5 months ago
#ቃለየሱስ በቀለ - የአቪየሽን ወርቃማው ጋዜጠኛ
#ethiopia | ተወዳጅ ሚድያ እና ኮምዩኒኬሽን ፣ መዝገበ-አእምሮ ( የአማርኛ ኢንሳይክሎፒዲያ ) ፕሮጀክቱ ለአገር የሠሩ ሰዎችን ታሪክ እየሰነደ እንደሆነ ይታወቃል። ይህ ታሪክ በዲጂታል ሚድያዎች ፣በመፅሀፍ፣በድምፅ ትረካና በሌሎችም መንገዶች እየቀረበ እንደሆነ ይታወቃል።በተለይ ጉግል ላይ ታሪካቸው ሲፈለግ የማይገኝ ሰዎች አሁን የሙያ አበርክቷቸው በቀላሉ ኢንተርኔት ላይ በግልፅ ተቀምጦ ይገኛልደ ባለፉት 4 ዓመት ከ 5 ወር ጊዜ ውስጥ የ423 ሰዎችን የሕይወትና የሥራ ታሪክ ለመሰነድ የቻልን ሲሆን 600 ገፅ ባላቸው ሁለት የተለያዩ መፅሐፎች ላይም ታሪኮቹ ዘመን ተሻጋሪ ሆነው እንዲቀመጡ አድርገናል።
#በዚህ የስነዳ ሥራችን ውስጥ በቅፅ 3 ከተካተቱት 20 ዘርፎች ውስጥ የሥራ ዘርፎች ውስጥ ሚድያ አንዱ ነው። በአሁኑ የሚድያ ሰዎችም፣ የቴአትር ባለሙያዎች እየተሰነዱ ይገኛሉ። አጠቃላይ 74 ከፍተኛ የሚድያ አመራሮች፣ሚኒስትሮች ፣ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ የግል ሚድያ መሥራቾች፣ዋና አዘጋጆች እና መካከለኛ አመራሮች ተካተዋል። 35 ያህሉ በዋና ሥራ አስፈጻሚ ደረጃ ያሉ ሲሆን የሁሉም ታሪክ በተሟላ ደረጃ ለመሰነድ ተችሏል። የእነዚህን ሰዎች ታሪክ ሰንዶ ለአንባቢ ተደራሽ ማድረግ ፈታኝ ቢሆንም አሳክተነዋል። በዚህ ተግባራችንም ተጠናክረን እንቀጥላለን።
#ዛሬን ሰንደን የምናስነብባችሁ የሚድያ ባለሙያ የቃለየሱስ በቀለን የሙያ ታሪክ ነው። በሚድያው ሥራ ሩብ ክፍለ- ዘመን የዘለቀው ቃለየሱስ በአቬሽን እና ማዕድን ላይ ትኩረት ሰጥቶ በመዘገብ ትልቅ አሻራ አኑሯል። በጋዜጠኝነት ሙያ ውስጥ በአገራችን በአንድ ርዕስ ላይ ትኩረት ሰጥቶ ወይም ተክኖ መዘገብ ባልተለመደበት ሁኔታ ቃለየሱስ ችሎ አሳይቷል። ከባለታሪኩ የተገኘውን መረጃ በማግኘት፣ የቅርብ ሰዎቹን በማነጋገር የሙያ ታሪኩ ተሰንዷል። ዕዝራ እጅጉ እና ታደሠ ማሞ አጠናክረውታል።
፨፨፨፨፨ ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ ፨፨፨፨፨፨፨፨፨
#ትውልድና ዕድገት
‹‹የትኛውም አውሮፕላን ወደ አየር አኮብኩቦ መነሳቱ የተለመደ የጉዞው አማራጭ ቢሆንም አውሮፕላኑ ካሰበበት ደርሶ ማረፉ ደግሞ የግድ መሆን ያለበት ተግባር ነው፡፡››የሚል የአቪየሽን አባባል አለ፡፡በዚህ አባባል ተንደርድረን ወደ ውስጥ እንዝለቅ፡፡ሁሉም ዘርፍ የየራሱ አነፍናፊ ጋዜጠኞች እንዳሉት ሁሉ ቃለየሱስ በቀለ የተባለ ህልመኛና ደፋር ጋዜጠኛ በአቪየሽኑ ዘርፍ በተለየ መንገድ የራሱን የብዕር አሻራ ማኖር መቻሉ የዚህ ፅሁፋችን መነሻ ነው፡፡
#ቃለየሱስ በቀለ የውልደቱም ሆነ የእድገቱ መነሻ የምስራቅ ሸዋ አዳማ (ናዝሬት) ከተማ ናት፡፡ሀምሌ 18/1967 ዓ.ም በአዳማ ሀይለ ማሪያም ማሞ ሆስፒታል ቃለየሱስ የተባለ ብላቴና ከተፋፋመ ምጥ ውስጥ ወቅቱ አብዮታዊ ለውጥ ኢትዮጵያን በሚንጥበት በዚያ ጊዜ የለውጥ አየሩን እየማጉ ድምፃቸውን በማሰማት ይቺን ምድር ከተቀላቀሉት ጨቅላዎች አንዱ ሆኖ ተመዝግቦ በስሙ የልደት ካርድ ወጣለት፡፡
#ይህ ሰው ከመዋዕለ ህፃናት እስከ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ያለውን የትምህርት ጉዞውን ያሳለፈው በናዝሬት ቅዱስ ዮሴፍ ት/ቤት ነው፡፡ትምህርት ቤቱ ከቀለም ትምህርት በተጨማሪ ተማሪዎችን በግብረ ገብና በመፅሀፍ ቅዱስ ትምህርት አንፆ በማብቃት ረገድ የተዋጣለት እንደነበር ቃለየሱስና አብረውት የተማሩት ሁሉ የሚመሰክሩት ሀቅ ነው፡፡
#በ1986 ዓ.ም ውጤታማ ሆኖ የአዲስ አበባ ንግድ ስራ ኮሌጅን ደጃፍ መርገጥ የቻለው ቃለየሱስ በኮሌጁ ሁለት ዓመታት በአካውንቲነግ ሙያ ተምሮ ቢያሳልፍም የሂሳብ ባለሙያ ሆኖ መቀጠሉ ስላልተዋጣልኝ ከልጅነቴ ጀምሮ አልመውና እፈልገው የነበረውን የጋዜጠኝነት ሙያ ለመቀላቀል መንከራተት የየዕለት ተግባሬ ሆነ ይላል፡፡ያኔምደፋር ብዕሩን ስሎ አሰሳውን የጀመረውና በእንግሊዝኛ ቋንቋ አርቲክሎችን እየዘጋጀ ለዴይሊ-ሞኒተር እና ዘ-ሪፖርተር ጋዜጦች ማቅረብ መጀመሩ የምኞት ጭላንጭሉን ወገግ አደረገለት፡፡
#ጋዜጠኝነት
እንደምኞትና ፍላጎቱም መንከራተቱ ፍሬ አፍርቶ ሳምንታዊ የቢዝነስ ጋዜጣ በሆነው ፎርቹን ጋዜጣ ላይ በሪፖርተርነት ተቀጥሮ ማገልገል ጀመረ፡፡ምኞትና ህልሙ መሬት እንዲረግጡ ቀዳሚውን ዕድል ያመቻቸለት የፎርቹን ጋዜጣ መስራችና ማኔጂንግ ኤዲተር የሆነው አቶ ታምራት ሀይለ ጊዮርጊስ በቃለየሱስ የህይወት ጉዞ ውስጥ ትልቅ ዋጋ አለው፡፡የጋዜጠኝነት ሀ ሁን ከማስቆጠር ጀምሮ ከዚያም ባሻገር አንደ ዓለም ባንክ፣የአሜሪካ ኤምባሲና ብሪቲሽ ካውንስል ያሉ ተቋማት በሚያዘጋጁት የሚዲያ ስልጠናዎች ላይ ተሳታፊ እንድሆን ዕድሉን ከማመቻቸት አልፎ ጠንካራ የጋዜጠኝነት ሰብዕናን እንድላበስ ያደረገኝ ባለውለታዬ ታምራት ነው ይላል ቃለየሱስ፡፡
#ወትሮም ለጋዜጠኝነት ታላቅ ጉጉት የነበረው ቃለየሱስ ዜና እንዴት ይፃፋል፣የዜና ግብዓቶች እንዴት ይሰበሰባሉ፣የዜና አስተማማኝ ምንጮችን እንዴት ማዳበር ይቻላል፣ፊቸር አርቲክል እንዴት ይፃፋል የሚሉና ሌሎችም ስልጠናዎችን አግኝቶ በብዕሩ መጠንከር የቻለው በፎርቹን ጋዜጣ ቆይታው እንደሆነ ያስታውሳል፡፡መች ይሄ ብቻ ከሀገር ውጪም በዓለም አቀፍ የአየር ትራንስፖርት በኤር ባስ አማካኝነት ከበረራና የበረራ ደህንነት መረጃ አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ስልጠናዎችን በስፋት በመውሰድ የማረጋገጫ ሰርቲፊኬቶችን ተቀብሏል፡፡
#ቃለየሱስ ባለውለታዎቼ ብዙ ናቸው ይላል፡፡የፎርቹን ጋዜጣ ኤዲተር የነበሩት መላኩ ደምሴና ይበቃል ጌታሁን በጋዜጠኝነት ሥነ ምግባር ኮትኩተው ለውጤት አብቅተውኛል ካለ በኋላ በአጠቃላይ የፎርቹን ኤዲተሮች እኔን ጠፍጥፈው ሠርተውኛል ብል ማጋነን አይሆንም በሚል ያለፈበትን የጋዜጠኝነት ህይወት በአጭሩ ገልፆታል፡፡
#ከፎርቹን የሁለት ዓመታት ቆይታ በኋላ ሪፖርተር ጋዜጣን በመቀላቀል ለ18 ዓመታት ከከፍተኛ ሪፖርተርነት እስከ ኤዲተርነት ያገለገለው ቃለየሱስ ከሪፖርተር ጋዜጣ መሥራች አቶ አማረ አረጋዊ ጋር መሥራት መታደል ነው ይላል፡፡ከአቶ አማረ ጋዜጠኝነትን ብቻ ሳይሆን የአገር ፍቅርና ብሔራዊ ጥቅምን (National Interest)፣ደግነትንና ለሠራተኞቹ ያለውን ፍቅርና አክብሮት እንዲሁም ለጋዜጠኞች የሙያ ነፃነት ሰጥቶ ሠርቶ የሚያሠራበትን መልካም ትምህርት ቀስሜያለሁ ብሏል፡፡በሪፖርተር ሳለሁም በርካታ የሙያ ማሻሻያዎችንና የአጭር ጊዜ ሥልጠናዎችን በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገሮች አግኝቻለሁ በማለት ትናንቱን ያመሰግናል፡፡
#በዘ -ሪፖርተር እንግሊዝኛ ጋዜጣ የማቀርባቸው ዘገባዎቼ በአብዛኛው ቢዝነስ ተኮር ነበሩ የሚለው ቃለየሱስ በተለይ በአቪዬሽንና በማዕድን ዘርፎች ላይ አተኩር ስለነበር፤በእነዚህ ዙሪያ በሚሠሩ የውጭ መጽሔቶች ለእኛም ጻፍልን የሚሉ ጥያቄዎች ቀርበውልኝ እ.ኤ.አ. ከ2006 ጀምሮ ኤርላይን ፍሊት ማኔጅመንት፣ወርልድ ኤር ኒውስ፣ኤርላይን ኢኮኖሚክስ፣አፍሪካን ኤሮስፔስና ዓረቢያን ኤሮስፔስ፣አቪዬሽን ኢንተርናሽናል ኒውስ፣አፍሪካን ቢዝነስ እና አፍሪካን ማይኒንግ ጆርናል ለተባሉ መጽሔቶች በፍሪላንስነት ለረዥም ዓመታት ሠርቻለሁ ይላል፡፡
እ.ኤ.አ.በ2008 በእንግሊዝ አገር በሚካሄድ “Best Aerospace Journalist of the Year” ሽልማት ታጭቼና ለንደን ተጋብዤ ዋናውን ሽልማት ባላሸንፍም፣"How Safe Are African Airlines?" በሚል ርዕስ በኤርላይን ፍሊት መጽሔት ላይ ያሳተምኩት ጽሑፍ ከ500 ለውድድር ከቀረቡ ጽሑፎች አምስቱ ምርጥ ውስጥ ለመግባት በመቻሉ፣ሰርተፊኬት ተበርክቶልኛል ብሏል፡፡
#በ2007 ዓ.ም. በትግራይ ሽመልባ የኤርትራ ስደተኞች መጠለያ ካምፕ ጉብኝት በማድረግ፣ ስለኤርትራዊያን ስደተኞች አሳዛኝ ሕይወት "The Woes of Eritrean Refugees” በሚል ርዕስ በዘ- ሪፖርተር ጋዜጣ ያሳተምኩት ሰፊ ጽሑፍ ጄኔቭ በሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር (UNHCR) ዋና መሥሪያ ቤት ተመርጦ፣ለረዥም ጊዜ በድረ ገጻቸው ላይ ለንባብ ተቀምጦ ነበር፡፡በሻሸመኔ መልካ ኦዳ ስለሚገኙ የራስ ተፈሪያን ማኅበረሰቦች በቦታው ተገኝቼ የሠራሁት "The Plight of Rastafarians in Ethiopia" ዘገባ ከራስ ተፈሪያን ማኅረሰብ ምሥጋናና ዕውቅና አስገኝቶልኛል ይላል፡፡
ቃለየሱስን አንባቢያን የሚያውቁት ስለኢትዮጵያ አየር መንገድና በሀገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች ስለሚካሄዱ የማዕድንና የነዳጅ ፍለጋዎች ተከታታይ በርካታ ዜናዎችን በሪፖርተር ጋዜጣ ላይ በመሥራቱ ነው፡፡ ከዚያ ባለፈም ከተለያዩ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎችና ጋዜጠኞች ጋር የመሥራት ዕድሉን አግኝቷል፡፡
#የተለያዩ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ለሥራ ወደ ኢትዮጵያ በሚመጡበት ወቅትም እነሱን በማገዝ የተለያዩ ሥራዎችን ከውኗል፡፡ከእነዚህም መካከል “CNN, Aljazeera, SKY News, The Economics, National Geographic, Los Angeles Times, News Week, New York Times, Christian Science Monitor, Chicago Tribune…” እና ሌሎችም ከተሳተፈባቸው ውስጥ ይገኙበታል፡፡
እ.ኤ.አ. በ2019 አደጋ የደረሰበት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላንን በተመለከተ ሲኤንኤን (CNN) በሠራቸው ዘገባዎች ላይ በረዳት ፕሮዲዩሰርነት የሠራ ሲሆን፣በወቅቱ ላበረከተው አስተዋጽኦ ከሲኤንኤን ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ምሥጋና ተችሮታል፡፡በዘገባዎቹ ላይም ሙሉ ስሙን በማስፈር ተገቢውን ዕውቅና ሰጥተውታል፡፡የአሜሪካው አልጄዚራ ኢንግሊሽ ቡድን ስለአውሮፕላን አደጋው ዶክመንተሪ ለማዘጋጀት አደጋው ከደረሰ ከአንድ ዓመት በኋላ ወደ ኢትዮጵያ በመጣበት ወቅትም፣አብሮ የአገር ውስጥ ፕሮዲዩሰር (Local Producer) ሆኖ ሠርቷል፡፡
መቼ ይሄ ብቻ ቃለየሱስ የ”Fault Lines” ፕሮግራም አዘጋጅ ከሆነው ጆሽ ረሺንግ (Josh Rushing) እና ፕሮዲዩሰሯ ካቢታ ቺኩሩ ጋር የሠሩት ዶክመንተሪ የተለያዩ አህጉሮችን የሸፈነ ሲሆን፣ለኤሚ አዋርድ ዕጩ ሆኖ ቀርቦም ነበር፡፡
#ከ18 ዓመታት አገልግሎት በኃላ እ.ኤ.አ. በ2020 ሪፖርተር ጋዜጣን ተሰናብቶ ኦሪጅንስ ሚዲያን በማቌቋምና ከኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ሬዲዮ ጣቢያ የአየር ሰዓት በመውሰድ፣‹‹ኢትዮ የንግድና የኢንቨስትመንት መድረክ››የተሰኘ ፕሮግራም በሳምንት ለሁለት ቀናት እያዘጋጀ ለሦስት ዓመታት ያህል አቅርቧል፡፡ኦሪጅንስ የሚል የጉዞ (Travel Magazine) ለማሳተም እየንቀሳቀሰ የነበረ ቢሆንም፣በኮቪድ ወረርሽኝና በሰሜኑ የአገራችን ክፍል በተቀሰቀሰው ጦርነት ምክንያት ለፍሬ ሊበቃለት እንዳልቻለ በቁጭት ያስታውሳል፡፡
#ገጠመኞቹ
#ቃለየሱስ በጋዜጠኝነት ሙያ የገጠሙኝ ፈተናዎች ብዙ ናቸው ይላል፡፡ሙያው ራሱ የሚያስደስት ነገር እንዳለው ሁሉ ብዙ የሚያስጨንቁና የሚከብዱ ነገሮችም አሉት።ጋዜጠኛው ከህሊናው ጋር ተሟግቶና ሚዛኑን ጠብቆ የሚሰራው ነገር አንዱ ሲሆን።ዘገባን ወቅት ጠብቆ መስራትም የራሱ ፈተና አለው። ሚዛናዊነቱ ሳይጓደልም እንኳን ስለአንድ ነገር ሲፃፍ ወይም ሲዘገብ በዜናው ምከንያት የሚጠቀሙ ወገኖች ሊኖሩ ይችላሉ።
ወዲህ ደግሞ ጉዳቱም የዛን ያህል ነው።አንድ ሚዲያ በሚሰራው ዘገባ ባለስልጣንም ሆነ ካምፖኒ ሊሆን ይችላል የነበረውን አቅም ሊያጣ ይችላል።ይህ የሚዲያ ባህሪ ነው።ፈተናዎቹ የበዙ ቢሆኑም ጋዜጠኛው ሲፅፍ ሚዛናዊነት የተለበሰ መሆን አለበት ባይ ነው ቃለየሱስ።
#ቃለየሱስ ረጅም ዓመት የሠራው ህትመት ሚዲያ ላይ ነው።በአንድ ወቅት ከቺጋጎ ትሪቡን ጋዜጠኛ ጋር ወደ ትግራይ በማቅናት በኢትዮ ኤርትራ ስላለው ሁኔታ ለመዘገብ አመሩ፡፡ሽሬ አካባቢ ሽመልባ የሚባል የኤርትራ ስደተኞች ያሉበትን ስፍራ ጎብኝተውና አነጋግረዋቸው ወደ ሽራሮ ሄዱ፡፡የጦርነቱ ከተማ ወደነበረችው ባድመ ሄደውም ነዋሪዎችን፣አርሶ አደሮችና የከተማውን አስተዳደር ቃኝተውና ቃለመጠይቅ አድርገው ወደ ኤርትራ ድንበር ተጠጉ፡፡
#የኤርትራን መሬት ከወንዝ ባሻገር እያዩና የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አባላት ሲያስጎበኟቸው የተቀበሩ ፈንጂዎች ስለነበሩ በተባበሩት መንግስታት የሰላም አስከባሪ ሀይል አማካኝነት የፈንጂ ማስወገድ ስራው እየተሰራ ስለነበር የምንረግጠውን መንገድ ጠቆሙን ካለ በኋላ ቀይ ቀይ የተደረገባቸውን ድንጋዮች አሳይተውን ለእግር ፉካ የምትሆን ድንጋይ አሳዩን።ቀይ ምልክት የተደረገባቸውን ድንጋዮች ትተን ሌላ ከረገጥን ልንሞት እንደምንችል ነገሩን።በፈንጂ መሀከል በጭንቅና በዝግታ ያሳለፍንውን ምንጊዜም አልረሳውም ይላል ቃለየሱስ።
ሌላ ጊዜ ደግሞ በአቬየሽን፣በነዳጅ እና ማዕድን ፍለጋ ስራዎች ዙሪያ ለመዘገብ ወደ ሱማሌ ክልል ይሄዳል፡፡ከኦጋዴን ነፃ አውጪ ጋር የነበሩ ውጊያዎች ስለነበሩ አንድ ጊዜ አቦሌ ከሚባል በደቡብ ምዕራብ በሚገኝ ኩባንያ የነዳጅ ስራ ፍለጋ በሚያደረግ ካምፕ ላይ ታጣቂዎቹ ጥቃት ሰንዝረው 9 ቻይናውያን እና ወደ 65 የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን ህይወት ያልፋል።
ያንን ለመዘገብ ወደ አካባቢው የሄደው ቃለየሱስ ከቺጋጎ ትሪቡን ጋዜጠኛው ፖልስ አሎቤ ጋር ያለ እንቅልፍ ረጅም ቀናት በማሳለፋቸው በሀሩራማው ኦጋዴን ውስጥ ለረጅም ሰአታት ራሱን ስቶ ወደ ሆስፒታል ተወስዶ በህክምና የነቃበትን ጊዜም ያስታውሳል።ቃለየሱስ ገጠመኞቹ የትየለሌ ናቸው፡፡በችሎት ዘገባ እንዲሁም ጋምቤላ ለዘገባ ሄዶ ያጋጠሙትንም ሁሌ እያስታወሰ ይገረምባቸዋል፡፡ በተለያዩ የአቪዬሽን ስብሰባዎችና እንዲሁም በአውሮፕላን አምራች ካምፓኒዎች በአካል እየተገኘም የሚያማልሉ ዘገባዎችን አስነብቧል፡፡
#ስለ ቃለየሱስ የታላላቅ ሰዎች ምስክርነቶች
"ቃለ ኢየሱስ በቀለ ሪፖርተር ጋዜጣ ላይ በትጋት ከሠሩ ባለሙያዎች አንዱ ነው።" ይላል የሪፖርተር ጋዜጣ መስራች አማረ አረጋዊ። ምስክርነቱንም በመቀጠል፦
"... ቃለ ኢየሱስ በአቬሽን እና በማዕድን ዘገባዎች ላይ ያተኩር እንጁ የተሰጠውን ደስ ብሎት የሚሠራ ጋዜጠኛ ነው። የጋዜጠኝነት የሥነ ምግባር ደንብን አውቆ የሚተገብር ባለሙያ ነው። ፕሮፌሽናሊዝም እንዲሰፍን የሚታገል ጠንቃቃ ባለሙያ መሆኑን መመስከር እወዳለሁ።" በማለት ገልጿል
፨፨፨፨፨፨ ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
#የአቶ ግርማ ዋቄ ምስክርነት
#ቃለ ኢየሱስ በቀለን ረጅም ጊዜ አውቀዋለሁ። ለአቬሽን የተለየ ፍቅር አለው። አለምአቀፍ ኮንፈረንሶች ላይ ንቁ ተሳትፎ ያደርጋል። ከዚያም በዕውቀት ላይ የተመሠረተ ፅሁፍ ያቀርባል።ብስለቱ ይደንቃል። ከሌሎች የስሚ ስሚ ሰምቶ ሳይሆን አንድን ጉዳይ ከስር ከመሠረቱ አውቆ የመዘገብ ችሎታውን አደንቅለታለሁ። ስለ አፍሪካ አየር መንገድ ፣ ስለ ኢትዮጵያ አየር መንገድ በወጉ ተረድቶ ስለሚፅፍም ፅሑፉ ተነባቢ ለመሆን ችሏል። ኢትዮጵያ ውስጥ አቬሽን ጋዜጠኝነት በጥልቀት ሲሠሪ የማውቀው እርሱን ነው።ሌሎችም አሉ። እርሱ ግን ከፍ አድርጎ በልህቀት የሚሠራ በመሆኑ ይለያል።
ገና አየር መንገድ ሲመጣ መረጃ ለማግኘት ፍላጎት ያሳያል። ዕውነትን ለማግኘት ይጎለጉላል። አፍሪካም ውስጥ ፈጠን ብሎ አቬሽን ጋዜጠኝነት ላይ የገባ በመሆኑ ይህም ግንባር ቀደም ያደርገዋል። ቃለኢየሱስ ካለበት ካናዳ ሆኖ የአቬሽን ጋዜጠኝነትን ሙያ እንዲያሳድግ ምክሬን እለግሰዋለሁ።
አቶ ግርማ ዋቄ
የቀድሞ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
‹‹እኔ ቃለየሱስ በቀለን የማውቀው ከ1993 ዓ.ም. ጀምሮ ለሁለት ዓመታት ፎርቹን ጋዜጣ አብረን ስንሠራ ጀምሮ ነው›› የሚለው የሪፖርተር ጋዜጣ ማኔጂንግ ኤዲተር የሆነው መላኩ ደምሴ ነው፡፡‹‹ከዚያም በኌላ ለ18 ዓመታት አብረን በሪፖርተር ጋዜጣ ሠርተናል፡፡ከጀማሪ ሪፖርተርነት አንስቶ እስከ አርታኢነት በዘለቀው የሥራ ጉዞው በሚገባ አውቀዋለሁ፡፡በተለይ በአቪዬሽንና በማዕድናት ዘርፍ እጅግ በጣም በርካታ ዘገባዎችን የሠራ ሲሆን፣በሁሉም ሥራዎቹ አንጀት አርስ የሚባል ጋዜጠኛ ነው፡፡ጋዜጠኝነትን ከልቡ ከማፍቀሩ የተነሳ አብረው ለሚሠሩ ጋዜጠኞች ጭምር የሙያውን ፍቅር የማጋባት ችሎታ ያለው ነው፡፡ቃለየሱስ ዘገባዎችን ሲሠራ የሁሉንም ባለጉዳዮች ደምፅ ከማካተት በተጨማሪ፣አንባቢያን ለርዕሰ ጉዳዩ ቅርበት እንዲፈጥሩ የሚያስችል ስሜትን የተካነ ነው፡፡
‹‹ኢትዮጵያ ውስጥ በተለይ በአቪዬሽን ዘገባ በግንባር ቀደምነትነት የሚጠቀስ ጋዜጠኛ ማነው ቢባል በመጀመሪያው ረድፍ ላይ የሚገኘው ቃለየሱስ ነው፡፡በዓለም ላይ አሉ የሚባሉ አውሮፕላን አምራች ኩባንያዎችን፣አየር መንገዶችን፣በአቪዬሽን ዘርፍ ውስጥ የተሰማሩ የሥራ ኃላፊዎችንና ባለሙያዎችን ሳይቀር በተለያዩ አገሮች በማግኘት በሪፖርቶቹ ውስጥ ድምፃቸውን ከማካተቱም በላይ በቃለ ምልልስ ጭምር ለአንባቢያን ተደራሽ በማድረግም ወደር የለውም፡፡የአውሮፕላን አደጋዎች ሲያጋጥሙም ሆነ የተለዩ ክስተቶች ሲኖሩ ከሚሠራቸው ዘገባዎች በተጨማሪ፣በተለያዩ ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ለማብራሪያ የሚፈለገው ቃለየሱስ ነው፡፡በውጭ ለሚዘጋጁና ቁጥራቸው ቀላል ለማይባል የአቪዬሽን መጽሔቶች በርካታ ዘገባዎችን በመሥራትም ታዋቂ ነው፡፡
‹‹በማዕድናት ዘርፍም ከካሉብ ነዳጅ የጀመረው የጋዜጠኝነት ህይወቱ በተለያዩ ክልሎች የሚደረጉ የነዳጅ፣የወርቅ፣የብረት፣የፖታሽ፣የታንታለም፣የኦፓልና ሌሎች የከበሩ ማዕድናት ፍለጋ ሥራዎችን በስፋት የዳሰሰ ነው፡፡በኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ ግንባታዎች፣በጂኦ ተርማል ፕሮጀክቶች፣ በፀሐይና በንፋስ ኃይል ማመንጫዎች፣በሲሚንቶና በሌሎች የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴዎችም ሰፋፊ ዘገባዎችን በማበርከት ስመጥር ሆኖ ዘልቌል፡፡በፖለቲካው መስክ ደግሞ በተለያዩ አገራዊ ምርጫዎች ከአዲስ አበባ ውጪ በክልሎች ተሰማርቶ አመርቂ ሪፖርቶችን በማቅረብ ችሎታውን ማስመስከር የቻለ ነው፡፡ከሪፖርተር በገዛ ፈቃዱ ከተሰናበተ በኃላም በኤፍኤም 107.8 ሬዲዮ ጣቢያ የአየር ሰዓት ወስዶ ያቀርባቸው የነበሩ የቢዝነስ ፕሮግራሞቹ፣የቃለየሱስን ችሎታ ከጋዜጣ አንባቢያን ወደ ሬዲዮ አድማጮች በማዝለቅ ረገድ ትልቅ ግምት የሚሰጣቸው ነበሩ፡፡
‹‹ቃለየሱስ ግልጽ፣ ቅን፣ ሰብዓዊነትን የሚያስቀድም፣ኃላፊነት የሚሰማው፣ በአስገራሚ ትውስታው የረሳናቸውን ጉዳዮች የማስታወስ ችሎታ ያለው፣በቀልድም ሆነ በቁምነገር የሚታወቅ፣ ከማንኛውም ሰው ጋር ወዳጅነት ለመፍጠር ምንጊዜም ዝግጁ የሆነ፣በተለይ በሪፖርተር የሥራ ባልደረቦቹ ዘንድ በእጅጉ ተወዳጅና ምሥጉን ጋዜጠኛ ነው፡፡በተጨማሪም በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ በሚሰጣቸው ሰፊና ጥልቅ ትንተናዎቹ የሚታወቅ ሲሆን፣ብዙዎችም በዚህ መጠን ለነገሮች ትኩረት ሰጥቶ የማስረዳት ብቃቱን በአድናቆት የሚመሰክሩለት ነው፡፡እኔም ከሁለት አሠርት ዓመታት በላይ አብሬው ስለሠራሁ ችሎታውን በዚህ መጠን ስገልጽ በከፍተኛ ስሜት ሲሆን፣ይህንን ከመሰለ ብርቱና ታታሪ ጋዜጠኛ ጋር የመሥራት ዕድል በማግኘቴ በእጅጉ ደስተኛ ነኝ›› በማለት መላኩ ምስክርነቱን አጠቃሏል፡፡
ካፒቴን ሰሎሞን ግዛው ስለ ቃለየሱስ በሰጡት ምሥክርነት ‹‹እኔ እሱን ለአየር መንገዱ ልዩ እንደ ሆነ ሰው አየዋለሁ።በጣም ትሁት፣አዳማጭ የሆነ ሰው ነው።ከየት እንዳመጣው ባላውቅም ልዩ የሆነ የኢንግሊዘኛ ፀሀፊ ነበር።በሁለት ምክንያት የሱን ፅሁፍ አነብ ነበር፡፡አንዱ በፅሁፉ ለመደሰትና እንደ ግጥም ስለምወደው ነው።ሌላው ከእውቀቱ ወይም አንብቦም ይሁን ባላውቅም የፅሁፎቹ ይዘት በሚያውቀው ነገር ላይ የተመሰረተ በመሆኑ ነው።በዚህም በጣም አበረታታዋለሁ።
‹‹ከተዋወቅን 15 ዓመታት ሆኖናል።በውጪ ህትመቶች ላይ የሚያወጣቸው ስራዎች ቃለየሱስ ብሎ ስሙ ይገለፅ ይሆናል እንጂ ማንም ነጭ የሚፅፈው አይነት ፅሁፍ ነው።የፅሁፉ ይዘትና አያያዝ ደረጃውን የጠበቀ ነው።የሚፅፍባቸው መፅሄቶች ደረጃቸውን የጠበቁና ትላልቅ ናቸው።ነገር ግን ደረጃቸውን ጠብቀዋል የሚባሉትም አንዳንዴ ትርኪምርኪ ሲፅፉም ይታያል።ግን የሱ ፅሁፍ በጣም የሚያኮራ ነው።ሌላው ዜግነቱን የሚወድ ሰው ነው።ተጨባጭ በሆነ መልኩ ለኢትዮጵያ አየርመንገድ በቦታው ካሉት ህዝብ ግንኙነቶች እሱ ብዙ የሰራ ይመስለኛል።እውቅናና ሽልማት ሊሰጠው በርታ ሊባል የሚገባው ልጅ ነው።ወገቡን ይዞ ነበር ለአየር መንገዱ ይሰራ የነበረው።አሁንም ቢሆን ባለበት ሆኖ ለአየርመንገዱ ነገሮችን መስመር የሚያሲዝ ሰው ነው››ብለዋል፡፡
፨፨፨፨፨፨፨
የቀድሞ የሲቪል አቬሽን ዋና ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ወሰንየለህ ሁነኛው በበኩላቸው ‹‹ከተዋወቅን ከ7 ዓመት በላይ ይሆነናል።እኔ ከማቃቸው የሚዲያ ሰዎች በጋዜጠኝነት የሱን ያህል ብዙም አቬሽን ዘርፉ ላይ ገብቶ እያንዳንዱን ነገር አይቶ የኢትዮጵያ አየር መንገድም ይሁን የግል ኦፕሬተሮቹም ጋር እንደሱ የሚፅፍ አላየሁም።እሱ ነው የተሻለ ጠይቆ አንብቦ ተረድቶ አስተዋጽዖ ለማድረግ የሚጥረው።በዛ ወቅት ቃለ እየሱስ ጥሩ ዘጋቢ ነበር።ብዙ መፅሄቶች ላይ ይሳተፋል አንዳንድ አለም አቀፍ ስብሰባዎች ላይ ይሄዳል። በኢትዮጵያ አየርመንገድና በሲቪል አቬየሽን ላይ የተለየ እውቀት ያለው ነው።ምክንያቱም በየእለቱ ስለሚከታተል ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን አቬየሽን ኢንዱስትሪ በደንብ ያውቀው ነበርና ነው።
‹‹አቬየሽን ኢንዱስትሪው በእነዚህ መፅሄቶች በብዙ መንገድ ይጠቀማል።ህብረተሰቡ አቬየሽኑም ሆነ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ራሱን ከማስተዋወቁ በላይ ምን ላይ እንዳለ እና በተለየ አካል እንዲሰራለት ትክክለኛነቱን ይረጋገጣል።እንዲሁም ምን ያህል የግል ኦፕሬተሮች ምን ያህል በኢኮኖሚው ይሳተፋሉ የሚለውንም ለህብረተሰቡም ለመንግስትም መረጃ ይሰጣል።ስራዎቹ ለብዙ ነገሮች የመረጃ ምንጮች ሆነው ያገለግላሉ ።
‹‹ቃለእየሱስ በዚያ ወቅት የሚያደርገው የኢትዮጵያን አቬየሽን ኢንዱስትሪ ከሌላው እያነፃፀረ በሚያውቀው ልክ ለህብረተሰቡ ሙሉ መረጃ ይሰጣል።ለግል ኦፕሬተሮችም ለኢትዮጵያ አየር መንገድም ግብዐት የሚሆኑ ብዙ ነገሮችን ያደርጋል።በተዘዋዋሪም ያስተዋውቃል።እውነተኛ መረጃ ሲያቀርብ ሰው ስለ አቬየሽን ኢንዱስትሪ ያለውን እውቀት ያዳብራል።አብዛኛው ሰው ስለ ግል ኦፕሬተር አያውቅም አውሮፕላን አላቸው ወይ ? ብሎ የሚጠይቅም ብዙ ሰው ነው።በዚህ ጉዳይ ላይ በብዛት የሚሰራው ቃለእየሱስ ነበር››ብለዋል፡፡
‹‹በኢትዮጵያ የጉዞና ቱሪዝም ዘርፍ ላይ የቃለየሱስ አስተዋፅኦ ትልቅ ነው።››ብለው ምስክርነታቸውን መስጠት የጀመሩት አቶ ተወልደ ገብረማርያም የቀድሞ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ናቸው፡፡‹‹ቃለየሱስና እኔ ለረጅም ጊዜ እንተዋወቃለን በ«Reporter» ጋዜጣ ሲሰራ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዜናዎችንና እድገቶችን ይዘግብ ነበር።በቀጣይ የአቪዬሽን ዘርፍ ላይ ጥልቅ ፍላጎት አሳየ፤እኛም ከIATA ጋር እንዲገናኝ አደረግነው፣በተለይም በየዓመቱ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚካሄዱ የIATA አመታዊ አጠቃላይ ጉባኤዎች (AGM) ላይ የፕሬስ ኮንፈረንሶች ላይ ይሳተፍ ነበር።
‹‹በአፍሪካ አየር እና አቪየሽን (African Aerospace and Aviation) መጽሔት እና በሌሎች ከአቪየሽን ጋር የተያያዙ መጽሔቶች ላይ ጽሁፎችን ይጽፍ ነበር።በአጋርነትም ብዙ ፕሮጀክቶችን አከናውነናል። እኔም የኢትዮጵያ ቱሪዝም ቦርድ ሊቀመንበር በነበርኩበት ሰዓት፣የራሱን የጉዞና ቱሪዝም መጽሔት እንዲጀምር ወይም እንዲያስብበት ሀሣብ አቀርብለት ነበር፤እርሱም ይህን ሀሳብ በአዎንታ ይመልከተው ነበር።
‹‹በአጠቃላይ፣ ይህ ዘርፍ እስከዛሬም በቂ የሚዲያ ሽፋንና የማስተዋወቂያ መድረክ ስላልነበረው፣ ቃለየሱስ ይህን ክፍተት ልብ ብሎ በማጤን በኢትዮጵያ የጉዞና ቱሪዝም ዘርፍ ልማት ላይ ከፍተኛ ስራ ሰርቷል።በእኔ አመለካከት፣ያበረከተው አስተዋፅኦ አስደናቂ ነው፣ለሥራውም እውቅናና ምስጋና ሊቀርብለት ይገባል››ብለዋል፡፡
ሲጠቃለል ከ15 አመት በላይ በአለም አቀፍ የአቪየሽን ስብሰባዎችን በአሜሪካ፣አውሮፓ፣አፍሪካ፣ መካከሉኛው ምስራቅ እና ኤሽያ ተሳትፌያለሁ 36 ሃገሮችንም የማየት እድል ገጥሞኛል የሚለው የአቪየሺን ባለወርቃማ ብዕሩ ቃለየሱስ በቀለ እ.ኤ.አ.ከ2023 መጨረሻ ጀምሮ ኑሮውን በካናዳ ያደረገ ሲሆን፤ለአፍሪካ ኤሮስፔስና አቪየሽን ኢንተርናሽናል ኒውስ በፍሪላንስነት በማገልገል ላይ ይገኛል፡፡

8 months ago
ሊከተሉት የሚገባ ሰው!
ሠዓሊና ቀራፂ ፕሮፌሰር በቀለ መኮንን
(ሂላሪያ ተስፋዬ እና ዕዝራ እጅጉ ተወዳጅ ሚድያ)
#ፕሮፌሰር በቀለመኮንን ለተወዳጅ ሚድያ የቅርብ ወዳጅና ቤተሰብ ነው። የምንሠራውን የስነዳ ፕሮጀክት በሙሉ ልብና መንፈስ የሚደግፍ ቀና ምሁር ነው። ታናሾቹን ለማገዝ በቀዳሚነት የሚሰለፍ ኩራት ያልፈጠረበት ታላቅ ወንድም እንደማለት ነው። ከ4 ዓመት አስቀድም "መዝገበ አእምሮ" ቅጽ አንድ ሲዘጋጅ ከጀርባ እና ከጎን ሆኖ ሲረዳን ነበር። የኃይሉ ልመንህን ታሪክ ፕሮፌሰር በቀለ አስታውሶ ታሪኩን ባይነግረን ኖሮ ኃይሉ ልመንህን አናገኘውም። ፕሮፌሰር በቀለ ሌሎችም ስሙን ከአክብሮት ጋር የሚያነሱት የሥነጥበብ ሰው ነው።
#ተወዳጅ ሚድያ እስከዛሬ የ432 ባለሙያዎችን ታሪክ በመፅሐፍ፣ በዲጂታል ሚድያ እና በድምፅ ሲሰንድ ፕሮፌሰር በቀለ መኮንንም እንዲካተት አድርጓል። እስከዛሬ በሚዲያ እና ኪነ-ጥበብ ዘርፍ የሠሩትን በምንችለው አቅም ታሪካቸው ዘመን እንዲሻገር ያደረግን ሲሆን የስነዳ ተግባሩም ተጠናክሮ ቀጥሏል። በቀጣይ እያዘጋጀነው ባለነው ዕትም ከ20 ዘርፎች የተውጣጡ ታላላቆችን በማሰባሰብ ላይ እንገኛለን ። ከእነዚህ ታላላቆች ውስጥ ፕሮፌሰር በቀለ መኮንን አንዱ ነው። የሕይወት ታሪኩንም ብዙ ካልታዩ የልጅነት ምስሎቹ ጋር አንድ ላይ በማድረግ ታሪኩን አጋርቶናል። ዕዝራ እጅጉ እና ሂላሪያ ተስፋዬም ታሪኩን እንደሚከተለው ሰንደውታል።በነገራችን ላይ በዚህ የሕይወት ታሪክ መጣጥፍ ውስጥ ተባባሪ ፕሮፌሰር ቴዎድርስ ገብሬ "በቀለን በብሔራዊ ትእምርት ፍለጋ ውስጥ" ብሎ የጻፈው ረዘም ያለ ምሁራዊ ትንተና አቅርበናል። የፕሮፌሰር በቀለ መምህር ወርቁ ጎሹ የሰጡትንም ምስክርነት አካተናል። መልካም ንባብ።
#የሰባተኛ ክፍል ተማሪ እያለ የስዕል ዝንባሌውን እንዲከተል እንዲሁም የስዕል ትምህርትን እንዲማር ያመለከቱትን መምህሩን በአንደበቱ ቃላት ይስላቸዋል። እኚህ መምህሩን፥ “ሊከተሉት የሚገባ ሰው” ሲል ይገልጻቸዋል። ምንአልባት ከበርካታ ዓመታት በኋላ እርሱ ራሱም እንዲያ ያለ ‘ሊከተሉት የሚገባ’ የጥበብ ሰው ሊሆን እንደሚችል አልገመተ ይሆናል።
#ፍላጎቱ ከእኩዮቹ የተለየ፣ ‘ተርታ’ ለሆነ ነገር መሻት የሌለው፣ በለጋ እድሜው ሳይቀር ነገሮችን እንደሆኑ ማየትና መሥራትን የማይመርጥ፣ አዲስ ነገር መፍጠርን አልያም የነበረውን በአዲስ መልክ መቃኘት ይቀናው የነበረ ተማሪ ነው። ስሙን ሳይቀር በስዕል ይጽፍ እንደነበር ይናገራል። በስጋው ላይ ያሠለጠናት ነፍሱ፥ ሰዓሊ የመሆን ግቡን ለማሳካት ይችል ዘንድ ‘የሰው ልጅ መሠረታዊ ነገሮችን’ አሻግሮ እንዲያይ ጉልበት ሰጥታዋለች። ይህ ጉልበትና ጽናት ነው፣ አሁን በሥነ ጥበብ ዘርፍ በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ሙሉ ፕሮፌሰር የወለደው፥ ሠዓሊና ቀራፂ ፕሮፌሰር በቀለ መኮንን።
#ትውልድና እድገቱ ደብረዘይት (ቢሾፍቱ) ከተማ ነው። ጥር 6 1956 ዓ.ም። ትምህርትን አሃዱ ያለው በቆሎ ትምህርት አቡጊዳ ብሎ ፊደል ቆጥሮ፣ ዳዊት ደግሞ ነው። የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን አፄ ልብነ-ድንግል ወናግሰገድ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ እንዲሁም ኹለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በዚያው ደብረዘይት ልዕልት ተናኘወርቅ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተከታትሏል። የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተናውን የወሰደው ደግሞ በአዲስ አበባ ምኒልክ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ነው።
ከልጅነት እድሜው ጀምሮ የተገዛው ለስዕል ጥበብ ብቻ ሳይሆን በጠቅላላ ለጥበብ ነበር። አዲስ ነገርን አልያም የነበረው በተሻለ መንገድ ሆኖ ማየትን ይመርጣል። በጥበብ ለሚሠራ ነገር ሁሉ ልዩ ፍቅር አለው። አሁን በአዋቂነትና በርቱዕ አንደበቱ ውበት እንደሚገዛው፥ ሰው የማይሠራውን መሥራት አልያም የተሠራውን ነገር ባልተሠራበት መንገድ መሥራት እንደሚወድድ ይናገራል። ይህን ቃሉን በልጅነት እድሜው ሲገልጥ ደግሞ፣ ስሙን ሳይቀር በስዕል ይጽፍ ነበር።
#የተካነበት፣ የሠለጠነበትና የታወቀበት የስዕል እና የቅርጻ ቅርጽ ጥበብ ይሁን እንጂ፥ ለጽሑፍ ጥበብ እና ውበትም ስሱ ነው። በልጅነትና ወጣትነት እድሜው በደብረዘይት ኪነት ውስጥ ቴአትር፣ ግጥም እንዲሁም መፈክር ጭምር በመጻፍ ይታወቃል። እንደውም ለተማሪዎች፣ ለሰፈሩ ወጣቶች የጻፋቸው የፍቅር ብሎም ልዩ ልዩ ደብዳቤዎችና ግጥሞች ጋር በተያያዘ በተለያየ አጋጣሚ የሚያነሳቸው ገጠመኞቹ ጥቂት አይደሉም። የእጅ ጽሑፉን ብቻ ሳይሆን የሚጽፋቸው ጽሑፎችና ግጥሞች ይዘት ጭምር ነበር ብዙዎችን የሚስበው።
#በኋላ 12ኛ ክፍል ፈተናን ከመውሰዱ አስቀድሞ፥ የስዕል ትምህርትን ለመማርና መምህሩ የዘራበትን ዘር ለማፍራት ዝንባሌውን ተከትሎ በዘመኑ አዲስ አበባ የሥነ ጥበብ ትምህርት ቤት (አሁን አለ ሥነ ጥበብና ዲዛይን ትምህርት ቤት) አቀና። ትምህርት ቤቱን ለመቀላቀል ደጅ ጥናትና ምልልስ እንዲሁም ተማጽኖ አስፈልጎታል። በኋላም ተሳክቶለት ተማሪ ለመሆን በሚጠበቀው ፈተና አንድ ሺህ ከሚጠጉ ተወዳዳሪዎች መካከል ከ14 አላፊ ተማሪዎች አንዱ መሆን ቻለ።በ1971።
#በአንድ ወቅት በአራዳ ኤፍኤም አዲስ አራዳ የራድዮ ፕሮግራም ላይ ባደረገው ቆይታ፣ የዚያን የአምስት ዓመት የትምህርት ዘመን ሲያነሳ፥ በትምህርት ቤቱ የነበረው የ5 ዓመት ቆይታ ቀላል እንዳልነበር ያስታውሳል። ሌሊት ማረፊያ የሚያጣባቸው ቀናት ብዙ ናቸው። ምንም እንኳ ለአምስት ዓመታት እያንዳንዱ ቀን የአንድ ዓመት ያህል ከባድ የነበር ቢሆንም፥ እርሱ ግን ‘ቀኑን ጎበዝ መሆን ነበር የሚፈልገው’። እናም ቀኑን ጎብዞ ከባዱን ጊዜ በብልሃትና በጽናት ተወጣው። ትምህርቱን አጠናቅቆም በማዕረግ ተመረቀና እዚያው የተማረበት ትምህርት ቤት መምህር ሆኖ ተቀጠረ።
በተማረበት ትምህርት ቤት በወጣት መምህርነት ለአራት ዓመታት አገልግሏል። ከዚያ በኋላ፥ ወደ ሩሲያ ለከፍተኛ ትምህርት ተላከና ሞስኮ ከተመ። ‘ግራጫ’ ይለዋል፣ የሩስያን ፀሐይ አልባ ቀዝቃዛና ደመናማ የጨላለመ የዘመኑን ድባብ። በዙሪያው ውበትን ማሰስ የለመደ ዐይኑ በሞስኮ ያንን ሊያገኝ አልቻለም። እንዲያም ሆኖ የደከመለት ትምህርቱን ለመፈጸም ጽናትን በመምረጥ፥ ከስድስት ዓመት የሞስኮ ቆይታ በኋላ የከፍተኛ የሥነጥበብ ትምህርቱን በሚገባ አጠናቅቆ ወደ እናት ሀገሩ ኢትዮጵያ ተመለሰ።
ከሩስያ መልስ አስቀድሞ በመምህርነት ያገለግልበት በነበረው ሥነ -ጥበብ ትምህርት ቤት የማስተማር እድል አገኘ። በዚያም በመጀመሪያ በሥነ ጥበብ ታሪክ ከዚያም በንድፍ ጥናት መምህር ሆኖ ቆይቷል። በመምህርነት ብቻም አይደለ፥ በጊዜው ‘አርት ስኩል’ ይባል የነበረውን ይህን ትምህርት ቤት፣ ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋምነት ለማሳደግ ከ1990ዎቹ ጀምሮ ለዓመታት በዘለቀውና በተደረገው እልህ አስጨራሽ ትግል ውስጥ ከፊት ሆነው ሲያስተባብሩ ከነበሩት መካከል ሆኗል። በመጨረሻም ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ በተሰጠ የጥናት ውሳኔ ሥነ ጥበብ ትምህርት ቤቱ ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተዛውሮ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ሲሆን ትልቁን ድርሻ ከተወጡት ጥቂት ግለሰቦች መካከል ፕሮፌሰር በቀለ መኮንን ተጠቃሽ ነው።
ትምህርት ቤቱ የዩኒቨርሲቲው አንድ አካል ክፍል ከሆነ በኋላ የመጀመሪያው ዳይሬክተር በመሆን ሠርቷል። በዚያም ወቅት የትምህርት ቤቱን ነባር ስርዓት የከፍተኛ ትምህርት ስርአት ቅርፅ ለማስያዝ በብርቱ ለፍቷል፣ አሳክቷልም። በ2009 ዓ.ም ገደማ የሥነጥበባት ኮሌጅ ሲመሠረት በድጋሚ የትምህርት ቤቱ ዳይሬክተር ሆኖ ከማገልገሉ ባሻገር፥ ትምህርት ቤቱ መጠሪያው ወደ አለ የሥነ ጥበብና ዲዛይን ትምህርት ቤት የተቀየረው የኮሌጁ ዲን ሆኖ ባገለገለበት ዘመን ነበር። ከዚያም ባሻገር አዲስና ተጨማሪ የፊልም ትምህርት ክፍል እንዲቋቋም ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ትምህርት ክፍሉ እውን እንዲሆን አስችሏል። ከዚህም ባሻገር በማስተማርና በማማከር በርካታ ተማሪዎችን ያፈራ ብርቱ ባለሙያ ነው።
#ፕሮፌሰር በቀለ በብሉይ ወይም ክላሲክ አካዳሚ ትምህርቱን ጠንቅቆ የተማረ ይሁን እንጂ በዘመነኛ የሥነ ጥበብ እንቅስቃሴ በኢትዮጵያና በአፍሪካ ከሚጠቀሱ ባለሙያዎች አንዱ ነው። አዳዲስ ሙከራዎችና አሰሳዎችን በድፍረት ግን በኃላፊነት በማከናወን ሁሌም ፈር ቀዳጅና አዲስ መንገድ የሚያሳይ ከልቡ የፈጠራ ሰው ስለመሆኑም ብዙዎች ይመሰክራሉ፥ ከዚያም በላይ ሥራዎቹ ምስክሮቹ ናቸው።
#ፕሮፌሰር በቀለ የመጀመሪያ የሥዕል ኤግዚቢሽኑን ያቀረበው ከሀገር ውጭ ፊንላንድ፥ ‘ኮ’ፕዮ’ የሚባል ዩኒቨርሲቲ (Kuopio - በአሁኑ ምሥራቅ ፊንላንድ ዩኒቨርሲቲ) ነበር። ይህም በሞስኮ የሥነጥበባት የመጨረሻ ዓመት ተማሪ እያለ ሲሆን፣ ለዕይታ ያቀረባቸው ሥራዎቹም የተለያዩ አስቀድሞ በትምህርት ቤት ቆይታው ያዘጋጃቸው ናቸው።
ከዚያ በኋላ ለቁጥር በርካታ፣ ለዓይነት ብዙ፣ ለዐይን ውብና አስደማሚ የሆኑ ሥራዎችን ያለማቋረጠ ለበርካታ ዓመታት ሲያቀርብ ቆይቷል። ከስዕል ኤግዚቢሽን እስከ አደባባይ ሐውልቶችና ዓለም አቀፍ መድረኮች፥ በቀለ መኮንን የሚለው ስም እንግዳ ሆኖ አያውቅም።
#በ1996 ዓ.ም ያቀረበው ‘እንቆቅልሽ’ የተሰኘ የ‘ኢንስታሌሽን ጥበብ’ ትርዒቱ ዘይቤያዊ (Methaphorical) ትርጉም የያዘና አሁንም ድረስ አነጋጋሪ ሆኖ የቆየ ሥራ አንዱ ተጠቃሽ ነው። በ2000 ዓ.ም ‘እድልና ምርጫ’ የሚል ‘ክሪቲካል’ ትርዒቱን አቅርቦ ተመልካቹን አስደምሟል። በ2010 ዓ.ም ‘ባሩድና ብርጉድ’ ሲል የሰየመው አነጋጋሪና አወያይ ኤግዚቢሽኑ፥ ተመልካቹ ስለ ሥነጥበብ ያለውን አመለካከት ደጋግሞ እንዲፈትሽ ያስገደደ ነበር።
በ2016 ዓ.ም በኢትዮጵያውያን የሕይወት ዘይቤ ላይ ትልቅ ጥያቄ አንስቶ ያወያየውንና እስከ አሁንም የሚያወያየውን “ግሉተን ፍሪ-ደም” ወይም ‘ጤፍና ነፃነት’ የተሰኘውን ልዩ ትርዒት አቅርቦ የሥነ ጥበብ ተመልካቾችን ማስደነቁና ማነጋገሩን ቀጠለበት።
ከ25 ዓመታት በላይ እነዚህን የፈጠራ ሥራዎቹን በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር በተለያዩ መድረኮች ሲያሳይ ቆይቷል። በአፍሪካ፣ በአውሮፓ እና በአሜሪካ፣ በተለያዩ ሙዚየሞች ሥራዎቹን አቅርቧል፣ ሐሳብና ዕይታውን አስደምጧል። ሀገሩን አልፎም አኅጉሩን አፍሪካን በዓለም መድረክ በዘርፉ በኩራት እንዲቆሙም ምክንያት ሆኗል።
#በቅርብ ማለትም ባለፈው 2017 ዓ.ም፥ በኢጣሊያ ቱሪን ከተማ ሮያል ፓላስ ሙዚየም ተጋብዞ ‘ዘ ስሞኪንግ ቴብል’ ወይም ‘የሚጤሰው ጠረጴዛ’ የተሰኘ ፀረ ቅኝ ግዛት ይዘት ያለው ዘመነኛ የሥነ ጥበብ ሥራ በመፍጠር ለዕይታ አቅርቧል። ይህም ከፍተኛ እድናቆትን ያስገኘለት ብሎም ሐሳቡን ያስደመጠበት አውድ መሆን ችሏል።
#መሥራት እንጂ ይህን ሠራሁ ብሎ መናገርን የማያዘወትረው ፕሮፌሰር በቀለ፣ እንዲህ ካሉ አውደ ርዕዮች ባሻገር በቀራጺነቱ የተጠበበባቸው ሥራዎችም እጅግ በርካታ ናቸው። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የሠራቸውን በማማከር የተሳተፈባቸውን ብቻ ለመጥቀስ፥ በሙሉ ነሃስ የተሠራው የቀዳማይ ኃይለሥላሴ ኪነ ሀውልትን ጨምሮ፥ አብርኆት የሕዝብ ቤተመጻሕፍት ደጃፍ የሚገኘው ኪነ ሀውልት (ከነሐስ ቀልጦ የተሠራው ሕፃን)፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት ያሠራው ሕንጻ ጋር የሚገኘው የባንኩን ዓላማና ርዕይ የሚያሳየው ግዙፍ ኪነ ሀውልት (ሀብት ካለ በሰማይ መንገድ አለ) እጅግ ጥቂቶቹ ናቸው።
ታድያ ለእነዚህና ለበርካታ ሥራዎቹ ሽልማቶችና እውቅናዎች ተበርክተዉለታል። ከእነዚያም መካከል በ1990 ዓ.ም የቺካጎ አርቲስቶች ዓለም አቀፍ ሽልማትን ያሸነፈ ብቸኛው አፍሪካዊ የስነ ጥበብ ባለሙያ መሆን ችሏል። እ.ኤ.አ. በ2006 በአሜሪካ ኒው-ዮርክ ውስጥ የIIE ፕሮግራም የሆነውን የ’Scholar Rescue Fund’ ሲቀበል የመጀመሪያው የሥነ ጥበብ ሰው ነበር። በዚያው ዓመት በባልቲሞር ሜሪላንድ ውስጥ በተጋባዥ ሠዓሊነት በበሜሪላንድ የአርት ኮሌጅ (MICA-Maryland institute college of Art) ለስምንት ወራት ቆይታ አድርጓል።
#ፕሮፌሰር በቀለ የኢትዮጵያ ሚሌኒየም ዓርማ ነዳፊ ሲሆን በመላ ሀገሪቱ በርካታ ኪነ ሀውልቶችን ነድፏል፣ አቅዷል፣ አማክሯል፣ መርቷል፣ ሠርቷል። በርካታ የመጻሕፍት ሽፋኖችንና የውስጥ ምስሎችን አዘጋጅቷል። በሀገር እና በዓለም አቀፍ የሥነጥበብ እና የሥነ ሕንፃ የውድድር መድረኮች ላይ በከፍተኛ ዳኝነት አገልግሏል። ከስነጥበቡ ማኅበረሰብ ውስጥ ደግሞ በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ መደበኛ አባል ነው።
#ከዚህም በላይ ከእለት እለት የማስተማር ተግባሩ ጎን ለጎን በቅርቡ በተባበሩት መንግሥታት ፕሮጀክት ስር ነባሩ የአፍሪካ አዳራሽና የሥነ ጥበብ ሥራዎቹ እድሳት ውስጥ ባለሞያ፣ አማካሪና ተቆጣጣሪ በመሆን የተሳካ ሙያዊ ተልዕኮ ፈፅሟል። በአሁኑ ወቅትም በአለ ሥነጥበብ እና ዲዛይን ትምህርት ቤት የቅድመ እና ድኅረ ምረቃ ፕሮግራም ፕሮፌሰር ሲሆን፣ የዘመናዊ ሥነጥበብ ሙዚየም ገብረ ክርስቶስ ማዕከልንም በመምራት ላይ ይገኛል።
#ኅዳር 4 ቀን 2018 ዓ.ም የአለ የሥነጥበብና ዲዛይን ትምህርት ቤት የቀድሞ ተማሪዎች በትምህርት ቤቱ የአክብሮትና የምስጋና ፕሮግራም አድርገዉለታል። ተማሪዎቹ ያንን ያደረጉት ፕሮፌሰር በቀለ በጀርመን ሀገር ፍራንክፈርት ከተማ ከሚገኝው የሥነጥበብ ዩንቨርሲቲ ጋር ከዓመታት በፊት የተጀመረውን የኹለትዮሽ ግንኙነት ዳር በማድረስ ላደረገው ታላቅ ተግባር እና የትምህርት ቤቱን ዳግም ትንሳኤ ለማሳካት ድልድይ በመሆኑ በማመስገን ነው።
አሁን ታድያ ይህና ያልተነገረ እጅግ በርካታ፣ ውብና አስደናቂ፣ ገና ያልተተነተነና ዐይን የሚሻ ሥራን የሠራ ሰው ነው፥ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አለ የሥነጥበብና ዲዛይን ትምህርት ቤት የመጀመርያው ሙሉ ፕሮፌሰር ማዕረግ የተሰጠው።
#ምንአሉ ?
ይህንን ዜና በደስታ በማኅበራዊ ገጾቻቸው ካጋሪት መካከል ጋዜጠኛ #ቴዎድሮስተክለአረጋይ እንዲህ አለ፥
“አንዳንድ ጊዜ ማዕረግም፣ ሹመትም፣ ሽልማትም በተለያዩ ምክንያትና አጋጣሚዎች ያልተገባ ሰው እጅ ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ። ይህ ይበልጡን በሀገራችን፣ በዓለምም ላይ ታይቷል። ለፕሮፌሰር በቀለ መኮንን ዓይነቱ ደግሞ እንዲህ ግጥም ያለ ፣ በልኩ የተሰፋ ይሆናል። የበቄ ፕሮፌሰርነት በሥነ ጥበብ ዘርፍ የተሰጠ የመጀመሪያው ቢሆንም የሰውየው የበቀለ ብቻ አይደለም። የመጭው ትውልድ ሁሉ ነው። የሥነ ጥበብነት ብቻ ሳይሆን የመቻል ፕሮፌሰርነት ነው። ከእንግዲህ ለአንድ ጥበበኛ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ መሰጠት እንደሚችል ማሳያው፣ ማመላከቻው፣ ዳገቱ፣ ምልክቱ ነው፥ በቀለ መኮንን። ያሉትና የመጭዎቹ የሥነጥበብ ልሂቃን ተስፋና ብርታት ነው። እንደሚቻል ማሳያውም፣ ማረጋገጫውም ሆኗል። ይህ ለሥነጥበቡ ብቻም ሳይሆን ለሙዚቃውም ፣ ለትያትሩም ነው።”
የሙያ አጋሩንናበአለ የሥነ ጥበብ እና ዲዛይን ትምህርት ቤት ዲን #ሠዓሊአገኘሁአዳነ በበኩሉ፥ “የቤት ሰው፣ መምህር፣ ባልደረባ፣ የሞያ አባት… ከፍ ሲል፣ ሲከብር፣ ድካሙ ፍሬ ሲያፈራ ወዘተ. ልብ ይሞላል። በቀለ መኮንን ንጉሡ ባለግዙፍ ሰብዕና፣ ከሰው ፊት የሚያቀረቡት፣ የሚያኮራ፣ ጥንቅቅ ያለ ሙያተኛ፣ በጥረቱ ከጉልበተኞች ቅሚያና ንጥቂያ፣ ከሰሜነኛው ንፍቀ ክበብ (global north) በር ጠባቂነት በጥበብ ሾልኮ በርካታ ዓለማቀፍ መድረኮችን የተጋራ፣ ረብ ያለው ተግባር እየፈጸመ ያለ ሰው የሚሠራበት ተቋም አዲስ አበባ ዮኒቨርስቲ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቶታል። የአለ የሥነጥበብና ዲዛይን ትምህርት ቤት የመጀመርያው ሙሉ ፕሮፌሰርሽፕ ማዕረግ መሆኑ ነው።” ሲል አያይዞ የእንኳን ደስ አለህ መልዕክቱን እስተላልፏል። #ደራሲእንዳለጌታከበደ (ፒኤችዲ) “አሁን የሆንከውን ለመሆን፣ አንተው ራስህ የጻፍከውን ግጥም ኖሮ መገኘትን ይጠይቃል።” ሲል መግቢያ አኑሮ ባጋራውና ራሱ ፕሮፌሰር በቀለ መኮንን በጻፈው ‘ቼ በለው’ በተሰኘው ግጥም እናብቃ፥
ቼ በለው!
ሕይወት ጎዳናው ገጹ ሲለወጥ
በጭነት ታክቶ ጀርባው ሲመለጥ
የእንቅፋት አጽሙ ቋጥኙ ሲገጥ
ሸክም ዘንቦበት ትቢያው ሲላቆጥ
ሲሆን ድጥ በድጥ
ሾህ ጭቃ ቅይጥ
ልብህ አይደንግጥ።
በምኞት ቅዥት በስጋት ርዶ
አይፍረስ ግንቡ ወኔህ ተንዶ
ከቆመው ቆመህ ከንፈር ከመምጠጥ
በተስፋ ፈረስ በልጓም ሸምጥጥ።
አያረጅ የለም አይለዋወጥ
ነገን ተማምነህ በመጓዝ ቁረጥ…
ከሩቅ አልመህ ቅርብ አትርመጥመጥ
ሰግተህ ከምትቆም ስትጋልብ ፍረጥ።
#መምህሩጋሽወርቁ ስለ ፕሮፌሰር በቀለ
መምህር ወርቁ ጎሹ የፕሮፌሰር በቀለ መኮንን አስተማሪ ሲሆኑ የ85 ዓመት ሰውም ናቸው። በቀለ ከወጣትነቱ አንስቶ ህልሙን ለማሳካት ታላቅ ጥረት የሚያደርግ ተማሪዬ ነው ሲሉ በኩራት ምስክርነት ይሰጣሉ። መምህር ወርቁ ጎሹ ቀራጺ በቀለ ከሰዎች ጋር የመግባባት ክህሎትን የታደለ የሚወደውን ሙያ እየሠራ ያለ ብቃት ያለው የሥነ ጥበብ ባለሙያ ነው ሲሉ ይገልጹታል።
ጋሽ ወርቁ 30 ዓመታት አስተምረዋል። በቀለን ሲገልጹት የሚደነቅና የሚከበር ይሉታል። በራሳቸው ጥረት ካደጉት ተርታ ይመድቡታል።
ጋሽ ወርቁ ወደ ኃላ መለስ ብለው የፕሮፌሰር በቀለን የትምህርት አቀባበል ሲያጤኑ የቀን የሌት ጥረት የሚያደርግና የልፋቱን ያገኘ በሚል ያስረዳሉ። ተሰጥዖም የሚታይ ነው ይላሉ።
ዛሬ ፕሮፌሰር መሆኑ ለአገር ትልቅ ኩራት መሆኑንም ነግረውናል።
" የበቀለ ፕሮፌሰር መሆን ለእኔ ብቻ ሳይሆን ለአገር ኩራት ነው። እኔ እንደ አስተማሪው ይህን የምሥራች ስሰማ ደስታዬ ያይላል።እንኳን ደስ ያለህ ልለውም እወዳለሁ። "ሲሉ ለተወዳጅ ሚድያ ምስክርነት ሰጥተዋል።
በቀለ መኮንን፤
በብሔራዊ ትእምርት ፍለጋ ውስጥ
#በተባባሪፕሮፌሰርቴዎድሮስገብሬ
I
ከብረት እስከ ጨርቅ በደረሱ ትይዩ ተቃራኒዎች መካከል ሲያመላልሰን የከረመው በቀለ መኮንን፣ ጥቁር ጤፍ ፈጭቶ--ጥቁር ጤፍ አቡክቶ “በጋገራቸው” ኪነቶች አማካይነት ሊፈትነን “ጤፍና ነጻነት” የሚል ርእስ በሰጠው አዲስ ትርኢት ተገልጧል፡፡ “ጤፍ” እና “ነጻነት”? ጤፍ ገቢር ነው፡፡ ነጻነት ደግሞ ኀልዮ፡፡ ጤፍ ይሰፈራል፤ ይፈጫል፤ ይቦካል፤ ይጋገራል፡፡ ነጻነት ግን በኅሊና ይነደፋል፡፡ ጤፍ እና ነጻነት በነገረ ፍጥረታቸው አይገናኙም፡፡ 'እናስ በምን ተጠየቅ ተዛምደው በአንድ ርእስ ውስጥ በ“እና” ተዳሩ?' የሚል ጠያቂ ከመጣ ምላሹን የሚያገኘው ከትርኢቱ ዐውድ ይሆናል፡፡
በቀለ በትርኢት መግለጫዎቹ በገሀድ እንደሚጠቁመን በአዳዲስ ሥራዎቹ ውስጥ ረቂቁ “ነጻነት” በግዙፉ ጋሻ ውስጥ አድሮ ተጨባጭ ሆኗል፡፡ በእርግጥ ጋሻ የሚመስሉ “እብጠቶች” በበቀለ ዕይታዊ መድበለ ቃላት ውስጥ የሰርክ ጉዳዮች ናቸው፡፡ በቀደሙት ትርኢቶች ውስጥ ጋሻዎች አንድም ቅርጽ ከቅርጽ ተጋጭተው ለሚፈጥሩት “ግብታዊ” ፍቺ ሲባል ይመላለሳሉ፤ አንድም ደግሞ የማረሻን የገነነ ወንዴነት ማስከኛ ሆነው በሚዛን ጠባቂነት (as a feminine energy) ይመጣሉ፡፡ በ“ጤፍና ነጻነት” ነጻነት በጋሻ ውስጥ በማደሩ፣ ጋሻ ከቀደመ ግብሩ የተለየ አዲስና ቋሚ ሚናና ግብር ይዟል ማለት እንችላለን፡፡ አዲስ ግብር ለመያዙ ምስክሩ ይህ ብቻ አይደለም፡፡ በትርኢቱ ውስጥ የሚገጥሙን ጋሻዎች በሙሉ በጤፍ ዱቄት የተገነቡ (የተለሰኑ) ናቸው፡፡ የጋሻዎቹ በጤፍ ዱቄት መገንባት አንድም፣ በትእምርቶቹ መካከል የባሕርይ መጋራት እንዲፈጠር፤ አንድም በኪነቱ ውስጥ ጥንድ ምናብ--ድርብ አስተማስሎ (double representation) እንዲከሰት ዕድል ሰጥቷል፡፡ የጉዳዮች በአንድ ወደተሸረቡ መንታ ትእምርትነት ማደግ ተመልካች ሐሳቡን የሚያሰላበትን፣ ትችቱን የሚያፍታታበትን ምቹ የመፈከሪያ ዐውድ እንዲያገኝ አስችሎታል፡፡
ጋሻ የነጻነት እና የአርበኝነት ማኅደር ነው፡፡ (ይህ ዓይነቱ የጋሻ ፍቺ በተገኘበት ባህል ውስጥ ጭምር ይታወቃል፡፡) ቆየት አድርጌ በስፋት እንደማሳየው ጤፍ በፈንታው የ“ኢትዮጵያ” እና “የኢትዮጵያዊነት” ብሔራዊ ትእምርት ነው፡፡ በዚህ ዐውድ የብሔራዊ ትእምርት ፋይዳ አንድም፣ በነጻነት፣ በአገር እና በብሔራዊ ምንትነት መካከል ያለውን ረቂት ተራክቦና ውስብስብ ተጻምሮ ተጨባጭ ማድረግ ነው፡፡ አንድም ደግሞ ተራክቦውን--ተጻምሮውን ጠብቆ ለማኖር ዜጎች በአርበኝነት መንፈስ የሚከፍሉትን የላብና የደም መስዋዕትነት ማመልከት ነው ማለት እንችላለን፡፡ (በ“Gluten-free-dom II” እንጀራ የጠመጠመ ጋሻ በአናታቸው የደፉ፣ በትኩስ የአመድ ደለል ላይ/ውስጥ የቆሙ ሰባት እናቶች እንዲህ ላለው አንድምታ አስረጂዎች ይሆኑናል፡፡)
II
ብሔራዊ ትእምርቶች የብሔራዊ ምንትነት ግላጼዎች (identity expressions) ናቸው፡፡ የምንትነቱ ሥሪት (identity construction) በተረኮቹና በትእምርቶቹ ጥራትና ጥንካሬ ላይ ይወሰናል፡፡ ግላጼዎቹ እና ሥሪቱ የሚተጋገዙ ብቻ ሳይሆን የሚተካኩ ጉዳዮች ጭምር ናቸው፡፡ ያንዱ መድከም ሌላውን ያጎድላል፡፡ ያንዱ መዛል ሌላውን ያፈርሳል፡፡ የብሔራዊ ትእምርት ቀረጻ ብሔራዊ-ጥበባዊ ተልእኮ ነው፡፡ የአንድ ሕዝብ ብሔራዊ ምንትነት በአንጻራዊነት ለዘመናት ጸንቶ ይዘልቅ ዘንድ ተረኮች (ቃላዊ፣ ዕይታዊ፣ ትውናዊ፣ ወዘተ. ተረኮች) እና ትእምርቶች በጥንቃቄ መመረጥና መቀናበር፣ በየጊዜው እየተመረመሩ መታረምና መከለስ ይኖርባቸዋል፡፡ ብሔራዊ ምንትነት በዐቢይነት የውክልና ጉዳይ ነው፡፡ በአንድ አገር ውስጥ እያሉ እንደሌሉ የተቆጠሩ ወገኖች፣ ቸል የተባሉ ሰብአዊ ዕሤቶች፤ አቅም ባገኙ፣ የኃይል ሚዛን በለወጡ ጊዜ በነባር ተረኮች እና ትእምርቶች የተሸመነውን ብሔራዊ ምንትነት እስከ መሻር፣ አፍርሶ እንደ አዲስ እስከመሥራት የሚያደርስ ጥያቄ ያነሳሉ፡፡ ይህ ሲከሰት የአገር ግንባታ ሂደት ይስተጓጎላል፤ ማኅበራዊ ውጥረት ይነግሣል፡፡ (የዛሬዋ ኢትዮጵያ ለዚህ ዓይነቱ እውነታ አብነታችን ናት፡፡) በመሆኑም ብሔራዊ ትእምርት ቢያንስ ቢያንስ ረጅም የታሪክ ዘመንን፣ ሰፊ መልክአ ምድርን እና ገሀድ የወጡ የማኅበረሰብ ክፍሎችን እና ዕሤቶችን ሊያካልል ይገባል፡፡ ብሔራዊ ትእምርት ከውክልናው ፈርጀ ብዙነት ባሻገር በኪነት ከፍታው እና በኀልዮ ጥራቱም ተለይቶ መታወቅ አለበት፡፡ ጥቅል በሆነ አነጋገር፣ ብሔራዊ ትእምርት ጥልቅ በሆነ ጊዜ ውስጥ፣ ጽኑእ በሆነ መሠረት ላይ የሚታነጽ በነባርና በአዳዲስ ዕሤቶች ትብብር የሚሸመን ዐውራ ምስል ነው፡፡
እንደ ኢትዮጵያ ላለ ኅብረ ባህላዊ አገር ብሔራዊ ትእምርት በትግግዝ የሚፈጸም ብሔራዊ--ኪናዊ ተልእኮ ነው፡፡ ብሔራዊ ትእምርት እርስ በርስ ሊናበቡና ሊከታተሉ በሚችሉ በግለሰብ፣ በቡድን፣ በትውልድ በሚፈጠሩ ገባር ምናቦች ትግግዝ በዘመናት ሂደት ምልዓት ላይ የሚደርስ ዐውራ ትእምርት ነው፡፡ እንዲህ ዓይነቱን ኪናዊ ትግግዝ--የምናብ ተናባቢነትና የምስል ተከታታይነት--በተጨባጭ ለማሳየት “ጤፍና ነጻነት”ን በሁለት መንገዶች ማንጸር እንችላለን፡፡ ቀዳሚው መንገድ ይህንን ትርኢት ከበቀለ መኮንን ነባር ትርኢቶች ጋራ እያመሳከሩ መፈከር ሲሆን፤ ተከታዩ ደግሞ በየትኛውም የኪነት ዘርፍ ካሉ ዘመነኞቹ ጋራ--ለምሳሌ ከአዳም ረታ ጋራ--እያናበቡ ማስተሳሰር ነው፡፡ የበቀለ መኮንንን ዕይታዊ ጥበብ ከአዳም ረታ ቃላዊ ኪነት አናብቦ በብሔራዊ ትእምርትነት ለማስላት በቂ ምክንያቶች አሉ፡፡ ለዛሬው ትርኢት የነፍስ ያህል የሆነውን ዐውራ መባያ[1]--ጤፍን በበቀለ የአከያየን ልማድ ውስጥ ከገነነው፣ ከማረሻ ጋራ አስተሳስሮ ለማሰብም እንዲሁ፡፡ ከምክንያቶቹ ውስጥ መሠረታዊዎቹ፡- አንደኛ፣ የዐውድ ተዛማጅነት፤ ሁለተኛ፣ የኀልዮ (የጭብጥ) ተከታታይነት፤ ሦስተኛ፣ የቅኝት ወይንም (የርእዮተ ዓለም) ተወራራሽነት፤ አራተኛ፣ የጊዜ ጥልቀት (የነገረ ፍጥረት ብሉይነት)፤ አምስተኛ፣ ሥነ ልሳናዊ ተዛማችነት ናቸው፡፡
“ማረሻ” የግብርና ማምረቻ መሣሪያ፣ “ጤፍ” ደግሞ የግብርና ምርት በመሆናቸው በተፈጥሮ የቅደም-ተከተል ዝምድና አላቸው፡፡ (ተፈጥሯዊው ቅደም ተከተል በጉዳዮቹ መካከል አለ ያልነውን የጭብጥ ተከታታይነት እና የትእምርት ተጋጋዥነት ተጨባጭ ያደርግልናል፡፡) የማምረቻ መሣሪያው (ማረሻ)፣ የአምራቹ (ገበሬ) እና የምርቱ (ጤፍ) ተፈጥሯዊ የተራክቦ ዐውድ ገጠር ነው፡፡ ጤፍ እና ማረሻ ከ85 ከመቶ በላይ ኢትዮጵያዊ ይኖርበታል የሚባለውን፤ ዳሩ ግን በአገሪቱ ፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ እና ምጣኔ ሀብታዊ እንቅስቃሴ ውስጥ ተገቢ ሥፍራ የተነፈገውን ወገን በቀጥታ ይመለከታሉ፡፡ ከያኒው ለተገፉ፣ ሥፍራ ለተነፈጉ ብሔራዊ ጉዳዮች ማድላቱ የትእምርቶቹን ምርጫ ተገቢነት ከማረጋገጡ ባሻገር ቅኝቱን ርእዮተ ዓለማዊ ያደርገዋል፤ (“history from below” እንደሚባለው)፡፡ ገጠርን አትኩሮ፣ ነባር የግብርና መሣሪያንና ጥንታዊ ምርትን (ማረሻንና ጤፍን) ከዚያው ዐውድ መልምሎ በምናብ ማጥለቁ፣ በምስል ማበልጸጉ እና በኀልዮ ማራቀቁ ብዙኃኑን የሚወክል፣ ዘመናትን የሚዋጅ ጽኑእ ብሔራዊ ትእምርት ለመቅረጽ ዕድል የሚሰጥ ይመስለኛል፡፡
የጤፍ ነገረ ኪን እና ፖለቲካም (the poetics and politics of teff) በቅኝት ከዚህ የሚለይ አይመስለኝም፡፡ ጤፍ በመጠን በአነስተኛነቱ “ዝነኛ” ነው፡፡ ለምሳሌ፣ አንድ የስንዴ ቅንጣት በአማካይ ከአንድ መቶ ሃምሳ የጤፍ ቅንጣቶች ጋራ እኩል እንደሆነ ይገመታል፡፡ ይህ ደግሞ “ከትውልድ ሥፍራው” አልፎ በዓለም ካሉ የእኽል ዝርያዎች በሙሉ በመጠን ትንሹ ያደርገዋል፡፡ በደስታ ተክለ ወልድ መዝገበ ቃላት ይህ የእኽል ዘር በተከታዩ መንገድ ተበይኖ እንመለከታለን፤ “ጤፍ፤ የታናሽ እኽል ስም፤ የሣር ዐይነት ሙርዬ የሚመስል፡፡ (ተረት)፤ ሳይቸግር ጤፍ ብድር” (19962፡ 675)፡፡[2] በዓለም ምግብ ድርጅት ገጽ ላይ ሰፍሮ እንደምናነበው፣ ጤፍ ከኢትዮጵያ ውጪ ባሉ አገራት፣ ለምሳሌ በደቡብ አፍሪካ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ከከብቶች ቀለብነት ባለፈ የአፈር መሸርሸርንና የውሃ ብክነትን ለመቀነስ ታስቦ የሚለማ “ተራ ሣር” ነበር፡፡[3] ተወዳጅ ነው በሚባልባት እናት አገሩም ቢሆን በመጠን ማነሱን ታክከው የሚቀርቡ ንጽጽሮች አጓጉልነት አላጣቸውም፡፡ ለአብነት፣ “ከመጤፍ አልቆጠረኝም” እና “ሰው ጤፉ” የሚሉ አገላለጾች በደረጃ ማነስን በገሀድ ያውጃሉ፡፡
ጤፍ በጄኔቲካዊ አወቃቀሩ እጅግ የተወሳሰበ፣ በጾታ ቅንብሩ የተደባለቀ (ፈናፍንት)፣ በምግብ ይዘቱ የበለጸገ የእኽል ዓይነት እንደሆነ የአዝርእት ባለሙያዎች ያስረዳሉ (ሰይፉ 1997)[4]፡፡ ሰይፉ ከተማ በመስኩ ላይ የተካሄዱ ምርምሮችን በከለሱበት ጽሑፋቸው እንደሚያስረዱን፣ የጤፍን የትውልድ ቦታ በእርግጠኝነት መናገር ቢከብድም፣ ጄኔቲካዊ ብዝኃነቱን በማጤን ኢትዮጵያ እናት ምድሩ ልትሆን እንደምትችል መገመት አስቸጋሪ አይሆንም፤ “[T]he genetic diversity for teff exists nowhere in the world except in Ethiopia, indicates that tef originated and was domesticated in Ethiopia” (12)፡፡ ጤፍ በዓለም አቀፍ ደረጃ እጅግ ጥንታዊ ከሚባሉ ጥቂት የእኽል ዘሮች መካከል አንዱ ነው፡፡ በዚህ የእኽል ዘር ላይ ከተካሄዱ ምርምሮች መካከል ብዙዎቹ፣ Nicolai Vavilovን (1951)[5] መሠረት በማድረግ፣ ቅድመ ክርስቶስ ከ4000–1000 በኢትዮጵያ ውስጥ እንደበቀለና ተስፋፍቶ እንደለመደ ይገምታሉ፡፡ እንደ ጤፉ ሁሉ፣ “ኢትዮጵያዊው” ማረሻ፣ ከዕድሜው ጥንትነት ባለፈ ልደትና ዕድገቱም እዚሁ መሆኑን የሚያመላክቱ ምርምሮች አሉ፤ ለምሳሌ፣ Hubert Cochet ኢትዮጵያውያን ገበሬዎች በማረሻ ለ2000 ዓመታት እንዳረሱ ይጠቁማል (2011፡ 31)፡፡[6]
በኢትዮጵያ ውስጥ ከሦስት ሺህ በላይ ዘመናትን ያስቆጠረው፣ ከአገሪቱ ሕዝብ መካከል 70 ከመቶው በእንጀራ መልክ ይመገበዋል ተብሎ የሚገመተው ጤፍ (ታደሠ 2017፡ 50) በሦስቱ ዐበይት የሥነ ልሳን ቡድኖች ተቀራራቢ ስያሜም አለው፡፡ በአማርኛ “ጤፍ”፣ በኦሮምኛ “tafi” በትግሪኛ “ጣፍ”፡፡ በቀለም ስርጭትም ረገድ ወተት ከመሰለ ነጭ (ማኛ) አንስቶ እስከ ጥቁር ድረስ የሚዘልቁ አራትና አምስት ቀለማትን ያቅፋል (አዳም በሁሉም ቀለሞች የሚጫወት ሲሆን የበቀለ ምርጫ ጥቁሩ ነው)፡፡ እንዲህ ያለው የባሕርይ ውስብስብነት፣ የጾታ መንታነት፣ ኅብረ ቀለማዊነት ጤፍን--በአዳም ረታ ጥበበ ቃላት እና በበቀለ ዕይታዊ ጥበብ--ውስጥ ለብሔራዊ ትእምርትነት የተመቸ መባያ አድርጎታል፡፡ “ማረሻ” በበኩሉ ኢትዮጵያውያን የወል ምንትነታቸውን ከሚቀርጹባቸው ብሉይ ዕሤቶች መካከል አንደኛው ነው፡፡ የወልነቱን በዐበይቱ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ውስጥ ባለው የስያሜ ተወራራሽነት መረዳቱ አያሰቸግርም (የአማርኛው “ማረሻ”-- በግእዝ “ማሕረስ”፣ በኦሮምኛ “maarashaa”፣ በትግርኛ “ማሕረሻ” የሚሉ አቻዎች አሉት)፡፡ ብሉይ ነው ስል አንድም፣ የዘፍጥረቱን ጥንታዊነት፤ አንድም፣ የጊዜ ጥልቀቱን ታክኮ የሚመሠረተውን ባህል ጽኑእነት ማመልከቴ ነው፡፡ በተፈጥሮው ቀጥ ያለው፣ የተሳለውና የሾለው ማረሻ፣ በበቀለ ትርኢቶች ውስጥ በከያኒው ፈቃድ፣ ፍላጎትና እጅ መዋቅሩ ተናግቶ፣ “ተፈጥሮው” ተዛብቶ ልክ እንደ ጤፍ ወደ ፈናፍንትነት ተቀይሯል፡፡ የበቀለ ማረሻዎች መዋቅር መናጋት የአድሏዊው የተባዕትነት ሥርዓት ፈርሶ በአዲስ ተምኔታዊ ሥርዓት የመተካቱ አምሳያ ነው፡፡ ከዚህ ሥርዓት ውስጥ ነው እንግዲህ ከያኒው አዳዲስና ነባር ዕሤቶች ተዳርተው የሚሰናኙበትን ብሔራዊ ትእምርት ለመፍጠር የሚታገለው፡፡[7]
ጤፍ እና ማረሻ ኢትዮጵያውያን ጥልቅ ከሆነ ጊዜ፣ የጋራ ታሪካቸውን፣ ርእዮታቸውንና ንጽረታቸውን የሚጠልቁባቸው፤ ሩቅ ከሚባል ትናንት የወል ልቡናቸውንና ምንትነታቸውን የሚያደሩባቸው “ቁሳዊ” ዕሤቶች ናቸው፡፡ ቤኔዲክት አንደርሰን፣ “It is the magic of nationalism to turn chance into destiny” (1983፡ 12)[8] እንዳለው ዕጣ ፈንታቸው ጭምር ተጠላልፎ የተሰናኘባቸው የወል ዕሤቶች፡፡ ማን ከዕጣው ማምለጥ ይቻለዋል? እንደሚታወቀው እንዲህ ያለ ዕሤት በጥልቅ ጊዜ እና በጽኑእ መሠረት ላይ የሚቆም አገር ለማነጽ ምቹ ዕድል ይፈጥራል፡፡ በእርግጥ አንድ ማኅበር በጽናት ይቆም ዘንድ ዕጣውን ከቋጠረበት ሩቅ ትናንት በተጨማሪ፣ በገነነ “የሕዝብ ማኅበራዊ ልቡና” ነገውን የሚዋጅበት የጋራ ስኬት እንደሚያስፈልገው አሌ አይባልም፡፡ ለዚህ ዓይነቱ ስኬት ጤፍ እንግዳ አይመስለኝም፡፡ ትናንት፣ ጤፍን ለሰው ልጅ ምግብነት በማዋል ረገድ ኢትዮጵያ ከዓለም ብቸኛ አገር ነበረች፡፡ ዛሬ፣ በተለይ በአውሮፓና በሰሜን አሜሪካ በሚኖሩ፣ እንጀራን መለያቸው ባደረጉ በ“ነባሬ ባዕድ”[9] (diaspora) ኢትዮጵያውያን በሚተዳደሩ ምግብ ቤቶች አማካይነት ዝናን ያተረፈው ይህ የእኽል ዘር የኢትዮጵያን ድንበር ተሻግሯል፡፡ በጣዕሙ፣ በምግብ ይዘቱና ለጤና ባለው ጠቀሜታ ከተመጋቢው እኩል በሥነ ምግብ ተመራማሪዎች ዘንድ ተወዳጅ የሆነው ጤፍ በትልልቆቹ የዓለም የመገናኛ ብዙኋን ሳይቀር (ለምሳሌ፣ በBBC, VoA, The Washington Post, The Guardian, The New York Times, ወዘተ.) “the next ‘super grain’ of the World” የሚል መወድስ ወርዶለታል፡፡ ይህንን ዝና ተከትሎ ሊመጣ የሚችለው ማኅበራዊ ከፍታ እና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ--(as a national branding) ብሔራዊ ክብርና ኩራትን የመፍጠር አቅም አለው፡፡ የጤፍ ታሪካዊ፣ ባህላዊ እና ማኅበረ-ኢኮኖሚያዊ ፋይዳው አንድም በመከባበር ላይ የተመሠረተ አንድነትን ለመፍጠር የሚያግዝ፤ አንድም በጎሣ፣ በሃይማኖት እና በቋንቋ ምክንያቶች የተፈረቀቀውን ብሔራዊ ልቡና (the national psyche) ለማከም የሚያስችል ዕድል እመስጠቱ ላይ ነው፡፡[10]
III
ትኩረታችንን ወደ ዛሬው ትርኢት እንመልስ፡፡ “ጤፍና ነጻነት”፡፡ ጤፍ የ“ኢትዮጵያ” እና “የኢትዮጵያዊነት” ብሔራዊ ትእምርት፤ ጋሻ በበኩሉ የነጻነት እና የአርበኝነት ማኅደር መሆኑን በመግቢያዬ አመልክቻለሁ፡፡ እንዲህ ያለው የጋሻ ትርጉም ህልው በሆነበት ባህል ውስጥ ጭምር ታውቆ የሚሠራበት ነው፡፡ በትርኢቱ ውስጥ ከቀረቡት ሥራዎች ብዙዎቹ ከጤፍ እና ከጋሻ ተራክቦ የተገኙ ናቸው፡፡ ይህ ማለት ግን ሁለቱ ጉዳዮች በሁሉም ትዕይንቶች ውስጥ እኩል ሥፍራ አላቸው ማለት አይደለም፤ በፍጹም፡፡ ጤፍ በሚናው ይልቃል፡፡ የጭብጥ ክትትል ከመፍጠር፣ የመተርጎሚያ ዐውድ ከመተለም ባለፍ ዝርው ህልውናም አለው፡፡ ጤፍ በቤት ውስጥ ቁስነት ተከስቷል፤ የግድግዳ ምርጊት ሆኖ ተገልጧል፤ ወዘተ፡፡ ጤፍ ታሪክ ነው፤ ምጣኔ ሀብት ነው፤ ፖለቲካ ነው፤ ርእዮተ ዓለም ነው፡፡ በጤፍ የሰው አካል ተገንብቷል፤ የሰው ገጽ ተነድፏል፡፡ ገጻተ ሰብኡ ከጤፍ መልኩንም ይዘቱንም ወርሰዋልና ወደ ጤፍነት ተለወጡ ማለትም እንችላለን፡፡ ከተጨባጭ ሁነቶችና ህልውናዎች ባለፈ ጤፍ ለልእለ አካላዊ ክስተቶች ማድሪያነት ውሎም እንመለከታለን፡፡ ለምሳሌ፣ “ጓዳና ግርግዳ” የሚል ርእስ በተሰጠው፣ በቀጫጭን ዘንጎችና በጥቁር ጤፍ ትግግዝ በተቀናበረ ግድግዳ ላይ (በጤፍ ቡኮ የተመረገ፣ ጋሻ ያዘለ ግድግዳ) ከያኒው ይሁነኝ ብሎ በተዋቸው ሽንትር ሽንቁሮች ውስጥ አሳልፈን የምናየው “የቤተ ክርስቲያን” ጨርቅ ልእለ ፍጥረት ህላዌ ከልደትና ሞት ጋራ የታተመበት ነው፡፡ በመሆኑም ጤፍ በትርኢቱ ውስጥ የነገረ ሰብእን ዕጣ የምናሰላበትን ስብርባሪ አፍታ ጭምር ይሰጠናል ማለት ነው፡፡
በትርኢቱ ውስጥ በጤፍ ከተገነቡ ምስሎች መካከል ገጸ ሰብእ[11] የተነደፈው በሁለት ተከታታይ ትዕይንቶች ውስጥ ብቻ ነው፤ በ“Gluten-free-dom I” እና በ“Gluten-free-dom II”፡፡ እነዚህ ትዕይንቶች “ተከታታይ” ብለን ብቻ የምናልፋቸው አይመስሉኝም፡፡ ይልቁንም እጅግ በተወሳሰበ ትእምርታዊነትና በተራቀቀ ዘይቤ የተከየኑ፣ ለፈርጀ ብዙ ንጽጽርና ትርጓሜ የተመቹ ወደረኛ ቅርጾች ናቸው፡፡ ኋለኛውን መነሻ እናድርግ፡፡ ጀርባ ለጀርባ እንጂ ፊት ለፊት የማይተያዩ፣ ትከሻ ለትከሻ ገጥመው ክብ የሰሩ የሰባት ነፍሰ ጡሮች ትዕይንት ነው፡፡ በዚህ ትዕይንት ውስጥ ሴቶቹ ክብነቱን ጠብቆ በጠባቡ በሚዞራቸው ቡላ ቀለም ያለው የአመድ ደለል ላይ ቆመዋል፡፡ ደለሉን ተከትሎ በክቡ የሰፈነው ነጭ አመድ ከሸማ የተሠራ ምንጣፍ፣ በዙሪያው የተኮለኮለው የከሰል ሰልፈኛ ደግሞ ጥቁር ጥለት ይመስላሉ፡፡ በሆዳቸው ፍሬ የያዙ ሰባት ሴቶች የተደራረቡ እጆቻቸውን ሐፍረታቸው ላይ ጣል እንዳደረጉ፣ እንጀራ የለበሰ ጋሻ አናታቸው ላይ እንደደፉ፣ በአክብሮት ይሁን በፍርሐት አልያም በሐፍረት አቀርቅረዋል፡፡
ሁለተኛው ትዕይንት የአንድ ሰው “ገድል” ነው፡፡ ይህንን ገድል እኔ “ገልና ገልቱ” ብዬ እጠራዋለሁ፡፡ (“ገል” የጋን ስባሪ፤ “ገልቱ” ያልሠለጠነ፣ በድንቁርና የተደፈነ፡፡) ዙሪያውን በተሰባበሩ ሸክላዎች የተከበበ፣ ከምድር ከፍ ብሎ የታነጸ፣ ባለ ስድስት ማዕዘን ቅርጽ ያለው ጡብ ገዝፎ ይታያል፡፡ ሙቀት ፍለጋ እጆቹን ወደ ፊት የዘረጋው ሰው እጡቡ አናት ላይ ባፍጢሙ እደፋው የአባቶቹ ጋሻ ላይ “ተመቻችቶ” ተቀምጦ “የደቀቁ የሸክላ ገሎችን በተመስጦ ይሞቃል”፡፡ ሁለቱ ትይዕንቶች የመከታተል ብቻ ሳይሆን እርስ በእርስ የመተረጓጎም ባሕርይም አላቸው፡፡ ይህንን ለማጤን እላይ በገለጻዎቹ ውስጥ የሰፈሩትን ወደረኛ ድርጊቶችና ሁነቶች ማነጻጸሩ ብቻ በቂ ይመስለኛል፡፡
ሴቶቹ በገዛ ፈቃዳቸው ፋታ ለማይሰጥ፣ ድካም ለበረታበት፣ ህመም ላለበት ኃላፊነት ራሳቸውን የሞሸሩ ይመስላሉ፡፡ አንድም የቁጥራቸው ሰባትነት የኃላፊነቱን ክብደት ያጸናል፡፡ ሰባት ቁጥር በትውፊት፣ በሃይማኖት፣ በኪነት፣ ወዘተ. ውስጥ ምልዐትን፣ ፍጹምነትን ለማመልከት ተመላልሶ የሚመጣ ነባር መባያ ነው፡፡ ፍጹምነቱና ሙሉነቱ የበረከትም የቅጣትም ሊሆን ቢችልም፡፡ አንድም ሴቶቹ የቆሙበት የአመድ ደለልም ሆነ አካላቸው ተገጣጥሞ የፈጠረው የቅርጽ ክብነት እላይ በቁጥር ጸና ያልነውን በድካምና በህመም የተሞላ ኃላፊነት ፍጹም ያደርገዋል፡፡ በክብነት ውስጥ መውጫ ቀዳዳ ይጠፋል፤ መነሻና መድረሻ ይታጣል፡፡ ለእረፍት የሚሆን ጥጋት አይሰጥም፡፡ በቀለ በምስሉ መግለጫ ላይ በገሀድ እንደሚጠቁመን ሰባቱ ሴቶች በዝርው ሰባቱን ቀናት ይወክላሉ፡፡ በዚህም ሰንበት ተገድፏል፤ የለመድነው የጊዜ መስፈሪያ ተሽሯል፡፡ ቀናቱ በሴቶቹ ድርጊት ተቃኝተው “ጊዜ” ከሰው ጋራ የሚለያይበት መስመር ደብዝዟል፡፡ መነሻ፣ ማጋመሻ፣ መዳረሻ የሚባሉ አንድም፣ የድርጊትና የሁነትና መሥፈሪያዎች፤ አንድም የጊዜ ዋቢዎች ሳስተዋል፡፡
እላይ በእንጥልጥል ወደተውነው ጉዳይ እንመለስ፤ “ገሎችን መሞቅ” ምን ማለት ነው? ከከያኒው ምስክርነት ባሻገር የወጣቱ የእጅ አዘረጋግ ሁኔታ በሙቀቱና በአካሉ መካከል በፈጠረው ሚዛን ሙቀትና ምቾት መኖራቸውን እንረዳለን፡፡ ግን እሳቱ ወዴት ነው? የሙቀቱ ምንጭስ ምንድ ነው? ለእነዚህ ጥያቄዎች በአንድምታ የምንገልጠው እውነታ ካልሆነ በቀር፤ በቀጥታ የምናገኘው መልስ ያለ አይመስለኝም፡፡ በባለ ስድስቱ ማዕዘን ጡብ ዙሪያ በሰፊው የፈሰሱት የገል ስብርባሪዎች በኢትዮጵያውን የቆየ ታሪክ ውስጥ ቋሚ ሥፍራ ያላቸው፣ በሸክላ የተሠሩ አገረ ሰብአዊ ዕደ ጥበባት ናቸው፤ በየዓይነቱ --የጀበና፣ የምጣድ፣ የድስት፣ የጋን፣ የጣባ፣ የዕጣን ማጨሻ፣ ወዘተ. ስብርባሪዎች፡፡ ስብርባሪዎቹን በቅርበት ላጤነ ሰው ዕደ ጥበባቱ በእርጅና ምክንያት ከሰርክ ግብራቸው የተገለሉ አይመስሉም፡፡ ይልቁንም ከነወዛቸው ከነጉልበታቸው ያሉ፣ ከግብራቸው በግድ ተነቅለው የደቀቁ ነው የሚመስሉት፡፡ በሌላ ቋንቋ ሙቀቱ የሚመነጨው ከገሎቹ ትኩስነት ነው፡፡ ትኩስነት፤ አንድም፣ ከእሳት ምድጃ የሰበሰቡትን ሙቀት ይዞ ማቆየት ነው፡፡ ገልቱው ዕደ ጥበባቱን ከተሰየሙበት ምድጃ ላይ ነቅሎ --ቡናና ወጡን ደፍቶ፣ ዳቦና እንጀራውን ገልብጦ--ጀበናውን፣ ድስቱን፣ ገበር ምጣዱን፣ ምጣዱን አንክቶ፣ እንካቹን ሜዳ ላይ ዘርቶ ትኩስነታቸውን እየሞቀ ነው፡፡ አንድም በዘይቤ ተራ እንናገርና ትኩስነት አፍላነት ነው፡፡ የአገልግሎት ዘመን አለመጋመስ፡፡ ከብርታትና ጥንካሬ ጋራ መሆን፡፡ ጠላውን ደፍቶ፣ እርጎውን ገልብጦ፣ ወዘተ. ያደቀቃቸው የሸክላ ውጤቶች፡፡
በዚሁ ተጠየቅ ከተጓዝን የሴቶቹን አቋቋም በመመርመር በሰባት ቁጥር እና በክብ ቅርጽ ትግግዝ ጸና ያልነውን ህመም በተጨባጭ መመልከት እንችላለን፡፡ የሴቶቹ ፋታ የለሽነት ድርጊቶቹንና ሁነቶቹን በሙሉ ወደማያቋርጥ ሂደትነት ለውጧቸዋል፡፡ ይህንን ለማጤን--በተለመደው አገላለጽ--እንጀራ የጠመጠመ ጋሻ ከሰፈነበት የራስ ጸጉራቸው፣ በአመድ ደለል እስከተደበቀው የእግር ጥፍራቸው ድረስ መመልከቱ በቂ ነው፡፡ አመዱ እና እንጀራው ትይዩ ናቸው፤ አንዱ ምርት ሌላው ግርድ፡፡ ከአናት እንጀራው በተመረተ ቁጥር ከስር አዲስ አመድ ይወድቃል፡፡ አዲስ አመድ --ትኩሣቱን ያልጨረሰ አመድ፤ ረመጥ፡፡ ይህ ማለት ሴቶቹ ረመጥ ላይ ቆመዋል እንደማለት ነው፡፡
ቀደም አድርጌ ለማሳየት እንደሞከርኩት ሴቶቹ እንዲህ ያለውን በድካምና በህመም የተሞላ ኃላፊነት በፈቃዳቸው መርጠው ተቀብለዋል፡፡ በማሕፀኗ ሽል የያዘችን እናት በረመጥ እስከመድበን የሚያደርስ መስዋዕትነት ምን የሚሉት ኃላፊነት፣ እንዴት ያለ ዓላማና ተልእኮ ነው? የራስን ሰብእና የሚያደቅቅ፣ ህልውናን የሚያመነምን፣ ሕይወትን የሚያሰልል ተግባር ውስጥ በፈቃድ መሳተፍ ራስን ለከፋ ጉዳት ማጨት ይመስላል፡፡ የፈቃድ ጉዳት (self-destruction)፣ ከፍ ሲልም የፈቃድ ሞት ከዳግም ልደት ጋር የሚዛመዱበት እንዲህ ያለው አቀራረብ ሚታዊ አመሳሰል ነው፡፡ ይህን ዓይነቱን አመሳሰል በሚቶሎጂ ውስጥ በብሉየ መዋዕልና[12] ደንብ ከተቀረጹ ምስሎች (archetypal imageries) ጋራ አቆራኝተን መመልከት እንችላለን፡፡ በሆዳቸው ፍሬ የያዙ ሴቶች ትከሻ ለትከሻ ገጥመው ክብ መሥራታቸው፣ በሠሩት ክበብ ውስጥ ረመጥ ላይ መቆማቸው፣ በአመድ ደለል መያዛቸው፣ እንጀራ “ማብቀላቸው” በአንድ ግዜ ኦሮቡረስን (በክብነት) እና ፊኒክስን (በረመጥነት-አመድነት) አቃልጠን እንድናስብ ያደርገናል፡፡ ራሷን አቃጥላ ከትቢያዋ ላይ ነፍስ የምትዘራው ፊኒክስ (Phoenix) እና በክብ ቅርጽ ከጅራቱ አንስቶ ሙሉ አካሉን በልቶ በአዲስ ህልውና የሚከሰተው አሮቡሮስ (Ouroborus) “ሁለንተናዊ” ሊባሉ የሚችሉ የህመምና ድኅነት፣ የሞትና ልደት ትእምርቶች ናቸው፡፡ ባዶ እግራቸውን ረመጥ ላይ የቆሙ ሰባት እናቶች በቸልታ የተጎዳውን ነባር ምንትነት፤ በሆዷቸው የያዟቸው ሰባት ፍሬዎች ደግሞ እንደ አዲስ ይወለድ ዘንድ የሚጠበቀውን ርእይና ርእዮት ይወክላሉ፡፡ ከዚህ ትዕይንት ዓላማዎች መካከል አንዱና ምናልባትም ቀዳሚው ለዘመናት ለኖረው፣ ዳሩ ግን ቸል ለተባለው የእናቶች ህመምና ድካም--የላቀ ብሔራዊ ተግባር--ዕውቅና መስጠት ነው፡፡ ይህ ዕውቅና ልዕለ ሰብአዊ እና ልዕለ ታሪካዊ እንጂ ተርታና ሰርካዊ አይደለም፡፡ በሌላ ቋንቋ፣ ከያኒው ከፍ ባለ የአከያየን ስልትና ርእዮት እናቶችን ጥልቅ ጊዜ ውስጥ በመትከል ወደ ሚታዊ ተጋዳሊነት ቀይሯቸዋል፡፡ በምላሹም ከዚያው ጥልቀት ውስጥ በጽናት የሚቆም ብሔራዊ ትእምርት እና ብሔራዊ ምንትነት ለማስገር ሞክሯል፡፡
አንድም እናቶች ካለመኖር ህጽን መኖርን አስገኝተዋልና ለዚያም ኪናዊ ውዳሴ እንደ ማውረድ ሊቆጠር ይችላል፡፡ በአንዳንዶች ግምት “ጤፍ” የሚለው መጠሪያ “ጠፋ” ከሚለው ቃል የተገኘ ነው፤ ጠፋ፣ መኖር አቆመ፣ ህልውናው አበቃ እንደማለት፡፡ በሌላ ቋንቋ የዚህ የእህል ዘር የመጠን አነስተኛነት ከመኖር ይልቅ ላለመኖር ይቀርባል እንደማለትም ነው፡፡ የ“ጤፍ” የፍቺ ነቅኡ “ጠፋ” የሚለው ግስ ከሆነ፣ አንድም፣ ጤፍ የምንለው፣ በጣት የምንቆነጥረው ደቃቅ ነገር በተጨባጭ አለመኖርን ያስተማስላል (the representation of absence, the visibility of invisibilty) እንደማለት ነው፡፡ አንድም ዐውራውን የብሔራዊ ሚቶች መሻት--የመነሻዎች ሁሉ መነሻ የመሆንን፣ ከምንምነት ነቅእ የመፍለቅን መሻት--ይጠልፍልናል፡፡ ጤፍ አለመኖርን ከወከለ ከጤፍ የምንጠልቀው “ኢትዮጵያዊነት” ከእመ አበ አልቦ እንደተገኘ (creation ex nihilo, that is, creation from nothing) ይቆጠራል፡፡ በዘይቤ ተራ እንነጋገርና የኢትዮጵያ ገበሬ “አለመኖርን” ይዘራል፡፡ እናቶች ደግሞ ከአለመኖር ማሕጸን “እንጀራን” የመሰለ ግዙፍ ኑባሬ ያዋልዳሉ እንደማለት ነው፡፡ ከጤፍ አብራክ እንጀራ የመክፈሉን ጉዳይ፣ እናቶቹ በሆዳቸው ከያዙት ጽንስ መወለድ ጋራ አቆራኝቶ ማየት ይቻላል፤ ያ ጽንስ አንድም በነባርና በአዳዲስ እሴቶች ትብብር ይሸመናል ያልነው “ኢትዮጵያዊነት” (pan-Ethiopianism) ነው፡፡ የእንጀራው አናት ወጥቶ በጋሻ ቅርጽ መስፈኑ ደግሞ የልደቱ መፈጸም ማረጋገጫ ትእምርት ነው፡፡ ጋሻ የአርበኝነትና የነጻነት ትእምርት፤ ጤፍ ደግሞ የኢትዮጵያና የኢትዮጵያዊነት ማደርያ ነው ካልን፣ በጋሻ መልክ የተከሰተው እንጀራ የዚህ ማረጋገጫ ሰንደቁ (the symbol of national imaginary) ይሆናል፡፡ አንድም በጋሻ ቅርጽ አናታቸውን የከበበው እንጀራ በሰማዕትነት እንዳገኙት የብርሃን አክሊል (halo or nimbus) ሊቆጠር ይችላል፡፡ እንዲህ ያለው ሐቲት ለኪነቱ በ“በብሉየ መዋዕልና” ደንብ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን አጥልቆ የሚተክልበትን ረቂቅ ዐውድ ይሰጠዋል፡፡
ኢትዮጵያውያን አንጀራን መመገብ የጀመሩበትን ጊዜ የሚያመለክት እርግጠኛ መረጃ የለም፡፡ ነገር ግን የእንጀራን መነሻ የሚጠቁሙ፣ ዘመኑን እስከ ቅድመ ክርስቶስ እስከ 100 ዓ.ዓ.
የሚያደርሱ የቃል ተረኮች እንዳሉ ስትዋርትና አስናቀ ይናገራሉ (1962: 127)[13]፡፡ በእነዚህ ተረኮች ወስጥ እንጀራ ኢትዮጵያውያን በተቸገሩ ወቅት ከልእለ ፍጥረት ህላዌ የተሰጠ በረከት ተደርጎ ነው የሚቀርበው፡፡ (በበቀለ ኪነት ውስጥ ያንን ሚና ወደ ሚታዊ ህልውናነት የተሸጋገሩት እናቶች ወስደውታል):: ቀደም አድርገን የጠቀስነው የታደሠ ጥናት እንደሚያመላክተን (2017፣ 50) ከኢትዮጵያ ሕዝብ ውስጥ 70 ከመቶ ያህሉ ጤፍን በእንጀራ መልክ ተመጋቢ ነው፡፡ ይህ ቁጥር የጤፍ እንጀራን ለብሔራዊ ምግብነት የሚያበቃው ይመስለኛል፡፡
ጋኖቹን[14] አንክቶ፣ ባፍጢሙ እደፋው ጋሻ ላይ ተቀምጦ ስብርባሪ ገሎች እየሞቀ በምቾት የሚመሰጠው ገልቱ በፈንታው ፍቺው የዚህ ተቃራኒ ነው የሚመስለው፡፡ በእኔ አረዳድ ትዕይንቱ የዘመናችን ክፉ አባዜ--አገር ለዘመናት ጸንታ የኖረችባቸውን የዕሤት ሥርዓቶች፣ የጋራ ታሪኮች፣ የወል ልቡናዎች የመቀናቀን አባዜ--በስላቅ የተነደፈበት ነው፡፡ ስላቁ የቤቱን ማገር እየመዘዘ በሚያነድድ፣ መሠረቱን እየቆረቆረ ቤቱን ራሱ ላይ በሚንድ ገልቱ ላይ ቢያርፍም፣ አገራዊ አደጋው የምር እና ቅርብ መሆኑን ትላልቅ ጋኖችን በማውደም አሳይቷል፡፡ አገር ጸናባቸው ያልናቸው ረቂቅ ዕሤቶች ወጣቱን በከበቡት ስብርባሪ ገሎች ገዝፈው ይታያሉ፡፡ “ጋን” ከአገረ ሰብእ ጥበብነቱ ባሻገር አገር አጽንተው ያቆዩትን ረቂቅ ዕሤቶች ለመወከል የሚያበቃ ሥነ ልሳናዊ እና ሥነ ፍቻዊ ባሕርይ አለው፡፡ በተለይም ቃሉ “ጋኖች” ተብሎ በብዙ ቁጥር ሲጠራ የፍቺው ስፋት ከማጀት እስከ አደባባይ ይዘልቃል፤ “ጋኖች፤ ትልልቆች ሰዎች ዋኖች ጨዎች ጎምቱዎች አባቶች ዐዛውንቶች፡፡ (ተረት)፤ ጋኖች ዐለቁና ምንቸቶች ጋን ኾኑ” (ደስታ ተክለ ወልድ፣ 280)፡፡ አንድም፣ ከማጀት እስከ ቤተ መንግሥት የተዘረጋ ፍቺ አለው፤ ከጠላ መጥመቂያ፣ ከጠጅ መጣያ ቁስነት እስከ ንጉሥ መጠሪያት የሚደርስ ፍቺ፤ የጃን ሆይ አቻ ሆኖ፣ “ጋን ሆይ ፤-ገናና ሆይ፤--ጃን ሆይ፡፡” (280) እያስባለ፡፡
እስካሁን ለማሳየት እንደሞከርኩት Gluten-free-dom “I” እና “II” በተወሳሰቡ ትእምርቶች እና በተራቀቁ እይታዊ ሜታፈሮች የተከየኑ ድንቅ ምስሎች ናቸው፡፡ በምስሎቹ መካከል የሚካሄደው ንጽጽር ከዚህም አልፎ ልሄድ ይችላል፡፡ እኛ ይህን በይደር ዘግተን ለመጣጥፉ እንደ ማሳረጊያ ወደሚያገለግሉ አንድ ሁለት ነጥቦች እንለፍ፡፡
IV
በትርኢቱ ውስጥ ከቀረቡት ሥራዎች ብዙዎቹ --ከፀሐይ እና ጎጆ (ከባህል እና ተፈጥሮ ) መስተጋብር ከተቀሰቀሱ የሰርክ ደፋ ቀናዎች (“አሁንና ቅድም” I፣ II፣ III)፣ የዘወትር ስሜቶች (“አዙረኝ አዛዙረኝ”) አንስቶ፤ ረቂቆቹ የወል ዕሤቶች፣ የጋራ ልቡናዎች እስከተከተቡባቸው ምስሎች (“ጓዳና ግድግዳ”፣ Gluten-free-dom “I” እና “II”) ድረስ ከጤፍ እና ከጋሻ ትእምርታዊ ተራክቦ የተገኙ ናቸው፡፡ እርግጥ ነው እንዲህ ካለው የትርኢት ጠቅላይ ፈለግ የሚሸሹ ጥቂት ሥራዎች አይጠፉም፡፡ ለዚህ ደግሞ፣ “የገደል ማሚቶ”፣ “ቆሜ ተቀምጬ” እና “አዲስ ጠላ በሰባራ አንኮላ” አብነት ይሆናሉ፡፡ “የገደል ማሚቶ” ለኀልዮ እምብዛም ያልተጨነቀ፣ ምናልባትም የሄደ ድምጽ ተመልሶ የሚመጣበት የቅርጾች ጨዋታ ነው፡፡ በ“አዲስ ጠላ በሰባራ አንኮላ” ውስጥ የጤፍና የጋሻን የተናጠልም ይሁን የወል ህልውና በገሀድ ፈልገን ስለማናገኝ ሥራው ከትርኢቱ አጠቃላይ መንፈስ ያፈነገጠ ይመስላል፡፡ ይሔ ግምት ግን ኪነቱን ከቀሪዎቹ ሥራዎች ጋራ አናብበን መተርጎም ስንጀምር በቀላሉ የሚፈርስ ነው፡፡ እንዲህ፣ እንደ “ጤፍና ነጻነት” ባለ አንድ ወጥ ርእስ በተሰጠው ከፍ ያለ ትርኢት ውስጥ ሥፍራ ያገኙ፣ በተቀራራቢ የጊዜ ክበብ ውስጥ የተከየኑ ሥራዎች በአመዛኙ ተነጥሎ ከሚከናወን ዝግ ምልከታ ይልቅ ለአጎራባች (co-textual) እና ለዐውዳዊ (contextual) ምርምር ይጋብዛሉ፡፡ ይህንን አጠቃላይ የነገረ ፍካሬ መርህ ከግምት ካስገባን፣ ከያኒው በምስሉ መግለጫ ላይ ባቀረበው ፍቺ ብቻ ረግተን የምንቆም አይመስለኝም፡፡ ይልቁንም በአንድምታ ተጨማሪ ትርጉም ለማከል እንጋበዛለን፡፡ በእኔ እምነት በትርኢቱ ውስጥ በአካል ጭምር የተጎራበቱት Gluten-free-dom “I” እና “አዲስ ጠላ በሰባራ አንኮላ” ከጤፍ እና ጋሻ መጉደል ባሻገር በገሎቻቸው ተሳስበው በመንፈስ ይሰምራሉ፤ በጭብጥ ይከታተላሉ፡፡ በትርጓሜም እንደሚከተለው ይተጋገዛሉ፡፡
በጥንታዊው የሒሳብ ማሰላሰያ፣ በአባከስ አምሳያ የተበጀው በአራት ማዕዘን የብረት ፍሬም የታጠረ ምስል፣ ብረቱ ላይ ሻጥ ሻጥ ተደርገው አግድም የተዘረጉ ወልጋዳ የእንጨት ዘንጎች፣ በዘንጎቹ ላይ የሚንሸራሸሩ በቅርጽ

9 months ago
በዳሞ መንግሥቱ የተጻፈ
“ያልተሻገርነው ድልድይ” የተሰኘ
ግሩም መጽሐፍ ለህትመት በቃ፡፡
ደራሲው ከጥልቅ የህይወት ልምዱ በመነሳት ስለ ሀገራችን ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ህይወት የሚመለከቱ ጉዳዮች ከአዝናኝ እና አስተማሪ ከሆኑ ዓለም አቀፍ ገጠመኞቹ ጋር በማዋሀድ ትዝብቱን እና ያልተሻገርናቸውን ድልድዮች ለመሻገር ምን ብናደርግ እንደሚሻል የግል ምልከታውን ከመፍትሔ ሃሳቦች ጋር ያጋራል ::
በእርግጠኝነት የምንነግሮ መፅሀፉን አንብበው ይወዱታል ኪስን በማይጎዳ ዋጋ አትርፋችሁ ትዝናኑበት ዘንድ እየጋበዘን መጽሀፉ :-
በጃፋር የመጽሐፍ መደብር፣
በሀሁ የመጽሐፍ መደብር እና በኤዞፕ የመጽሐፍ መደብር እንደሚገኝ ስንጠቁም በደስታ ነው፡፡
“ያልተሻገርነው ድልድይ”

በሀሁ የመጽሐፍ መደብር እና
በኤዞፕ የመጽሐፍ መደብር እንደሚገኝ ስንጠቁም በደስታ ነው፡፡

Sponsored by
Surafel
Comments