ተጠምዶ ትከሻው እስኪላጥ አርሶ፣ ወቅቶ፣ አዝመራ ተሸክሞ ወደ ጎተራ አስገብቶ አገልግሏል ። 🐎🐎🐎
አገው ልጁን ቢድር ሙሽሮቹን እንደሊሞዚን ተሸክሞ ጫጉላ አውጥቷል ። ቢታመም እንደ አምፑላንስ ኾኖ ሐኪም ደጅ አድርሷል ። ሞት መከራ ቢመጣ ከአልቃሽና አስለቃሽ ጋር ደክሞ፣ አልቅሶ በክብር ይሸኛል ። ዘመድ ቢናፍቁ ፈጣን ትራንስፖርት ኾኖ ወንዝ አሻግሮ ዘመድ በማገናኘት ናፍቆትን አስወጥቷል ። 🐎🐎🐎
አይሞሎ አይሞሎ ሞሎ ዎ!
ሲዋጋ ውሎ ሲዋጋ አመሸ፣
ጋሻውን በዘንግ እያንኮላሸ፡፡
ቦራ ብሎ ጠራው ጀግና ፈረሱን፣
እንኳን አግዜር ሰጠው የተመኘውን፡፡
የጀግናው ባለሟል እኔነኝ ፈረስ፣
ከተፋፋመው ጦር አብሬ ምደርስ፡፡
ጀግናው ፈረሰኛ መጣ ገሰገሰ፤
የጠላቱን ምሽግ እየደረመሰ። የተባለለት ...🐎🐎🐎
ጠላት ቢመጣ ጦር ሜዳ አድርሶ፣ ጠላትን እየረገጠ፣ በጌታው ፋንታ በጦሩም፣ በጎራዴውም፣ በጥይቱም እየቆሰለና እየሞተ ተዋግቷል ። ክብረ በዓላቱን ትርዒት እንደሰለጠነ ወታደር በሥርዓት ተሰልፈው ሰላምታ እየሰጡ ያደምቁታል። 🐎🐎🐎
ለዚህም በአገው ምድር ፈረስ፤ አርበኝነት፣ ነጻነት፣ ድል አድራጊነት፣ የሀገር ፍቅር እና አንድነት የሚንጸባረቅበት የድል ምልክት ኾኖ ይዘከራል ። ፈረሰኛው በንፁህ ባርኔጣ፣ በሎፊሳ፣ በነጭ ኮት እና ሱሪ (ግርቭ ታምባ) በገምባሌ እና አለንጋውን ከሰነደቁ ፤ ጋሻውን ከዘንጉ ጋር ይዞ ከመድመቁ በላይ፤ ፈረሱ በኮርቻ፣ በልቫቭ፣ በልጓም፣ በአምፓጉሲ እና በወደሊ ቀይ አበባ ይደምቃል፡፡ 🐎🐎🐎
የፈረሱ ሰላምታ አሰጣጥ፣ የድንግል ዓሳ ትርዒት፣ የስግሪያ፣ የጉግስ ፣ እና ሽርጥ ትርዒት ሲካሄድ ማየት ልብን ቀጥ የሚያደርግ ደስታ ይሰጣል። ፈረሰኛውና ፈረሱ በጥቅሻ የሚግባቡበት፣ የፈረስ ማዕበል በቀይ ጌጥ ተውቦ የሚፈስበት ትርዒት በአገው ምድር ሰማይ ሥር ይታያል። 🐎🐎🐎
ለሕጻናት ፈረሰኞች የሚታዘዝ ፈረስ በዚያ አለ፤ ለዐይነ ሥውሩ የሚታዘዝ መንገድ መሪ ብቻ ሳይሆን ከዐይናማዎቹ ጋር ተወዳድሮ አሸናፊ ፈረስ በዚያ አለ። ሴት ፈረሰኞች የሳይንስን የዙረት ስሌት ሽረው እየተሽከረከሩ የሚጋልቡት ፈረስ፣ በምልክት ተረድቶ የሚሽከረከር ፈረስ በአገው ምድር ይታያል ። 🐎🐎🐎
በአገው ምድር ሰባቱ ወንድማማቾች «አንክሺ፣ ባንጂ፣ ዚጋሚ፣ አዚኒ፣ ኳኩሪ፣ ቻሪና ሚቲክሊ» እንደአንድ ልብ መካሪ እንድ ቃል ተናጋሪ ናቸው። ፈረስ 🐎 ልዩ ምልክታቸው ስልጣኔ መለያቸው ነው።
ፀሐዩ አይሰማም እንጅ ከተሰማህ ለፀሐዩ አዊት ድጋግ (የአገው ጥላ) አለ። ለሆድህ አትጨነቅ አብዚ፣ ጉዝጉዝ፣ በመልክ በመልኩ ከጠላው ከጠጁና ከብርዙ ጋር በበቃኝ ይቀርባል ። በአገው ምድር የምታየውን ዐይተህ ታደንቀዋለህ፣ እያሰብኸው ትደመማለህ እንጅ ለመጻፍ እንዴት ይቻላል ?
በዚያ ምድር የተገኘህ፣ ፈረሰኛውና ፈረሶቹ በጥቅሻ ሲግባቡ ያየህ፣ ከፈረሱ ጋር ተጫወት።
አይሞሎ አይሞሎ ሞሎ ዎ! 🐎🐎
የፈንዞ ጌታ፣ የጥሪኝ ጌታ የሻሾ ጌታ፤ 🐎🐎
ጀምር ጨዋታ በል ጋሻ ምታ ግጠም እስክስታ ።
👉62 ሺህ ፈረሰኞችና ፈረሶች ያሉት፣ 🐎🐎🐎
👉86 ዓመታትን በሦስት ዐለቃ እየተመራ ዛሬ ላይ የደረሰ፣
👉ባህልን፣ ታሪክን፣ ባለውለታን የሚዘክር፣
👉 የድል አድራጊነት ምልክትና አንድነትን የሚያጠናክር፣
‼️ የአገው ፈረሰኞች 🐎 ማኅበር ‼️👌
እንኳን አደረሳችሁ ‼️
እንኮዋን 86ንቲ አጋው ፌሬስቴኑ ባልስ ታምፅኾስ‼️
🐎🐎🐎 የሀብከ ብርሃኔ ጥላሁን 🐎🐎🐎

Comments