2 months ago
የፓሪስ ኦሎምፒክ ኮከብ ጋቢ ቶማስ በአዲስ አበባ ሊትገኝ ነው!
#ethiopia | በአለም አትሌቲክስ አውድ ውስጥ ደማቅ ስም ያላት አሜሪካዊቷ የ200 ሜትር የኦሎምፒክ ሻምፒዮን ጋቢ ቶማስ፣ በኢትዮጵያ በሚካሄደው ታሪካዊ የግራንድ ፕሪክስ ውድድር ላይ እንደምትሳተፍ አረጋገጠች።
ታሪካዊ ውድድር በአዲስ አበባ
ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የምታስተናግደው የአንድ ቀን ዓለም አቀፍ የውድድር መድረክ (World Athletics Continental Tour) ሚያዝያ 10 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል። ይህ ውድድር የአለም የጥቁር ህዝቦች ኩራት በሆነችው አዲስ አበባ መካሄዱ ልዩ ትርጉም የሚሰጠው ሲሆን፣ የጋቢ ቶማስ መገኘት ደግሞ ውድድሩን በጉጉት እንዲጠበቅ አድርጎታል።
የጋቢ ቶማስ ድንቅ ስኬቶች
ጋቢ ቶማስ በዓለም አቀፍ መድረኮች ያስመዘገበቻቸው ውጤቶች በአጭሩ፦
በ200 ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት።
በዚሁ ኦሎምፒክ በ4x100 ሜትር እና በ4x400 ሜትር የሪሌ ውድድሮች ከአጋሮቿ ጋር ተጨማሪ ሁለት የወርቅ ሜዳሊያዎችን ለአሜሪካ አስገኝታለች።
በቡዳፔስት ዓለም ሻምፒዮና የብር እንዲሁም በቶኪዮ ኦሎምፒክ የነሐስ ሜዳሊያ አሸናፊ ናት።
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን (ኢአፌ) እንደገለጸው፣ የዚህች አንጋፋ አትሌት መምጣት ለኢትዮጵያ ስፖርት እድገትና ለቱሪዝም ዘርፉ ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ኢትዮfm #gabbythomas #addisababagrandprix #ethiopianathletics #paris2024champion #continentaltour #addisababa #ethiopia #athleticsnews

Comments