23 days ago
🔥 እንኳን ለመስቀል ደንጌሳት በዓል አደረሳችሁ!
የክስታኔ እህትማማቾች ማህበር በየዓመቱ የሚያከብረውን የመስቀል ደንጌሳት በዓል በዚህ ዓመትም በድምቀት ለማክበር ዝግጅቱን አጠናቋል።
እሁድ፣ መስከረም 10 ቀን 2019 ዓ.ም.
ጦር ሐይሎች መኮንኖች ክበብ
ከቀኑ 6:00 ጀምሮ እስከ ምሽት
የበዓሉ ድምቀቶች፦
የባህል ጭፈራ
ደመራ
ባዛር
የባህላዊ ምግቦች
አይብ
ጎመን
ክትፎ
የተበጠበጠ ብርንዶ
እና ሌሎችም የበዓሉ ድምቀቶች ይጠብቃችኋል!
ብቻ እናንተ ኑ!
የእኛን ባህል፣ ወግና አንድነት በጋራ እናሳድግ።
የሀገራችንን በዓል ለትውልድ እናሳውቅ!
ኑ፣
መስቀልን አብረን እናክብር!
የመግቢያ ካርድ የሚገኘው፦
አማኑኤል ቤተ ክርስቲያን ፊት ለፊት፣ አይመለል ሕንፃ ውስጥ፣ 1ኛ ፎቅ፣ በጽ/ቤቱ ቢሮ
ወይም
በዕለቱ በጦር ሐይሎች መኮንኖች ክበብ መግቢያ በር ላይ ይገኛል።
እንገናኝ! እንደምር! እናክብር! 🔥
#መስቀል #ደንጌሳት #ክስታኔ #የክስታኔእህትማማቾች #ባህል #አንድነት #ኢትዮጵያ
12 months ago
አመት እስኪደርስ የሚያጓጓው በአል"አዳብና"
#ethiopia | የጉራጌ ልጃገረዶች እና የወጣት ወንዶች በዓል የሆነው አዳብና ለመጀመርያ ጌዜ በአዲስ አበባ ተከብሯል።
በክስታኔ ዓለም አቀፍ ወጣቶች ማኀበር እና በአክራሚ የሴቶች በጎ አድራጎት ማህበር የሚዘጋጀው አመታዊ የአዳብና በአል በዛሬው እለት ተከብሯል።
በጥምረት አዳብና በፌስቲቫል ደረጃ ለመጀመርያ ጊዜ በአዲስ አበባ ወዳጅነት ፓርክ የብሔሩ ተወላጆች፣ የአካባቢው አመራሮች እንዲሁም የባህልና ቱሪዝም አመራሮች በተገኙበት ተከብሯል።
ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ አዳብና በአዲስ አበባ በዛሬው እለት የተከበረ ሲሆን ባሳለፍነው ሳምንት ማለትም መስከረም 24/2018 ዓ.ም በጉራጌ ዞን በኬላ ከተማ በደማቅ ሁኔታ መከበሩ ይታወሳል።
የአዳብና ባህል የልጃገረዶችና ወጣት ወንዶች ጨዋታና መተጫጫ ስነስርዓት ሲሆን ከ800 ዓመታት በፊት በክስታኔ ቤተ-ጉራጌ አካባቢ ለዘመናት ሲከበር ከትውልድ ወደ ትውልድ የተሸጋገረ ባህል ነው።
አዳብና አንድም ባህላዊ ጨዋታ ነው፤ በሌላ በኩልም የትዳር አጋር ማፈላለጊያ ሆኖ ያገለግላል።
ይህ ስርዓት በሶዶ ክስታኔ ጉራጌ ማኅበረሰብ ዘንድ በየዓመቱ ከመስከረም 16 ጀምሮ እስከ ጥቅምት 5 ድረስ የሚዘልቅ ተወዳጅ የወጣቶች የባህል ጨዋታ ነው።
አዳብና አጋጣሚው የመተጫጫም ጭምር በመሆኑ ሴቷ በባህል አልባሳት እና የተለያዩ ጌጣጌጦች ትዋባለች።
ወንዱም ቢሆን በመረጣት ወጣት ተቀባይነት ለማግኘት ያስችለኛል ባለው መንገድ ዘንጦ መቅረብ ይጠበቅበታል።
አዳብና በክስታኔ ዓለም አቀፍ ወጣቶች ማህበር እና አክራሚ በጎ አድራጎት የሴቶች ማህበር በጋራ ያዘጋጁት ይህ ድንቅ የሆነ የአዳብና ባህል በማይዳሰስ የዓለም ቅርስነት በUNESCO እንዲመዘገብ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑ ተነግሯል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል

1 year ago
የጉራጌ ልጃገረዶች እና የወጣት ወንዶች በዓል የሆነው አዳብና በአዲስ አበባ ሊከበር ነው።
#fastmereja I አዳብና በክስታኔ ዓለም አቀፍ ወጣቶች ማኀበር እና አክራሚ የሴቶች በጎ አድራጎት ማህበር በጥምረት አዳብና በፌስቲቫል ደረጃ በአዲስ አበባ ወዳጅነት ፓርክ ለማክበር እንደተዘጋጁ ዛሬ መስከረም 09/2018 ዓ.ም በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ተገልጿል።
ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ አዳብና በአዲስ አበባ ጥቅምት 02/2018 ዓ.ም የሚከበር ሲሆን ቀደም ብሎ መስከረም 24/2018 ዓ.ም በጉራጌ ዞን በኬላ ከተማ በደማቅ ሁኔታ ለማክበር ዝግጅት እንደተደረገ ተነግሯል።
የአዳብና ባህል የልጃገረዶችና ወጣት ወንዶች ጨዋታና መተጫጫ ስነስርዓት ሲሆን 800 ዓመታት በፊት በክስታኔ ቤተ-ጉራጌ አካባቢ ለዘመናት ሲከበር ኖሯል።
አዳብና በከስታኔ ዓለም አቀፍ ወጣቶች ማህበር ይህ ድንቅ የሆነ የአዳብና ባህል በማይዳሰስ የዓለም ቅርስነት በUNESCO እንዲመዘገብ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑ ተገልጿል።
መላው ኢትዮጵያውያን መስከረም 24 ኬላ እና ጥቅምት 02 በአዲስ አበባ ወዳጅነት ፓርክ የሚከበረውን ፌስቲቫል ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪ ቀርበዋል።
#ኹነት #ማህበራዊ

"እጮኛ ፍለጋ"
አዳብና (የመተጫጫ በአል)
#ethiopia |የዘንድሮው የክስታኔ አዳብና በመዲናዋ አዲሰ አበባ ጨምር በሀገር ቤት በተለያዩ የገበያ ቦታዎችን ላይ በድምቀት እንደሚከበር ተነግሯል።
የዘንድሮው አዳብና ከመሰከረም 16 ጀምሮ እሰከ ጥቅምት አቦ የሚካሄድ ሲሆን ጥቅምት 2 ቀን 2018 ዓ/ ም በአዲሰ አበባ በወዳጅነት አደባባይ ይከበራል ተብሏል።
አዳብና 2018 ፌስቲቫል በአዲስ አበባ ሲዘጋጅ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።
በየዓመቱ የመስቀል በዓልን ምክንያት በማድረግ የሚዘጋጀው ይህ ፌስቲቫል በሀገር አቀፍ ደረጃ የዘንድሮው በአዲስ አበባ ለመጀመሪያ ጊዜ ጥቅምት 02/2018ዓ.ም በወዳጅነት ፓርክ ይደረጋል።
ዋናው የአዳብና ፌስቲቫል ከአዲስ አበባ በአንድ መቶ ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምትገኘው የደቡብ ሶዶ ዞን መቀመጫ በሆነችው በኬላ ከተማ እንደሚከናወን ተገልጿል።
አዳብና የጉራጌ ህብረተሰብ ቱባ ባህል ከሚባሉት ውስጥ አንዱ ሲሆን የወጣቶች በዓል እንደመሆኑ መጠን የመተጫጫም ባህል ነው።
አዳብና በክስታኔ ዓለም አቀፍ ወጣቶች ማህበር እና አክራሚ በጎ አድራጎት የሴቶች ማህበር በጋራ ያዘጋጁት ይህ ፌስቲቫል የቤተጉራጌ መነሻ እንደመሆኑ መጠን በዮኔስኮ በማይዳሰስ ቅርስነት ውስጥ ለማስመዝገብ ጥረት እየተደረገ ይገኛል ተብሏል።

Comments