13 days ago
«ጽናት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ታሪካዊ የለውጥ ጉዞ» የተሰኘው መጽሐፍ ሊመረቅ ነው
#ethiopia | አንጋፋው የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ ያለፈባቸውን ታሪካዊ ሂደቶች ተቋማዊ ለውጦችን የሚዳስሰው መጽሐፍ ሊመረቅ መሆኑ ተነግሯል።
መጽሐፉ የዩኒቨርስቲው ስኬቶችንና የዕድገት ጉዞውንም ጭምር ይዳስሳል ተብሏል።
ይህ መጽሐፍ የጎንደር ዩኒቨርሲቲን ታሪክ ከመመዝገብ ባሻገር የተቋማዊ ለውጥ ልምዶችን የአመራር ተሞክሮዎችንና የከፍተኛ ትምህርት ጉዞን የሚያሳይ የእውቀትና የታሪክ ምንጭ እንደሆነ ነው የተገለፀው።
«ጽናት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ታሪካዊ የለውጥ ጉዞ» የተሰኘው ታሪካዊ መጽሐፍ የተጻፈው በዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት መሆኑም ሰምተናል።
መጽሐፉ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አሥራት ዓፀደወይን የተጻፈ ሲሆን ሐምሌ 18 ቀን 2018 ዓ.ም በደማቅ ሁኔታ በይፋ ይመረቃል ተብሏል።
«ጽናት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ታሪካዊ የለውጥ ጉዞ» በሚል ርእስ ተጽፎ የተዘጋጀው ይህ መጽሐፍ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች እና የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ አባላት በተገኙበት ይመረቃል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #ኢትዮጵያጎንደርየመጽሐፍምረቃ #ጽናትየጎንደርዩኒቨርሲቲ #ታሪካዊየለውጥጉዞ #ጎንደርዩኒቨርስቲአዲስመጽሐፍ

1 month ago
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ወደ ራስ-ገዝነት፤ ከልቀት ማዕከልነት እስከ ዘመናዊ ግብርና እና ዲጂታላይዜሽን
#ethiopia | የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከሀገሪቱ ቀዳሚ ተቋማት አንዱ በመሆን ወደ ሙሉ ራስ-ገዝነት ለመሸጋገር የሚያስችሉትን ሰፊ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ማጠናቀቁን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት አስራት አጸደወይን (ዶ/ር) ገለጹ።
ፕሬዝዳንቱ እንደገለጹት፣ ይህ የራስ-ገዝነት ጉዞ ተቋሙ የተሻለ አካዳሚያዊ፣ አስተዳደራዊ እና የፋይናንስ ነጻነት ጎናጽፎ የላቀ ተልዕኮውን እንዲያሳካ ሰፊ በር ይከፍትለታል። ለዚህም ስኬት ይረዳ ዘንድ በዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብና በከተማው ምክር ቤት ደረጃ ሰፊ የግንዛቤ ፈጠራ ስራዎች መከናወናቸውን ያነሱት አስራት (ዶ/ር)፣ ራስ-ገዝነት ነጻነትን ብቻ ሳይሆን ተጠያቂነትንም አብሮ የሚያሰፍን መሆኑን አስገንዝበዋል።
ከዚሁ ጋር ተያይዞ በሽግግሩ ወቅት መመሪያ የሚሆኑ 55 ያህል ልዩ ልዩ ስትራቴጂካዊ ፖሊሲዎችና ሰነዶች ተዘጋጅተው ለትምህርት ሚኒስቴር ገቢ መደረጋቸውንና በውጭ ባለሙያዎች በተደረገው የዝግጁነት ግምገማም ዩኒቨርሲቲው እጅግ አበረታች ውጤት ማስመዝገቡን በኩራት ገልጸዋል።
ዩኒቨርሲቲው ከመንግስት የሚገኘውን የፋይናንስ ድጋፍ በሂደት በመቀነስ ራሱን ለመቻል የገቢ ምንጮቹን እያሰፋ መሆኑን ፕሬዝዳንቱ አስረድተዋል። በዚህም መሰረት በ"እቴጌ ምንትዋብ ንግድና ማማከር ኢንተርፕራይዝ" ስር ደረጃቸውን የጠበቁ እንደ ማተሚያ ቤት፣ ሞዴል ፋርማሲ፣ የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ (ICT) እና የምህንድስና ማማከር አገልግሎቶችን ጨምሮ ወደ አስር የሚጠጉ የገቢ ማስገኛ ዲፓርትመንቶች ተቋቁመው ስራ ጀምረዋል።
አስራት (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ እነዚህ ተቋማት ለዩኒቨርሲቲው ተጨማሪ ሀብት ከመፍጠርና ለአካባቢው ወጣቶች የስራ እድል ከመስጠት ባለፈ፣ ለተማሪዎች እንደ ተግባራዊ መማሪያ ቤተ-ሙከራ በመሆን እያገለገሉ ይገኛሉ።
በተጨማሪም ጥራታቸውን የጠበቁ ምርቶችና መድኃኒቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ የአካባቢውን የገበያ ዋጋ በማረጋጋት ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ መሆኑን አብራርተዋል።
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ቀደም ሲል በጤናው ዘርፍ ብቻ ከነበረው የልቀት ማዕከልነት ወጥቶ አሁን ላይ በ11 ኮሌጆች ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ፕሬዝዳንቱ ጠቁመዋል። በተለይም በከተማ ግብርና ዙሪያ በአጼ ቴዎድሮስና በፋሲል ግቢዎች እንዲሁም በጎርጎራ ጣቢያ ሰፋፊ የአትክልት፣ ፍራፍሬና የቡና ልማት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልጸዋል።
አርሶ አደሩን በዘመናዊ የግብርና ቴክኖሎጂ ለማደራጀትና አመለካከቱን ለመቀየር የትራክተሮችና የኮምባይነር ሀርቨስተር አቅርቦቶችን በማመቻቸት የግብርና መካናይዜሽን ስራዎችን እያስተዋወቁ መሆናቸውን አስራት (ዶ/ር) ጠቅሰዋል።
ዩኒቨርሲቲው በየዓመቱ የገበሬዎች ቀንን በማክበር የልምድ ልውውጥ መድረኮችንና ኤግዚቢሽኖችን እያዘጋጀ ሲሆን፣ ይህም ማህበረሰቡ የተመጣጠነ ምግብ እንዲያገኝና የአካባቢው ምርታማነት እንዲያድግ ትልቅ መነቃቃት መፍጠሩን አብራርተዋል።
በመጨረሻም ተቋሙ የሀገሪቱን የዲጂታል 2030 እቅድ ለማሳካት በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን ፕሬዝዳንቱ አረጋግጠዋል።
ለዚህም ይረዳ ዘንድ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) የምርምር ማዕከል መከፈቱንና በዘርፉ የማስተርስና የፒኤችዲ ፕሮግራሞች መጀመራቸውን ገልጸዋል። ዩኒቨርሲቲው አሰራሩን ሙሉ በሙሉ ወረቀት አልባ (paperless) ለማድረግ የፋይናንስ፣ የግዢ፣ የንብረት አስተዳደርና የምርምር ግምገማዎችን በዘመናዊ ዲጂታል ሲስተሞች ማከናወን መጀመሩን አስራት (ዶ/ር) አስታውቀዋል።
ይህ የቴክኖሎጂ ሽግግር አላስፈላጊ ወጪዎችን በከፍተኛ ደረጃ የመቀነስ፣ ውጤታማነትን የማሳደግና ተጠያቂነትን የማስፈን አቅም እንዳለው የገለጹት ፕሬዝዳንቱ፣ በአሁኑ ወቅት ግንባታው እየተጠናቀቀ የሚገኘው ዘመናዊ የዳታ ሴንተርና የዋን ካርድ (One Card) ሲስተም መሰረተ ልማቶች ተቋሙን ይበልጥ ወደላቀ የዲጂታል ምዕራፍ እንደሚያሸጋግሩት እምነታቸውን ገልጸዋል።
በጌትነት ተመስገን
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ
#ethiopia #gondaruniversity #education #የጎንደርዩኒቨርሲቲ

Comments