5 months ago
ዶናልድ ትራምፕ ቴህራንን አስጠነቀቁ
#ethiopia | የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የኢራን መንግሥት ሰላማዊ ተቃዋሚዎችን በኃይል ለመጨፍለቅ የሚሞክር ከሆነ ዋሽንግተን አስፈላጊውን ምላሽ ለመስጠት መዘጋጀቷን አስጠነቀቁ።
ፕሬዝዳንቱ የግል ማህበራዊ ሚዲያ ገጻቸው በሆነው "ትሩዝ ሶሻል" ላይ ባሰፈሩት መልዕክት፣ "ኢራን ሰላማዊ ተቃዋሚዎችን በጥይት የምትገድል ከሆነ አሜሪካ ተቃዋሚዎቹን ልትታደግ ተዘጋጅታለች" ሲሉ ገልጸዋል።
በግጭቱ የሰው ሕይወት መጥፋቱ ተነገረ
የፕሬዝዳንቱ ማስጠንቀቂያ የመጣው በኢራን የተለያዩ ከተሞች በተቀሰቀሰው ተቃውሞ የሰው ሕይወት መጥፋቱ በተሰማበት ወቅት ነው። እንደ ፋርስ የዜና አገልግሎት እና ሄንጋው የሰብዓዊ መብት ድርጅት ዘገባዎች ከሆነ፦
* በደቡብ ምዕራብ ኢራን ሎርድጋን ከተማ ሁለት ሰዎች ተገድለዋል።
* በአዝና እና ኩዳሽት ከተሞች ደግሞ ሌሎች ሦስት ሰዎች መሞታቸው ታውቋል።
የሀገሪቱ ባለስልጣናት እንደገለጹት፣ በሎርድጋን አካባቢ ፀረ-መንግሥት መፈክሮችን በማሰማት በሕዝብ ሕንፃዎች ላይ ድንጋይ ይወረወር ነበር።
በጸጥታ ኃይሎች እና በተቃዋሚዎች መካከል በተፈጠረ የተኩስ ልውውጥ በርካታ የፖሊስ አባላት መቁሰላቸውንም የመንግሥት መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
🧨የተቃውሞው መነሻ
ባለፈው ታህሳስ 28 በቴህራን ግራንድ ባዛር የጀመረው ይህ ተቃውሞ፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ሌሎች ከተሞች የተስፋፋ ሲሆን፣
ዋና መነሻውም፦
* የኢራን ገንዘብ (ሪያል) የመግዛት አቅም በከፍተኛ ሁኔታ ማሽቆልቆል።
* የኑሮ ውድነት እና የኢኮኖሚ ቀውስ መባባስ እንደሆነ ተገልጿል።
⚡️የመንግሥት ምላሽ
የኢራኑ ፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን በሕዝቡ ዘንድ ያለውን ቅሬታ አምነው ተቀብለዋል።
ፕሬዝዳንቱ መንግሥታቸው ለተፈጠረው የኢኮኖሚ ችግር ኃላፊነት እንደሚወስድ የገለጹ ሲሆን፣ ባለሥልጣናት እንደ አሜሪካ ያሉ የውጭ ኃይሎችን ከመውቀስ ይልቅ ለችግሩ መፍትሔ እንዲፈልጉ አሳስበዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ኢራን #አሜሪካ #ዶናልድትራምፕ #የኢኮኖሚቀውስ #የተቃውሞሰልፍ #ዓለምአቀፍዜና #ቴህራን #ሰብዓዊመብት