2 hours ago
በዩኒቨርሲቲዎች ስር ለሚተዳደሩ ማስተማሪያ ሆስፒታሎች የሚመደበው የሕክምና አገልግሎት በጀት ከመደበኛው የትምህርት በጀት ስሌት ቀመር ውጪ በተናጠል ተጣርቶ የበጀት ድጋፍ እንዲቀርበለት የሚያዘው ደንብ በስራ ላይ ውሏል።
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ለራስ-ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች ከመንግሥት የሚሰጠውን የብሎክ ግራንት የበጀት አፈጻጸም ለመደንገግ ያወጣው ደንብ ቁጥር 594/2018 በስራ ላይ ውሏል።
ደንቡ ተቋማቱ በፋይናንስ ራሳቸውን እስኪችሉ ድረስ በሂደት እየቀነሰ የሚሄድ ዓመታዊ የበጀት ድጋፍ የሚመደብበትን ሥርዓት ያካተተ ሲሆን፣ ዩኒቨርሲቲዎቹ ከተጨባጭ ነባራዊ ሁኔታዎቻቸውና ስትራቴጂካዊ ዕቅዶቻቸው በመነሳት በበጀታቸው በነፃነት እንዲጠቀሙና ተልዕኳቸውን በጥራት እንዲወጡ ማስቻልን ዓላማ ያደረገ መሆኑን ያስረዳል።
ደንቡ ለራስ-ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች የሚመደበው ዓመታዊ የብሎክ ግራንት እንደ አግባብነቱ ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ሲባል፣ የመግቢያ መስፈርቱን አሟልተው ነገር ግን የትምህርት ወጪያቸውን መሸፈን ለማይችሉ ተማሪዎች የሚደረግ የበጀት ድጋፍ ሊያካትት እንደሚችል ያስረዳል።
በተጨማሪም ዩኒቨርሲቲዎች በሚያስተዳድሯቸው ማስተማሪያ ሆስፒታሎች አማካኝነት፣ በሕግ አግባብ በነፃ ሊሰጡ ለሚገባቸው የሕክምና አገልግሎቶች እና በነፃ ማግኘት ለሚገባቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች የሚውል የበጀት ድጋፍ እንዲያገኙ ለማስቻልም ሊመደብ እንዲሚችል ይገልጻል።
እንዲሁም ዩኒቨርሲቲዎች የሚያከናውኗቸውን የምርምርና ጥናት፣ የማኅበረሰብ ጉድኝት አገልግሎት እንዲሁም ብቁ ተቋማዊ አቅምን ለመገንባት የሚያስፈልግ የፋይናንስ ድጋፍ ሊመደብ እንደሚችል ተደንግጓል።
በዚህ ደንብ መሠረት አጠቃላይ የራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች የበጀት ድልድል የግብዓት፣ የውጤትና የፍትሐዊነት መስፍርቶችን መሰረት የሚያደርግ ሲሆን ይህም
• የመማር-ማስተማር ሂደቱን መደበኛ ተማሪዎች ቁጥር፣
• የሳይንሳዊ ምርምር ውጤትና ተፅዕኖን፣
• የቴክኖሎጂ ሽግግርና ማህበረሰብ ጉድኝት ስራዎችን እንዲሁም
• ልዩ ድጋፍ የሚሹ ተማሪዎችን እና የተቋማቱን መልክዓ-ምድራዊ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ታሳቢ ያደርጋል።
ይህ የበጀት ማከፋፈያ ቀመር እንደ አስፈላጊነቱ በገንዘብ ሚኒስቴር እና በትምህርት ሚኒስቴር ትብብር የሚዘጋጅ ሲሆን፣ ወቅታዊ ሁኔታዎችን ለማጣጣም በየሁለት ዓመቱ ክለሳ ይደረግበታል።
በተለየ መልኩ፣ በዩኒቨርሲቲዎች ስር ለሚተዳደሩ ማስተማሪያ ሆስፒታሎች የሚመደበው የሕክምና አገልግሎት በጀት ከመደበኛው የትምህርት በጀት ስሌት ቀመር ውጪ በተናጠል ተጣርቶ የበጀት ድጋፍ እንደሚደረግለት ተደንግጓል።
ይህ ድጋፍ ሆስፒታሎቹ በሕግ አግባብ በነፃ ሊሰጡ ለሚገባቸው የሕክምና አገልግሎቶችና ተጠቃሚ ለሆኑ የኅብረተሰብ ክፍሎች የሚውል ሲሆን፤ ድልድሉም በሆስፒታሉ አገልግሎት ያገኙ ታካሚዎች ብዛት፣ የህክምና አልጋዎች ቁጥር፣ የአገልግሎቶቹ ውስብስብነት እንዲሁም ለመድኃኒትና ለአላቂ የሕክምና ቁሳቁሶች የሚወጣውን ወጪ መሠረት በማድረግ ይወሰናል።
በዚህም ማንኛውም ራስ-ገዝ ዩኒቨርሲቲ የሚያገኘው ዓመታዊ ድጋፍ አጠቃላይ የመማር-ማስተማርና የምርምር በጀቱን እንዲሁም ለማስተማሪያ ሆስፒታሎች በጥናት ላይ ተመስርቶ የሚመደበውን ልዩ በጀት በአንድ ላይ ያካተተ የተቀናጀ የብሎክ ግራንት ሆኖ ይቀርባል።
የበጀት ጥያቄ አቀራረብና አስተዳደርን በተመለከተ፣ ማንኛውም ራስ-ገዝ ዩኒቨርሲቲ ዓመታዊ የበጀት ጥያቄውን በየዓመቱ እስከ የካቲት ወር መጨረሻ ድረስ ለገንዘብ ሚኒስቴር ማቅረብ እንዳለበት እና የተፈቀደው በጀትም በቀጥታ ወደ ተቋማቱ ፈሰስ እንደሚደረግ ተመላክቷል።
የቁጥጥር ሥርዓቱን ለማጠናከርም ትምህርት ሚኒስቴር በቁልፍ ውጤት አመላካቾች ላይ የተመሠረተ የአፈጻጸም ውል በመፈራረም በዓመት ሁለት ጊዜ ሁለንተናዊ ግምገማ እንደሚያካሂድ ተደንግጓል።
በተጨማሪም የዩኒቨርሲቲዎቹ የብሎክ ግራንት ሒሳብ በፌደራል ዋና ኦዲተር እንደሚመረመርና የሒሳብ ሰነዶችም ቢያንስ ለአስር ዓመታት ተጠብቀው እንዲቆዩ በማድረግ ተጠያቂነትና ግልጽነት እንዲሰፍን ይደረጋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia

3 hours ago
የኤርትራ ኃይሎች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ
ከኢትዮጵያ ግዛት እንዲወጡ መንግሥት አስጠነቀቀ
የኤርትራ ጦር ወደ ትግራይ ክልል ገብቶ አዲግራት ከተማን መቆጣጠሩን ሲነገር፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ይህንን ድርጊት "ወረራ" ሲል በይፋ ኮንኗል። የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ወ/ሮ እናትዓለም መለሰ ለብሉምበርግ እንደተናገሩት፣ የኤርትራ ኃይሎች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከኢትዮጵያ ግዛት እንዲወጡ አሳስበዋል። ይህ መግለጫ የኤርትራ ጦር ሀገሪቱን በቀጥታ መውረሩን ያረጋገጠ ይፋዊ አቋም ነው።
ይህ ውጥረት የተፈጠረው ህወሓት ከሌሎች አማፂ ቡድኖች ጋር አብሮ አዲስ ጥቃት ከከፈተ በኋላ ነው። መንግሥት እንደሚለው፣ ኤርትራ እነዚህን አማፂያን ከጀርባ ስትደግፍ ቆይታ አሁን ደግሞ ጦሯን በቀጥታ በማስገባቷ ሁለቱ አገራት ወደ ቀጥተኛ ጦርነት ሊገቡ ይችላሉ የሚል ከፍተኛ ስጋት ፈጥሯል።
#ዳጉ_ጆርናል

RESPECT ❤️
በዕውነቱ ይነዝራል እስኪ የነዘረውውው ☹️
@Bisrat_Sport_433et
@Bisrat_Sport_433et የኩሩ ህዝቦች መኖሪያ የህብሬ ብሔር ቡቃያ የሰላም ተምሳሌት አርማ የቀለሞች ህብር ኢትዮጵያ በደም አሻራሽ አትሞ ህዝቦች ለሴጡን አደራ ለሕገ መንግስታችን ክብር ታጥቀን ቆሜናል በጋራ 🎵🎵🎵🎵🎵🎵 ሉሲዎቹ ከድሉ በኋላ በስታዲየም በመገኘት ቡድናችንን ሲያበረታቱ ከነበሩት የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን አባላት ጋር በጋራ ደስታቸውን አጣጥመዋል። @Bisrat_Sport_433et …

4 hours ago
የኤርትራ ኃይሎች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ
ከኢትዮጵያ ግዛት እንዲወጡ መንግሥት አስጠነቀቀ
የኤርትራ ጦር ወደ ትግራይ ክልል ገብቶ አዲግራት ከተማን መቆጣጠሩን ሲነገር፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ይህንን ድርጊት "ወረራ" ሲል በይፋ ኮንኗል። የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ወ/ሮ እናትዓለም መለሰ ለብሉምበርግ እንደተናገሩት፣ የኤርትራ ኃይሎች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከኢትዮጵያ ግዛት እንዲወጡ አሳስበዋል። ይህ መግለጫ የኤርትራ ጦር ሀገሪቱን በቀጥታ መውረሩን ያረጋገጠ ይፋዊ አቋም ነው።
ይህ ውጥረት የተፈጠረው ህወሓት ከሌሎች አማፂ ቡድኖች ጋር አብሮ አዲስ ጥቃት ከከፈተ በኋላ ነው። መንግሥት እንደሚለው፣ ኤርትራ እነዚህን አማፂያን ከጀርባ ስትደግፍ ቆይታ አሁን ደግሞ ጦሯን በቀጥታ በማስገባቷ ሁለቱ አገራት ወደ ቀጥተኛ ጦርነት ሊገቡ ይችላሉ የሚል ከፍተኛ ስጋት ፈጥሯል።
@Yenetube Fikerassefa

(ዘ-ሐበሻ ዜና) ACLED አሁን ባወጣው ሪፖርት መሠረት... የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ኤርትራን ወረራ ለመቀልበስ እና የህወሓት ኃይሎችን ለማስወገድ ጠንካራ ወታደራዊ እርምጃዎችን በተለያዩ ግንባሮች እየወሰደ ይገኛል። የኤርትራ ኃይሎች በዛላምበሳ በኩል ድንበር ጥሰው በማዕከላዊ ትግራይ ዞን ወደሚገኘው አዲግራት-ዕዳጋ ሐሙስ መስመር ያመሩ ሲሆን፣ እነዚህ ኃይሎች በተሽከርካሪ ወደ ዕዳጋ ሐሙስ በመጓዝ ላይ እያሉ 'ጓዳ' በተባለ ስፍራ በመከላከያ ሠራዊት ድሮኖች ከባድ ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል።
በሌላ ግንባር ደግሞ የመከላከያ ሠራዊት ከመቀሌ በሰሜን ምስራቅ አቅጣጫ 35 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የምትገኘውን የአጉላ ከተማን ሙሉ በሙሉ በቁጥጥሩ ሥር ማዋሉን አክሊድ አስታውቋል። እንደ ሪፖርቱ ገለጻ ሠራዊቱ ይህንን ድ*ል *ያስመዘገበው ከህወሓት ታጣቂዎች ጋር በመድፍ እና በድሮን የታገዘ ከባድ ውጊያ ካደረገ በኋላ ነው። በተጨማሪም በትግራይ ጽሊሞይ (አካባቢ በተከዜ ወንዝ አቅራቢያ በመከላከያ እና በህወሓት ኃይሎች መካከል አዲስ ዙር የትጥቅ ግጭት ማገርሸቱን ካወጣው ሪፖርት ላይ ተመልክተናል።
እነዚህ የዛሬ ኦክቶበር 7 ቀን 2026 ወታደራዊ ክንውኖች የሚያሳዩት የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በአንድ ጊዜ የኤርትራን መደበኛ ጦር እና የህወሓት ታጣቂዎችን በተለያዩ ግንባሮች እየገጠመ መሆኑን ነው። ወታደራዊ ተንታኞች ለዘ-ሐበሻ እንደገለጹት መከላከያ የአጉላን ከተማ መቆጣጠሩ ወደ መቀሌ ያለውን የጸጥታ ቀለበት ይበልጥ ያጠናክረዋል። መንግስት የኤርትራን ድርጊት በይፋ "ወረራ" ብሎ ከፈረጀ በኋላ ወዲያውኑ ድንበር ጥሰው የገቡ ኃይሎችን በድሮን መምታቱ፣ የኢትዮጵያ መንግስት ሉዓላዊነቱን ለማስከበር ወደ ቀጥተኛ የአጸፋ እርምጃ መግባቱን በተግባር ያረጋግጣል።
እንደ ወታደራዊ ተንታኞች ከሆነ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የአየር ላይ የበላይነቱን በመጠቀም በህወሓት ላይ የወሰደውን የማጥቃት እርምጃ፣ አሁን በቀጥታ ወደ ኤርትራ ወራሪ ኃይሎች አዙሮታል። ይህ እርምጃ የኢትዮጵያ ጦር መሬት ላይ ያለውን ወታደራዊ ሚዛን በፍጥነት እየቀየረው መሆኑን ያሳያል።
ይህ ወታደራዊ ውጥረት በቀጣይ ቀናት ምን መልክ ሊይዝ ይችላል ብላችሁ ታስባላችሁ?
በሌላ ግንባር ደግሞ የመከላከያ ሠራዊት ከመቀሌ በሰሜን ምስራቅ አቅጣጫ 35 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የምትገኘውን የአጉላ ከተማን ሙሉ በሙሉ በቁጥጥሩ ሥር ማዋሉን አክሊድ አስታውቋል። እንደ ሪፖርቱ ገለጻ ሠራዊቱ ይህንን ድ*ል *ያስመዘገበው ከህወሓት ታጣቂዎች ጋር በመድፍ እና በድሮን የታገዘ ከባድ ውጊያ ካደረገ በኋላ ነው። በተጨማሪም በትግራይ ጽሊሞይ (አካባቢ በተከዜ ወንዝ አቅራቢያ በመከላከያ እና በህወሓት ኃይሎች መካከል አዲስ ዙር የትጥቅ ግጭት ማገርሸቱን ካወጣው ሪፖርት ላይ ተመልክተናል።
እነዚህ የዛሬ ኦክቶበር 7 ቀን 2026 ወታደራዊ ክንውኖች የሚያሳዩት የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በአንድ ጊዜ የኤርትራን መደበኛ ጦር እና የህወሓት ታጣቂዎችን በተለያዩ ግንባሮች እየገጠመ መሆኑን ነው። ወታደራዊ ተንታኞች ለዘ-ሐበሻ እንደገለጹት መከላከያ የአጉላን ከተማ መቆጣጠሩ ወደ መቀሌ ያለውን የጸጥታ ቀለበት ይበልጥ ያጠናክረዋል። መንግስት የኤርትራን ድርጊት በይፋ "ወረራ" ብሎ ከፈረጀ በኋላ ወዲያውኑ ድንበር ጥሰው የገቡ ኃይሎችን በድሮን መምታቱ፣ የኢትዮጵያ መንግስት ሉዓላዊነቱን ለማስከበር ወደ ቀጥተኛ የአጸፋ እርምጃ መግባቱን በተግባር ያረጋግጣል።
እንደ ወታደራዊ ተንታኞች ከሆነ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የአየር ላይ የበላይነቱን በመጠቀም በህወሓት ላይ የወሰደውን የማጥቃት እርምጃ፣ አሁን በቀጥታ ወደ ኤርትራ ወራሪ ኃይሎች አዙሮታል። ይህ እርምጃ የኢትዮጵያ ጦር መሬት ላይ ያለውን ወታደራዊ ሚዛን በፍጥነት እየቀየረው መሆኑን ያሳያል።
ይህ ወታደራዊ ውጥረት በቀጣይ ቀናት ምን መልክ ሊይዝ ይችላል ብላችሁ ታስባላችሁ?
4 hours ago
የኤርትራ ኃይሎች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ
ከኢትዮጵያ ግዛት እንዲወጡ መንግሥት አስጠነቀቀ
የኤርትራ ጦር ወደ ትግራይ ክልል ገብቶ አዲግራት ከተማን መቆጣጠሩን ሲነገር፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ይህንን ድርጊት "ወረራ" ሲል በይፋ ኮንኗል። የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ወ/ሮ እናትዓለም መለሰ ለብሉምበርግ እንደተናገሩት፣ የኤርትራ ኃይሎች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከኢትዮጵያ ግዛት እንዲወጡ አሳስበዋል። ይህ መግለጫ የኤርትራ ጦር ሀገሪቱን በቀጥታ መውረሩን ያረጋገጠ ይፋዊ አቋም ነው።
ይህ ውጥረት የተፈጠረው ህወሓት ከሌሎች አማፂ ቡድኖች ጋር አብሮ አዲስ ጥቃት ከከፈተ በኋላ ነው። መንግሥት እንደሚለው፣ ኤርትራ እነዚህን አማፂያን ከጀርባ ስትደግፍ ቆይታ አሁን ደግሞ ጦሯን በቀጥታ በማስገባቷ ሁለቱ አገራት ወደ ቀጥተኛ ጦርነት ሊገቡ ይችላሉ የሚል ከፍተኛ ስጋት ፈጥሯል።
Seledadotio

5 hours ago
#ችሎት
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ በማጽናት በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙት የኢህአፓ አባላት የዋስትና መብት እንዲከበር ብያኔ ሰጠ።
በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙት የኢህአፓ አባላት የዋስትና ጉዳይ በዳኞች ፈረቃ መቀያየርና መዝገብ ባለመቅረቡ ምክንያት በተደጋጋሚ ተለዋጭ ቀጠሮ ሲሰጥበት መቆየቱ ይታወሳል።
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የስር ፍርድ ቤት የዋስትና ውሳኔ ሊጸና ይገባል ወይስ አይገባም፤ እንዲሁም ለፖሊስ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ያስፈልጋል ወይስ አያስፈልግም የሚለውን ለመመርመር የፌደራል ፖሊስ ያደራጀውን የምርመራ መዝገብ አስቀርቦ ሲመለከት ቆይቷል።
ጉዳዩን ሲመለከት የቆየው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በዛሬው ዕለት በዋለው ችሎት፣ የስር ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ ሙሉ በሙሉ አጽንቷል።
በዚህም መሠረት በሽብር ተግባር ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙት አቶ ይስሓቅ ወልዳይ፣ አቶ አበበ አካሉ እና ጠበቃ አቶ አበራ ንጉሥ የዋስትና መብታቸው ተከብሮ ከእስር እንዲፈቱ ብያኔ መሰጠቱን ጠበቃቸው አቶ ሰለሞን ገዛኸኝ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት፣ ነሐሴ 29 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት፣ ፖሊስ የፎረንሲክ ውጤቶችን ለመጠበቅና ተጨማሪ ምስክሮችን ለመስማት በሚል የጠየቀውን የ14 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ውድቅ በማድረግ ተጠርጣሪዎቹ እያንዳንዳቸው በ50,000 (ሃምሳ ሺህ) ብር የገንዘብ ዋስትና ከእስር እንዲፈቱ ውሳኔ መስጠቱ ይታወሳል።
የፌዴራል ፖሊስ የተሰጠውን የፍርድ ቤት ውሳኔ በመቃወም ይግባኝ ማለቱን ተከትሎ ተጠርጣሪዎቹ ጉዳያቸውን እስከዛሬ መስከረም 27/2019 ዓም ድረስ በእስር ላይ ሆነው ሲከታተሉ ቆይተዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ/ም
@tikvahethiopia #ችሎት በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙት የኢሕአፓ አባላት የዋስትና ጉዳይ ዛሬም ውሳኔ ሳያገኝ ለአርብ ተቀጠረ። የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የስር ፍርድ ቤት የሰጠው የዋስትና ውሳኔ ሊጸና ይገባል ወይስ አይገባም? እንዲሁም ለፖሊስ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ያስፈልጋል ወይስ አያስፈልግም? የሚሉትን ነጥቦች ለመመልከት የፌደራል ፖሊስ የምርመራ መዝገብ እንዲቀርብለት ማዘዙ ይታወሳል። ይሁን…

በደቡብ ሱዳን የምግብ ክምችት በመቀነሱ የሰብዓዊ ቀውስ ተባብሶ መቀጠሉ ተሰምቷል
መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) በየሳምንቱ 3ሺህ ገደማ የሚሆኑ ስደተኞች ከሱዳን ወደ ደቡብ ሱዳን እንደሚሻገሩ ተገልጿል።
ከእነዚህ ስደተኞች አብዛኞቹ ለረሃብ የተጋለጡ መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን ሆኖም በደቡብ ሱዳን ያለው የምግብ ድጋፍ እየተሟጠጠ መሆኑ ተነግሯል።
እንደ ዓለም የምግብ ፕሮግራም መረጃ ተጨማሪ ድጋፍ ማግኘት ካልተቻለ እስከ መጪው ጥቅምት ወር ድረስ ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ለአስከፊ የምግብ እጥረት ሊጋለጡ ይችላሉ።
በላይኛው የናይል ግዛት የሚገኘው የተቋሙ ዋና ማዕከል ላይ የሚገኘው የምግብ ክምችት ባለፈው ዓመት በዚህ ወቅት ከነበረበት 10ሺህ ሜትሪክ ቶን አሁን ከ 300 ቶን በታች ዝቅ ማለቱ ተገልጿል።
ዘገባው የአልጀዚራ ነው
#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

Sponsored by
Surafel
5 hours ago
የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴር‼️
የኢትዮጵያ መንግስት ከጠቅላይ ሚኒስትሩ እስከ ከፍተኛ ወታደራዊ እና የፖለቲካ ባለስልጣናት ድረስ - "የባህር በር ሉዓላዊ መዳረሻ" የሚለውን ለማግኘት በኤርትራ ላይ ግልጽ ጦርነት እንደሚጀምር በግልጽ ሲናገር ቆይቷል ብለዋል።
በሰሜናዊው የኢትዮጵያ ክፍል በተነሳው ጦርነት ምክንያት በማድረግ ከፍተኛ ጄኔራሎች "... ጥቃቱን ስንጀምር በትግራይ አናቆምም፣ሌላኛው ጄኔራል ደግሞ "መቀሌ የሚቆም አይደለም የመጨረሻው መድረሻችን አሰብ ነው" ሲሉ ተደምጠዋል ብለዋል።
ይህ ሂደት አለምአቀፍ ህግን በግልጽ ይጥሳል ያሉ ሲሆን የኤርትራ ሰራዊት በዛሬው ዕለት ወደ ትግራይ መግባቱን በተመለከተ ግን ያሉት ነገር የለም።

የሱዳኑ አል ቡርሃን ድርድርን ውድቅ በማድረግ ከፈጥኖ ደራሽ ኃይል እጅ ሁሉንም ግዛቶች ለማስመለስ ቃል ገቡ
መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) የሱዳን ጦር አዛዥ አብደል ፋታህ አል ቡርሃን ለሶስት ዓመት ተኩል የዘለቀውን ጦርነት ለማቆም የሚደረገውን ድርድር ውድቅ በማድረግ በፈጣን ደራሽ ኃይሎች ቁጥጥር ስር ያለውን እያንዳንዷን ስንዝር መሬት በኃይል ለማስመለስ ቃል መግባታቸው ተዘግቧል።
እንደ ሱዳን ዜና ወኪል ዘገባ አል ቡርሃን ይህን አስተያየት የሰጡት ማክሰኞ ዕለት በሰሜን ሱዳን ሜሮዌ በተባለ አካባቢ በሚገኘው መንደር 5'ለተሰበሰቡ ሰዎች ንግግር ባደረጉበት ወቅት ነው።
ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ከሱዳን ምድር እስኪወገዱ ድረስ "ወታደራዊው አማራጭ" እንደሚቀጥልም ተናግረዋል።
ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉን ወደ ሱዳን ብሔራዊ ጦር ለማዋሃድ በነበረው እቅድ ዙሪያ የቡድኖቹ መሪዎች መስማማት ባለመቻላቸው ምክንያት ሁለቱ አካላት ከእ.ኤ.አ 2023 ጀምሮ እየተዋጉ ይገኛሉ።
ዘገባው የአልጀዚራ ነው
#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) የሱዳን ጦር አዛዥ አብደል ፋታህ አል ቡርሃን ለሶስት ዓመት ተኩል የዘለቀውን ጦርነት ለማቆም የሚደረገውን ድርድር ውድቅ በማድረግ በፈጣን ደራሽ ኃይሎች ቁጥጥር ስር ያለውን እያንዳንዷን ስንዝር መሬት በኃይል ለማስመለስ ቃል መግባታቸው ተዘግቧል።
እንደ ሱዳን ዜና ወኪል ዘገባ አል ቡርሃን ይህን አስተያየት የሰጡት ማክሰኞ ዕለት በሰሜን ሱዳን ሜሮዌ በተባለ አካባቢ በሚገኘው መንደር 5'ለተሰበሰቡ ሰዎች ንግግር ባደረጉበት ወቅት ነው።
ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ከሱዳን ምድር እስኪወገዱ ድረስ "ወታደራዊው አማራጭ" እንደሚቀጥልም ተናግረዋል።
ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉን ወደ ሱዳን ብሔራዊ ጦር ለማዋሃድ በነበረው እቅድ ዙሪያ የቡድኖቹ መሪዎች መስማማት ባለመቻላቸው ምክንያት ሁለቱ አካላት ከእ.ኤ.አ 2023 ጀምሮ እየተዋጉ ይገኛሉ።
ዘገባው የአልጀዚራ ነው
#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
Sponsored by
Surafel
5 hours ago
⭕️የሸገር ከተማው ተስፈኛ አጥቂ ዳዊት ካሳው ከቤልጂየም ክለብ የሙከራ ዕድል አገኘ
👇🏽
ዳዊት ካሳው ከቅርብ ጊዜያት ወደህ በሀገራችን እግር ኳስ ከተመለከትናቸው ተስፈኛ ተጫዋቾች መካከል አንዱ ነው።
የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ከ22 ዓመት በኋላ ወደ አፍሪካ መድረክ ሲመለስ ሰባት ግቦችን በማስቆጠር ራሱን ከስፖርት ቤተሰቡ ጋር ያስተዋወቀው ወጣቱ አጥቂ ፣ የቤልጂየም ጁፕሊየር ፕሮ ሊግ ክለብ ለሙከራ እንደፈለገው ሶከር ኢትዮጵያ አስነብቧል።
Nordic Sky Agencyን ዋቢ ያደረገው ዘገባው ኤጄንሲው ለጊዜው የክለቡን ስም መጠቅስ እንዳልፈለገ ጠቁሟል።
የቪዛ ሂደቱ እና የሸገር ከተማ ፈቃድ ማስፈለጉ ደግሞ ክለቡን ይፋ ላለማድረግ በምክንያትነት ተጠቅሷል። ሁኔታዎች ሲጠናቀቁም ዳዊት የሚሄድበት ክለብ እና ቀጣይ ሂደቶች ይፋ እንደሚሆኑ ፅፏል።
ከባህር ዳር ከተማ ፕሮጀክት የእግር ኳስ መነሻውን ያደረገው ዳዊት በስሪ ፖይንት አካዳሚ ቆይታ አድርጓል።
ዳዊት ካሳው በአሁኑ ሰዓት ለ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን እና በሀገሪቱ ትልቁ የሊግ ዕርከን ለሚሳተፈው ሸገር ከተማ በመጫወት ላይ ይገኛል።
በአንተነህ ዋለልኝ
@Bisrat_Sport_433et @Bisrat_Sport_433et

ኤርትራ "ኢትዮጵያ ራስን በመከላከል ስም ልትወረኝ ነው" ስትል ከሰሰች
#fastmereja I የኤርትራ መንግሥት ፕሬስ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው፣ የኢትዮጵያ መንግሥት "ሉዓላዊ የባህር በር ማግኘት" እና የባህርኃይል አቅምን ለመገንባት በሚል ሽፋን በኤርትራ ላይ የጥቃት ጦርነት ለመክፈት እንቅስቃሴ እያደረገ ነው አለ። የኤርትራ መንግሥት ቃለ አቀባይ የማነ ገብረመስቀል ከሰዓታት በፊት እንደገለጹት፣ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት እና ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች በሰሜናዊው የኢትዮጵያ ክፍል ከተከሰተው ግጭት ጋር ተያይዞ በኤርትራ ላይ የሐሰት ውንጀላዎችን በመሰንዘር አጀንዳቸውን በ"ራስን የመከላከል" ስም ለመሸፈን እየሞከሩ ነው ብለዋል።
በመግለጫው እንደሰፈረው፣ በቅርብ ሳምንታት ውስጥ የተሰሙ ከፍተኛ የሰራዊት ጄኔራሎች አስተያየቶች የኢትዮጵያን እውነተኛ አላማ የሚያሳዩ ናቸው። በተለይም አንድ ከፍተኛ ጄኔራል ለአገር ውስጥ ሚዲያ በሰጡት ቃል "ዘመቻውን ስንጀምር ትግራይ ላይ አንቆምም... ዋናው አላማችን ባንዲራችንን ቀይ ባህር ላይ ማቆም ነው" ማለታቸው አሳሳቢ መሆኑን የኤርትራ መንግሥት አመልክቷል። እንዲሁም "መቀሌ ማቆሚያ አይደለችም፣ የመጨረሻ መድረሻችን አሰብ ነው" የሚሉ ንግግሮች የኢትዮጵያን እቅድ ግልጽ የሚያደርጉ እንደሆኑ ገልጿል።
የኢትዮጵያ መንግሥት ሆን ብሎ ጦርነቱን በራስን መከላከል ስም ለመሸፈን የሚደረገው ጥረት ቀባይነት የሌለው እና ክልላዊ ጸጥታን አደጋ ላይ የሚጥል ነው ሲል የኤርትራው ቃለ አቀባይ ማነ ገብረመስቀል በመግለጫቸው ገልጿል።

ሰበር መረጃ❗
የኤርትራ ጦር ወደ ትግራይ ክልል ይበልጥ ጠልቆ በመግባት ከመቀሌ ቀጥላ ክልሉ ሁለተኛዋ ትልቅ ከተማ የሆነችውን አዲግራትን መቆጣጠሩን ተከትሎ፣ የኢትዮጵያ መንግስት የኤርትራን ድርጊት "ወረራ" ሲል በይፋ ኮነነ።
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ወ/ሮ እናትዓለም መለሰ ለብሉምበርግ የዜና አውታር እንደተናገሩት፣ "በትግራይ ውስጥ የሚንቀሳቀሱት የኤርትራ ኃይሎች ያለምንም የጊዜ ገደብ ከኢትዮጵያ ሉዓላዊ ግዛት ለቀው መውጣት አለባቸው" በማለት የመንግስትን ጥብቅ አቋም አንጸባርቀዋል። ምንም እንኳን የኤርትራ ጦር በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ መኖሩ ከዚህ ቀደም በከፍተኛ የፖለቲካ እና የወታደራዊ መኮንኖች ሲነገር ቢቆይም፣ የሚኒስትሯ የዛሬው መግለጫ ግን ኤርትራ ጦሯን በቀጥታ በማስገባት ሉዓላዊ አገር መውረሯን የሚያረጋግጥ "ይፋዊ የመንግስት ማረጋገጫ" ሆኖ ተመዝግቧል።

6 hours ago
የኤርትራ ጦር አዲግራት ከተማ ቢገባም
👉 ኤርትራ አስተባብላለች
የኢትዮጵያ መንግሥት ጦር ከአዲግራት ወደ መቀሌ ይጓዝ የነበረ የኤርትራ ጦር ቅፍለትን በሰዉ አልባ አዉሮፕላን መምታቱ ተነገረ።
የኤርትራ ጦር አዲግራት ከተማ ከገባ አራት ቀናት እንዳለፈዉ ነዋሪዎችና የከተማይቱ ባለሥልጣትናት አስታወቁ።ኤርትራ አስተባብላለች።ዉቅሮ አካባቢ የከባድ መሳሪያ ተኩስ መሰማቱ ተነግሯልም።

የጥገና ሥራ ለማከናወን ነገ ኃይል የሚቋረጥባቸ አካባቢዎች እንደሚኖሩ ተገለፀ።
መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) ነገ መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ.ም የጥገና ሥራ ለማከናወን የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥባቸው አካባቢዎችን የኢትዮጱያ ኤሌትሪክ አገልግሎት አስታውቋል።
ከጠዋቱ 2፡30-11፡00
👉ጅንካ፣ ደቡብ አሪ፣ ማሌ ወረዳ እና አካባቢው፣
ከጠዋቱ 12፡00-2፡00
👉አፋር ሎጊያ፣ ሚሌ፣ኤሊ ውሃ፣ አዳይቱ፣ አዳር፣ ካሳጊታ፣ ጠሩ እና አካባቢው የኃይል አቅርቦት ይቋረጣል፡፡
ስለሆነም በአካባቢው የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻችን ይህንኑ በመገንዘብ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ በአክብሮት እናሳውቃለን ሲል አገልግሎቱ ገልፃል
#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) ነገ መስከረም 28 ቀን 2019 ዓ.ም የጥገና ሥራ ለማከናወን የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥባቸው አካባቢዎችን የኢትዮጱያ ኤሌትሪክ አገልግሎት አስታውቋል።
ከጠዋቱ 2፡30-11፡00
👉ጅንካ፣ ደቡብ አሪ፣ ማሌ ወረዳ እና አካባቢው፣
ከጠዋቱ 12፡00-2፡00
👉አፋር ሎጊያ፣ ሚሌ፣ኤሊ ውሃ፣ አዳይቱ፣ አዳር፣ ካሳጊታ፣ ጠሩ እና አካባቢው የኃይል አቅርቦት ይቋረጣል፡፡
ስለሆነም በአካባቢው የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻችን ይህንኑ በመገንዘብ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ በአክብሮት እናሳውቃለን ሲል አገልግሎቱ ገልፃል
#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ
6 hours ago
ኢትዮጵያ ውስጥ የኤርትራ ጦር ድንበር ጥሶ ገብቷል መባሉን ተከትሎ የዜጎች የተቃውሞ ድምፅ እየተሰማ ነው
#fastmereja I የኤርትራ ጦር የኢትዮጵያን ድንበር ጥሶ ወደ ሀገር ውስጥ ገብቷል በሚል በተስፋፋው መረጃ እና የተከሰተውን ሁኔታ አስመልክቶ በርካታ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ ተቃውሞ እያሰሙ መሆናቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። በወቅታዊው ጉዳይ ላይ ስጋታቸውን የገለጹት ዜጎች፣ የሀገሪቱ ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት በግልጽ እንደተደፈረ በመጥቀስ ጦሩ በአስቸኳይ ከኢትዮጵያ መሬት እንዲወጣ ጥሪ እያቀረቡ ይገኛሉ።
የተከሰተውን አሳሳቢ ሁኔታ አስመልክቶ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያ መድረኮች ላይ እየተሰሙ ያሉ ድምጾች እንደሚያሳዩት፣ ዜጎች የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት መጠበቅ የሁሉንም ዜጋ ቀዳሚ ሃላፊነት መሆኑን በማስታወስ የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት በአፋጣኝ እጅግ ጥብቅና ግልጽ የሆነ ምላሽ እንዲሰጡበት አጥብቀው እየጠየቁ ይገኛሉ። የድንበር ጥሰቱ በሁለቱ አገሮች መካከል ያለውን አንጻራዊ ሰላም ሊያናጋው ይችላል የሚል ስጋትም በህብረተሰቡ ዘንድ ጎልቶ እየታየ ነው።
እስካሁን ባለው ሁኔታ ጉዳዩን አስመልክቶ ከፌዴራል መንግስትም ሆነ ከሚመለከታቸው የጸጥታ አካላት በይፋ የተሰጠ አጠቃላይ መግለጫ ያለመኖር ቢታወቅም፣ በሀገር ውስጥ ያለው የህዝብ ቁጣና ስጋት እየጨመረ መምጣቱን ከወጡት መረጃዎች ለመረዳት ተችሏል።

7 hours ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የኤርትራ ጦር ወደ ትግራይ ክልል ይበልጥ ጠልቆ በመግባት ከመቀሌ ቀጥላ ክልሉ ሁለተኛዋ ትልቅ ከተማ የሆነችውን አዲግራትን መቆጣጠሩን ተከትሎ፣ የኢትዮጵያ መንግስት የኤርትራን ድርጊት "ወረራ" ሲል በይፋ ኮነነ።
የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ወ/ሮ እናትዓለም መለሰ ለብሉምበርግ የዜና አውታር እንደተናገሩት፣ "በትግራይ ውስጥ የሚንቀሳቀሱት የኤርትራ ኃይሎች ያለምንም የጊዜ ገደብ ከኢትዮጵያ ሉዓላዊ ግዛት ለቀው መውጣት አለባቸው" በማለት የመንግስትን ጥብቅ አቋም አንጸባርቀዋል። ምንም እንኳን የኤርትራ ጦር በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ መኖሩ ከዚህ ቀደም በከፍተኛ የፖለቲካ እና የወታደራዊ መኮንኖች ሲነገር ቢቆይም፣ የሚኒስትሯ የዛሬው መግለጫ ግን ኤርትራ ጦሯን በቀጥታ በማስገባት ሉዓላዊ አገር መውረሯን የሚያረጋግጥ "ይፋዊ የመንግስት ማረጋገጫ" ሆኖ ተመዝግቧል።
ይህ ወታደራዊ ውጥረት ያገረሸው፣ ከ2014ቱ የትግራይ ጦርነት ማብቃት በኋላ ከፌደራል መንግስት ጋር ዳግም መቃቃር ውስጥ የገባው ህወሓት፣ ከመስከረም 13 ቀን ጀምሮ አዲስ ወታደራዊ ጥቃት መክፈቱን ተከትሎ ነው። ህወሓት ይህንን ጥቃት የከፈተው በአማራ ክልል ከሚንቀሳቀሰው 'AFN*M' እና በኦሮሚያ ከሚንቀሳቀሰው የኦሮ*ሞ ነጻነት ሠ*ራዊት (O*LA) ጨምሮ ከስድስት ሌሎች አማፂ ቡድኖች ጋር አዲስ ወታደራዊ ጥምረት ከፈጠረ በኋላ ነው።
መንግስት እንደሚከሰው፣ የኤርትራ መንግስት ይህንን የኢትዮጵያ አማፂያን ጥምረት በተለይም ህወሓትን በስተጀርባ ስትደግፍ ቆይታለች። እንደ መንግስት ትንተና የ"አስመራ ስትራቴጂ የራሷን ጦር ሳታስገባ፣ በእጅ አዙር አማፂያኑን በመደገፍ የኢትዮጵያን መንግስት ማተራመስ እና የመከላከያ ሠራዊቱን አቅም ማዳከም ነበር። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አቅም ከኤርትራ ጦር እጅግ የገዘፈ በመሆኑ፣ አስመራ ይህንን የእጅ አዙር የከበባ ስትራቴጂን እንደ ዋነኛ መከላከያዋ አድርጋ ወስዳው ነበር።"
የፖለቲካ ተንታኞች እንደሚሉት "በአሁኑ ወቅት አዲስ አበባ ድንበሯን የመጠበቅ እና ሉዓላዊነቷን የማስከበር እጅግ ፈታኝ አጣብቂኝ ውስጥ ትገኛለች። የውጭ አገር ጦር በዚህ ደረጃ ወደ አገር ውስጥ ጠልቆ መግባቱ፣ የቆየውን ፖለቲካዊ ስጋት ወደ አስቸኳይ ብሔራዊ አደጋ የቀየረው ሲሆን፣ የኤርትራ እርምጃም ሁለቱን አገራት ወደ ለየለት ቀጥተኛ ጦርነት ይበልጥ አቅርቧቸዋል።"

የኢሚግሬሽን እና የ"ፋይዳ" ሲስተሞችን ለማስተሳሰር ንግግር ተጀመረ
መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት እና የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም (ፋይዳ) አገልግሎቶቻቸውን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ለማስተሳሰርና የተቀናጀ አሰራር ለመዘርጋት የሚያስችላቸውን ንግግር ጀምረዋል።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት እና የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዮዳሄ አርዓያስላሴ በሁለቱ ተቋማት መካከል በሚከናወነው የሲስተም ትስስር ዙሪያ የጋራ ግምገማ ማድረጋቸው ተገልጿል።
ይህ የተጀመረው የሲስተም ትስስር ንግግር ከግብ ሲደርስ ዜጎች ለፓስፖርትም ሆነ ለሌሎች ተያያዥ አገልግሎቶች በተደጋጋሚ የአሻራና የገጽታመረጃ መስጠት አያስፈልጋቸውም ተብሏል።
በውይይቱ ወቅት እንደተገለጸው ይህ የቴክኖሎጂ ውህደት ሀገሪቱ ለጀመረችው የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ትልቅ አቅም የሚፈጥር ሲሆን ተገልጋዮች የፋይዳ ስርአትን በመጠቀም ፈጣን እና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኙ ያስችላል።

የኤርትራ ወታደሮች ላይ የድሮን ጥቃት ተፈጸመ ተባለ!
-መረጃውን ከገለልተኛ ወገን ማረጋገጥ ግን አልተቻለም
በትግራይ ምስራቃዊ ዞን ከዕዳጋ ሓሙስ ወደ አፅቢ በሚወስደው መንገድ ይጓዙ የነበሩ የኤርትራ ወታደሮች ዕዳጋ ዓርቢ በተባለ ቦታ ሲደርሱ የድሮን ጥቃት እንደተፈጸመባቸው የትግራይ የሰላም ኃይል አንድ ወታደራዊ አዛዥ ገለጹ። የኤርትራ ወታደሮች በዛሬው ዕለት ከዛላምበሳ አቅጣጫ የዓዲ ግራት ከተማን ጥሰው ዕዳጋ ሐሙስ ከተማ መግባታቸውን ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ የትግራይ የሰላም ኃይል አዛዥ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።
በምዕራባዊ የትግራይ ክፍልም የኤርትራ ወታደሮች በሸራሮና ሽረ እንዳስላሰ ከተሞች መሐል በሚገኙ ዓዲ ነብሪ ኢድና ዛግር ወደ ተባሉ አካባቢዎች መግባታቸውንም ገልጸዋል።
አንድ የዓዲ ግራት ከተማ ነዋሪ በበኩላቸው የኤርትራ ወታደዎች የዓዲግራት ከተማን ጥሰው በማለፍ ወደዕዳጋ ሓሙስ መግባታቸውን እንደተመለከቱ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። በዚህ ጉዳይ ላይ ለማነጋገር ለኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃልአቀባይ፣ ለመከላከያ ሚኒስቴር ቃል አቀባይና ለኤርትራው የማስታወቂያ ሚኒስትር በእጅ ስልኮቻቸው ብንደውልም ስልክ ባለማንሳታቸው ሐሳባቸውን ማካተት አልቻልንም።
ስማቸው እንዳይጠቀስ የገለጹት የትግራይ የሰላም አዛዥ እንደሚሉት ዕዳጋ ሓሙስ ከገቡት የኤርትራ ወታደሮች ወደ አፅቢ ወንበርታ አቅጣጫ በ2 የጭነት መኪኖች ተጭነው በሚጓዙበት ወቅት በድሮን ተመተዋል። ከመከላከያ ሠራዊቱ ጎን ተሰልፎ የሚዋጋው ታጣቂ ቡድን አመራር ተፈጽሟል ያሉትን የድሮን ጥቃት ዶይቼ ቬለ በገለልተኝነት አላረጋገጠም።
(DW)
@YeneTube FikerAssefa ሰበር ዜና! የኤርትራ ጦር አዲግራትን አልፎ ወደ መሃል ትግራይ እየተጓዘ መሆኑን ነዋሪዎች ተናገሩ! የኤርትራ ጦር ሠራዊት በትግራይ ክልል ወደ ምትገኘው የአዲግራት ከተማ መግባቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ።ዶቸ ቬለ ያነጋገራቸው ነዋሪዎቹ እንደሚሉት ወታደሮቹ ወደ መቐለ በመጓዝ ላይ ይገኛሉ።በትግራይ ክልል ዋና ከተማ መቐለ የሚገኙ የመረጃ ምንጭ የኤርትራ ወታደሮች “በበርካታ ከባድ ተሽከርካሪዎች ተጭነው…

8 hours ago
የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን የጥራት ጉድለት በታየባቸው ሰባት የመድኃኒት ምርቶች ላይ ማሳሰቢያ አወጣ
የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን የጥራት ጉድለት በታየባቸው እና ከገበያ እንዲሰበሰቡ በተወሰነባቸው ሰባት የመድኃኒት አይነቶች ላይ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስቧል።
ባለስልጣኑ ይህንን ማስጠንቀቂያ ያወጣው የኬንያ የመድኃኒት ተቆጣጣሪ አካል በሀገሪቱ በገበያ ላይ በተገኙ የተወሰኑ ምርቶች ላይ እርምጃ መውሰዱን መነሻ በማድረግ ነው።
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የመድኃኒት ጥራት እና ደህንነት ክትትል ክፍል አማካሪ ዶ/ር ኤልሳቤት ወልደማርያም እንደተናገሩት ኢትዮጵያ እና ኬንያ ሰፊ ድንበር የሚጋሩ በመሆናቸው እነዚህ ምርቶች ወደ ኢትዮጵያ የመግባት ዕድል አላቸው።
በተለያዩ የጥራት እና የደህንነት ጉድለቶች ምክንያት ከገበያ እንዲሰበሰቡ ከተደረጉት ሰባት የመድኃኒት አይነቶች መካከል በህንድ የተለያዩ የመድኃኒት አምራች ኩባንያዎች የተመረቱት
👉ፍላዛርት ሽሮፕ
👉ሄፓካል 25000
👉ቱናክላቭ እና ክላክሲ 1.2 ግራም የተባሉ የመድኃኒት አይነቶች ይገኙበታል።
በተጨማሪም በቻይና ኩባንያ የተመረተው ሜታሚድ መርፌ እና በኬንያ አምራች የተመረተው ክሎክሳም ሽሮፕም ከተሰበሰቡት የመድኃኒት አይነቶች ውስጥ እንደሚገኙበት ተገልጿል።
በዚህም የክልል ተቆጣጣሪ አካላት የእነዚህን ምርቶች ስርጭት እና አጠቃቀም በቅርበት እንዲከታተሉ ያሳሰበው ባለስልጣኑ ህብረተሰቡም ምርቶቹ በእጁ የሚገኙ ከሆነ እንዳይጠቀምባቸው ጥብቅ ማሳሰቢያ ሰጥቷል።
በፋሲል አረጋይ

9 hours ago
ጅማ አዌቱ አጠቃላይ ሆስፒታል ለመላው ኢትዮጵያውያን እንኳን ለመደመር መንግሥት ምስረታ አደረሳችሁ ሲል መልዕክቱን ያስተላልፋል
#ethiopia #houseofpeoplesrepresentatives #houseoffederation #ትልቅ_ሀገር ! #ትልቅ_ሕዝብ ! #ታላቅ_ርዕይ ! #ethiopia #ebc #medemer #የመደመርመንግሥት
9 hours ago
ወ/ሮ ለሊሴ ዱጋ ከስድስት ዓመታት አገልግሎት በኋላ የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን መሪነታቸውን አጠናቀቁ
#ethiopia | ለስድስት ዓመታት የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽንን በኮሚሽነርነት ሲመሩ የቆዩት ወይዘሮ ለሊሴ ዱጋ ከኃላፊነታቸው መሰናበታቸው ተገለጸ።
ወ/ሮ ለሊሴ በቆይታቸው በኢትዮጵያ የቱሪዝም እንቅስቃሴ ውስጥ ከፍተኛ አሻራ ያሳረፉ ሲሆን በተለይም «ቪዚት ኦሮሚያ» የተሰኘውን የቱሪዝም ብራንድ ከምንም በመነሳት በሀገር አቀፍ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ስሙ ከፍ ብሎ እንዲጠራና ለሌሎች ክልሎችም አርአያ እንዲሆን አስችለዋል።
የኦሮሚያን የቱሪዝም ሀብት በዓለም አቀፍ ደረጃ የማስተዋወቅ፣ አዳዲስ መዳረሻዎችን የማልማት፣ የሥራ አጋርነትን የማጠናከር፣ ዲጂታል ቱሪዝምን የማሳደግ፣ «የኦሮሚያ ቱሪዝም ሳምንት»ን ወደ ዓለም አቀፍ መድረክ የማሳደግ እንዲሁም ለኢንቨስትመንትና ለሥራ ዕድል ፈጠራ አዳዲስ መንገዶችን የመክፈት አበይት አሻራዎችን አሳርፈዋል።
በተጨማሪም የሀገሪቱንና የክልሉን የተፈጥሮና የባህል መስህቦች ዓለም በሚረዳው ቋንቋና መንገድ በማስተዋወቅ ረገድ ትልቅ ኢንሼቲቭ በመቅረፅና በመተግበር ረገድ የጎላ ሚና ተጫውተዋል።
ኮሚሽነሯ በሥራ አፈጻጸማቸው፣ በትህትናቸውና ሰዎችን ለመርዳት ባላቸው ዝግጁነት የሚታወቁ ሲሆንበሥራ አጋጣሚያቸው ወቅት ያጋጠማቸውን የካንሰር ሕመም በጽናት ታግለው በማሸነፍ ለሌሎችም የጽናት ማሳያ ሆነዋል።
''የኦሮሚያ ቱሪዝም ሳምንት'' በተከበረበት ወቅት በለተቋሙና ለዘርፉ ላበረከቱት ላቅ ያለ አስተዋጽኦና አገልግሎት ምስጋና የቀረበላቸው ሲሆን በሚቀጥለው አዲስ የሕይወትና የሥራ ምዕራፋቸውም መልካም ሁሉ እንመኛለን።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu

ኬንያ 109 የተደራጁ ወንጀለኛ ቡድኖችን ዝርዝር ይፋ አደረገች።
የኬንያ መንግሥት በሀገሪቱ 109 የተደራጁ የወንጀል ቡድኖችን ለይቶ ማውጣቱን አስታውቋል። ይህ ቁጥር በ2016 በGazette Notice No. 10427 ህገ-ወጥ ከተባሉ 89 ቡድኖች ጭማሪ ነው።
የተደራጁ የወጣት ቡድኖች ለፖለቲካ ማስፈራራት፣ ጥቃት እና ትንኮሳ ውስጥ መሳተፋቸው በስጋትነት ሲጠቀስ፥ ኬኒያ በ2027 ለምታካሂደው አጠቃላይ ምርጫ ከባድ የደህንነት ፈተና ሊሆን እንደሚችልም ተጠቁሟል።
«ጥቃት፣ ማስፈራራት እና የወንጀል ቡድኖችን ለፖለቲካ ጥቅም መጠቀም በዚህ ሂደት ውስጥ ቦታ የላቸውም» ብለዋል።
መንግሥት ባወጣው መረጃ መሰረት ምዕራብ ኬንያ 38 የሚሆኑ የተደራጁ ወንጀለኛ ቡድኖች የሚገኙባት ግዛት ስትሆን ሪፍት ቫሊ 22፤ እንዲሁም ናይሮቢ 20 የተመዘገቡባቸው ግዛቶች ሆነዋል።
በናይሮቢ የህዝብ ትራንስፖርት እና አነስተኛ ንግድ ላይ የሚደረግ ማስገደድ፣ በባህር ዳርቻ በቢላና በስለት የሚፈጸም ጥቃት፣ በሪፍት ቫሊና በድንበር ደግሞ የመሳሪያ ዝውውርና የከብት ዘረፋ የቆዩ መታወቂያዎች ሲሆኑ፣ እነዚህ ቡድኖች በፖለቲካ ውስጥ መሳተፍ መጀመራቸው ስጋት ሆኖ ተቀምጧል።
መንግሥት ምርመራውን ከግለሰብ ወንጀለኞች ባሻገር የቡድን መሪዎችን፣ ቅጥረኞችን እና ፋይናንስ አቅራቢዎችን እየተከታተለ መሆኑን ሲገልጽ፣ የተወሰኑ እንቅስቃሴዎች ድንበር ተሻጋሪ በመሆናቸው ከጎረቤት ሀገራት ጋር የሚደረግ ትብብርም እየተጠናከረ ነው ሲል አስታውቋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ.ም
@TikvahethMagazine

ኢትዮጵያ የራሷን የተፈጥሮ ሃብት አቅም ለማስተዋወቅ 3ኛውን የአፍሪካ የተፈጥሮ ሀብት ፖሊሲ ፎረም መጠቀም እንዳለባት ተገለፀ
መስከረም 27 ቀን 2019 ዓ.ም. (አሐዱ ሬድዮ) ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ልማት ባንክና ከሌሎች አጋሮች ጋር በመተባበር ያዘጋጀችው 3ኛው የአፍሪካ የተፈጥሮ ሀብት ፖሊሲ ፎረም በሀገራት መካከል ያለውን ኢኮኖሚያዊ ትስስር ማጠናከር ላይ ትኩረት በማድረግ ከማክሰኞ እለት ጀምሮ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል።
የምጣኔ ሃብት ባለሙያ አቶ ዘላለም በቀለ ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካም ሆነ በመላው አህጉሪቱ ያለውን የራሷን የኢኮኖሚና የተፈጥሮ ሀብት አቅም በመለየት፣ የንግድ ማስተዋወቅ ስራዎችን በስፋት መስራት እንዳለባት ተነግረዋል ፡፡
ይህ ፎረም አፍሪካውያን ሀገራት በንግድ፣ በፋይናንስና በመሰረተ ልማት ዘርፎች እርስ በርሳቸው በመደጋገፍ ኢኮኖሚያቸውን የሚያሳድጉበት ትልቅ እድል የሚፈጥር እንደሆነም መቁመዋል።
ኢትዮጵያ ፎረሙ እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም፣ ለኢኮኖሚ እድገቷ ወሳኝ የሆኑ እንደ የባህር በር እና የንግድ መስመር ያሉ ሀገራዊ አጀንዳዎቿን ለተሳታፊ ሀገራት ለማሳወቅና ዲፕሎማሲያዊ ድጋፍ ለማሰባሰብ መጠቀም አለባት ያሉት ደግሞ መምህርና ፖለቲከኛ ዶ/ር ጌትዬ ትርፌ ናቸው።
ኢትዮጵያን ጨምሮ የአፍሪካ ሀገራት በተፈጥሮ ሀብት የበለጸጉ ቢሆኑም፣ ሀብታቸውን በአግባቡ ባለመጠቀማቸው ተገቢውን ጥቅም እዳላገኙ ባለሙያዎቹ ገልፀዋል ፡፡ በዚህ ረገድ ሀገራቱ በጋራ መስራት እንደሚገባቸው አፅንኦት ሰጥተዋል።
በደረጄ መንግስቱ

10 hours ago
የኤርትራ ጦር አዲግራትን አልፎ ወደ መሃል ትግራይ እየተጓዘ መሆኑን ነዋሪዎች ተናገሩ
#fastmereja I የኤርትራ ጦር ሠራዊት በትግራይ ክልል ወደ ምትገኘው የአዲግራት ከተማ መግባቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ። ዶቸ ቬለ ያነጋገራቸው ነዋሪዎቹ እንደሚሉት ወታደሮቹ ወደ መቐለ በመጓዝ ላይ ይገኛሉ።
በትግራይ ክልል ዋና ከተማ መቐለ የሚገኙ የመረጃ ምንጭ የኤርትራ ወታደሮች “በበርካታ ከባድ ተሽከርካሪዎች ተጭነው ወደ ደቡብ አቅጣጫ” እየተጓዙ መሆናቸውን በአዲግራት ከሚገኙ ነዋሪዎች መስማታቸውን ገልጸዋል።
የአዲግራት ከተማ በአሁኑ ወቅት በትግራይ ኃይሎች ቁጥጥር ስር መሆኗንም ገልጸዋል። ከኢትዮጵያ እና ኤርትራ ድንበር በ40 ኪሎ ሜትር ገደማ ርቀት ላይ በምትገኘው አዲግራት የኤርትራ ወታደሮች እንደገቡ በተመሳሳይ የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።
ወታደሮቹ ከአዲግራት በደቡባዊ አቅጣጫ ወደ መቐለ በመጓዝ ላይ እንደሚገኙ የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት የመረጃ ምንጮቹን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

Comments