22 days ago
የ"ሸገሩ"፣ "የእነሆ መቆያው" እሸቴ አሰፋ!
#ethiopia | ባለፈው ሳምንት "እነሆ መቆያ" የተሰኘ መጽሐፉን ለንባብ ያበቃው፣ አንጋፋውና ስመ-ጥሩ ጋዜጠኛ እሸቴ አሰፋ (እሸቴ ከጃንሜዳ) ሐምሌ 19 ቀን 1953 ዓ.ም በሰሜን ሸዋ መንዝና ግሼ አውራጃ ተወለደ።
የአንደኛ ደረጃ ትምህርቱን በተወለደበት አካባቢ ራቤል የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ያጠናቀቀ ሲሆን፣ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ደግሞ በመሐል ሜዳ፣ በሆለታና በአቃቂ ተማሪ ቤቶች ተከታትሏል።
ገና በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እያለ በሚኒ-ሚዲያ በመሳተፍ የጋዜጠኝነት ፍቅሩን ያሳየው እሸቴ፣ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በቋንቋና ሥነ-ጽሑፍ የመጀመሪያ ዲግሪውን አግኝቷል።
ለመጀመሪያ ጊዜ ጽሑፉ የታተመለት በአዲስ ዘመን ጋዜጣ "አድማስ" አምድ ላይ ነበር ይላል - ለዚህ ጽሑፍ ዋነኛ ምንጭ አድርገን የተጠቀምነው የ"ተወዳጅ ሚዲያ" መረጃ።
በተለይም "የካቲት" መጽሔት ላይ እንደ ጳውሎስ ኞኞ፣ ስብሐት ገብረእግዚአብሔር፣ ብርሃኑ ዘርይሁን፣ ወጋየሁ ንጋቱ፣ ይድነቃቸው ተሰማና ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ያሉ ታላላቅ ሰዎችን ታሪክ በጥናት አስደግፎ በማቅረብ የአንባቢን ልብ መግዛት ችሏል።
በተለያዩ ዘርፎች ብዙ ውለታ የዋሉ ታላላቅ የሀገራችንን ሰብዕናዎችንም 'ቃለ-መጠይቅ' (Interview) አድርጓል።
በዚህ የጋዜጠኝነት ጉዞው ውስጥ የአጻጻፍና የጋዜጠኝነት ሙያዊ ዕውቀት የሰጡትንና እንደ መምህር የሚያያቸውን የመጽሔቷን ዋና አዘጋጅ አቶ ጸጋዬ ኃይሉ ተፈራን ምንጊዜም በታላቅ አክብሮት ያስታውሳል።
በአንድ ጊዜ በበርካታ ሚዲያዎች ላይ የመሥራት ልዩ ታታሪነት የነበረው እሸቴ፣ ከ1978 ዓ.ም ጀምሮ ለአምስት ዓመታት ያህል በለገዳዲ ሬዲዮ "የእሁድ ለአንዳፍታ" ፕሮግራም ላይ "እሸቴ ከጃንሜዳ" በሚል ስያሜ የገጠሪቱን ኢትዮጵያ ባህልና ውሎ የሚያሳዩ ማራኪ የሥነ-ቃል ስብስቦችን በራሱ አንደበት እያነበበ ለአድማጭ ያቀርብ ነበር።
በተያያዥነትም ከ1979 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በፍሪላንስ ጋዜጠኛነት በመቀጠር፣ በተለይ ታሪካዊና ተፈጥሯዊ አካባቢዎች ላይ ያተኮሩ የተለያዩ ባለ አንድ ሰዓት ዘጋቢ ፊልሞችን (ዶክመንተሪዎችን) አዘጋጅቷል።
ከእነዚህም መካከል ስለ ጣና ሐይቅ አድባራት የሠራውና አዲስ አበባ 100ኛ ዓመቷን ስታከብር ያቀረበው ባለ አንድ ሰዓት ተኩል ልዩ ፕሮግራም ተጠቃሽ ናቸው።
በ1987 ዓ.ም "ሪፖርተር" ጋዜጣ ሲመሠረት ከዋና መሥራቾቹ አንዱ የነበረ ሲሆን፣ ከ1989 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ የ"ሪፖርተር" ጋዜጣና መጽሔት ምክትል ዋና አዘጋጅና ዋና አዘጋጅ በመሆን ሙያዊና እውነተኛ መረጃ ላይ የተመሠረተ ጋዜጠኝነት እንዲሰፍን ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል።
ላለፉት አስራ አምስት ዓመታት ደግሞ በሸገር 102.1 ኤፍ ኤም ሬዲዮ በቅዳሜው "እነሆ መቆያ" መሰናዶው የዓለም መሪዎችን፣ ታዋቂ ሰዎችንና ታላላቅ የስለላ ተቋማትን፣ ታሪካዊ ክስተቶችን እና ሌሎችንም ጉዳዮች በበቂ ንባብና ማስረጃ አደራጅቶ በማቅረብ ከፍተኛ ተወዳጅነትን አትርፏል።
በአሁኑ ወቅትም በሸገር fm 102.1 ሬዲዮ ጣቢያ በዋና አዘጋጅነት እያገለገለ ይገኛል። ጋዜጠኛ እሸቴ አሰፋ ባለትዳርና የሁለት ልጆች አባት ነው።
ስለራሱ በአንደበቱ ከማውራት ይልቅ በሥራው መናገርን የሚመርጠው ይህ በሳል ጋዜጠኛ፣ ባለፉት ሠላሳ ዓመታት በሀገሪቱ ሚዲያ ታሪክ ውስጥ የራሱን የማይረሳ ደማቅ አሻራ አስቀምጧል። እናመሰግናለን፤ እሼ!
#ወይ_አዲስ_አበባ_on_Sheger_fm_102 .1 #sheger_fm_102 .1 #zefenenazemen #jafarbooks #radio #አዲስ_አበባ

Comments