5 hours ago
“ ከአሜሪካ መልስ ሬሴን ላገል ወስኜ ነበር “ ሮናልዶ
“ የፖርቹጋልን ህዝብ ይቅርታ እጠይቃለሁ ”
“ አሰልጣኙ ቃሉን አጥፏል ”
ፖርቹጋላዊው ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በብሔራዊ ቡድኑ ስለተፈጠረው አለመግባባት ማብራሪያ ሰጥቷል።
ከአለም ዋንጫ በኋላ ራሱን ለማግለል የስንብት ደብዳቤ አዘጋጅቶ እንደነበር ሮናልዶ አረጋግጧል።
ይሁን እንጂ የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት ሀሳቡን ቀይሮ እንዲቀጥል መጠየቃቸውን ተከትሎ ሀሳቡን እንደለወጠ ተናግሯል።
በወቅቱ ፕሬዝዳንቱ አዲስ አሰልጣኝ ማንን ለመሾም እንዳሰቡ ሲነግሩኝ “ ጄሱስ ጥሩ ምርጫ መሆኑን ነግሬያቸዋለሁ " ብሏል።
“ አሰልጣኙ ሲሾሙ ደስተኛ ነበርኩ ውጤቱም ምርጫው ትክክል መሆኑን አሳይቷል “ ሲል ገልጿል።
ሮናልዶ ብሔራዊ ቡድኑን ለመልቀቅ የወሰነው አሰልጣኙ ሁለት ጊዜ ቃላቸውን በመስበራቸው መሆኑን አስረድቷል።
“ ለዚህ የፖርቹጋልን ህዝብ ይቅር እጠይቃለሁ “ ያለው ሮናልዶ “ ቃሉን ማጠፉ እኔ ላይ ተፅዕኖ ነበረው "ብሏል።
"ከዚህ በፊት እንደማላስፈልግ ከተሰማኝ ሻንጣዬን ይዤ እሄዳለሁ ብዬ ነበር እሱን አድርጊያለሁ “ ሲል ተናግሯል።
ለዚህም በፌዴሬሽኑ መቀጣት አለብኝ ያለ ሲሆን “ በጥሩ አካላዊ ሁኔታ ላይ ነኝ ከቅጣቱ በኋላ ዝግጁ እሆናለሁ "ብሏል።
@tikvahethsport kidusyoftahe ሮናልዶ ወደ ብሔራዊ ቡድኑ እንደሚመለስ አሳወቀ ! ፖርቹጋላዊው ኮከብ ክርስቲያኖ ሮናልዶ በቀጣይ ጨዋታዎች ወደ ብሔራዊ ቡድኑ እንደሚመለስ ይፋ አድርጓል። ክርስቲያኖ ሮናልዶ በቀጣይ አሰልጣኙ ጥሪ ካቀረቡለት ብሔራዊ ቡድኑን እንደሚቀላቀል አሳውቋል። ሮናልዶ በሰጠው አስተያየት ከብሔራዊ ቡድኑ ራሴን አላገልም ሲል ለፖርቹጋል ህዝብ እና ደጋፊዎች አሳውቃለሁ ብሏል። @tikvahethsport kidusyoftahe

6 hours ago
“ ከአንተ ጎን ሆኖ ታሪክ መፃፍ ክብር ነው ” ኔይማር
ብራዚላዊው ተጨዋች ኔይማር ለቀድሞ የቡድን አጋሩ ሊዮኔል ሜሲ የስንብት መልዕክት አስተላልፏል።
ኔይማር በመልዕክቱ “ እግርኳስ የሚወዱ ሁሉ በእነዚህ አመታት በአንተ ተሰጥኦ ተደስተዋል "ብሏል።
አክሎም “ ዛሬ ለእግርኳስ ላደረግከው ነገር አርጀንቲናውያን ብቻ ሳይሆኑ መላው አለም ያመሰግንሀል “ ሲል ገልጿል።
“ እግርኳስን የበለጠ እንድወድ ስላደረከኝ አመሰግናለሁ ፣ ከአንተ በተቃራኒ መጫወት ክብር ነው አብሮ ታሪክ መፃፍ ደግሞ ከዛም በላይ ነው። ” ኔይማር
@tikvahethsport kidusyoftahe

7 hours ago
ኢትዮጵያውያን ሀገራቸው ሆነው ከቱርክ ስፔሻሊስቶች የሕክምና አስተያየት የሚያገኙበት ቢሮ ተከፈተ!
#fastmereja :-በቱርክ በጤና አገልግሎት ዘርፍ ግንባር ቀደም ከሆኑ ተቋማት አንዱ የሆነው አጂባደም ኸልዝኬር ግሩፕ (Acıbadem Healthcare Group) በአዲስ አበባ አዲስ የታካሚዎች መረጃ መስጫ ቢሮ በዛሬዉ እለት ተመርቆ ስራ ጀምሯል።
ይህ ማዕከል፣ አጂባደም በዓለም ዙሪያ ከከፈታቸው ተመሳሳይ ቢሮዎች 52ኛው መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ማዕከሉ ኢትዮጵያውያን ታካሚዎችና ቤተሰቦቻቸው ወደ ቱርክ ሳይጓዙ በሀገር ውስጥ ሆነው በአፍ መፈቻ ቋንቋቸው ስለ ሕክምና አማራጮች፣ ስለሚገመቱ ወጪዎችና የጊዜ ሰሌዳዎች ሙሉ መረጃ እንዲያገኙ የሚያስችል ስለመሆኑም ተገልጿል።
በተጨማሪም ማዕከሉ የታካሚዎችን ነባር የህክምና ሰነዶች በመገምገም ከቱርክ ስፔሻሊስቶች ሁለተኛ የሕክምና አስተያየት (second opinion) ማቅረብ፣ የሕክምና ቪዛ እና የጉዞ ሁኔታዎችን ማመቻቸት፣ እንዲሁም ሕክምና ተጠናቆ ወደ ሀገር ከተመለሱ በኋላ የሚደረግ ቀጣይነት ያለው የክትትል አገልግሎት እንደሚሰጥ ተገልጿል።
በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የአጂባደም የአለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር ሚስተር ኢሊያስ ቤንቬኒስቴ እንደገለጹት፣ ቢሮው ለአገልግሎት ፈላጊዎች መረጃ ከመስጠት ባለፈ ከኢትዮጵያ የጤና ባለሙያዎች ጋርበመተባበር የልምድና የእውቀት ሽግግር ለማድረግ ያለመ መሆኑን አስረድተዋል።
በዕለቱ በቦታው የተገኙት ታዋቂው የጉበት ንቅለ-ተከላ እና ሄፓቶቢሊየሪ ቀዶ ጥገና ስፔሻሊስት ፕሮፌሰር አሊ አዘርም ቀደም ሲል በቱርክ ሕክምና አድርገው ከነበሩ ኢትዮጵያውያን ታካሚዎች ጋር የተገናኙ ሲሆን፣ ከሀገር ውስጥ ሀኪሞች ጋርም ቀጣይነት ባለው ሙያዊ ትብብር ዙሪያ ተወያይተዋል።
አጂባደም ኸልዝኬር ግሩፕ በቱርክ፣ ቡልጋሪያ፣ ሰርቢያ፣ ኔዘርላንድስ እና መቄዶንያ 30 ሆስፒታሎችንና 15 የተመላላሽ ክሊኒኮችን የሚያስተዳድር ሲሆን፣ በየዓመቱ ከ50 ሺህ በላይ ዓለም አቀፍ ታካሚዎችን ያስተናግዳል።

8 hours ago
በፌርፎርድ ጦር ሰፈር ላይ ጥቃት ለማድረስ አቅዶ የነበረ የ22 ዓመት እንግሊዛዊ በዩኬ ፖሊስ በቁጥጥር ስር ዋለ
የእንግሊዝ ፖሊስ ማክሰኞ ዕለት እንደገለጸው፤ አሜሪካ በኢራን ላይ ጥቃት ለመሰንዘር በሚያገለግለው የራፍ ፌርፎርድ የአየር ኃይል ጦር ሰፈር አካባቢ የታሰበውን የሽብር ጥቃት ዝግጅት ተሳትፎበታል በሚል ጥርጣሬ አንድ የ22 ዓመት እንግሊዛዊ በለንደን በቁጥጥር ስር ውሏል።
የብሪታንያ ፖሊስ እንዳስታወቀው፣ ግለሰቡ በለንደን የተያዘው አሜሪካ፣ በኢራን ላይ ጥቃት ለማድረስ የምትጠቀምበትን የራፍ ፌርፎርድ አየር ኃይል ጦር ሰፈርን ለማጥቃት የታቀደውን ሴራ በተመለከተ እየተካሄደ ባለው ምርመራ አካል እንደሆነ ተናግሯል።
የፀረ-ሽብርተኝነት ፖሊስ ክፍሉ ግለሰቡ በዌስትሚኒስተር አካባቢ መያዙንና ፖሊሶች በዚያው አካባቢ የሚገኝን አንድ መኖሪያ ቤት መበርበራቸውን ገልጿል። ተጠርጣሪው በአሁኑ ወቅት በቁጥጥር ስር ይገኛል።
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር የተያያዘ ስጋት በመኖሩ ምክንያት አሜሪካ B-1 ቦምብ ጣይ ጄቶቿን ከጦር ሰፈሩ እንድታወጣ አድርጓል ካሉ በኋላ ይህ እስራት የአለም አቀፍ ትኩረትን የሳበው ምርመራ የቅርብ ጊዜ እርምጃ ነው።
ኢራን በተሰነዘረባት ክስ ላይ ምንም አይነት እጅ እንደሌላት አስተባብላለች።
ሰላማዊ ነጋሲ
#ዳጉ_ጆርናል

Sponsored by
Surafel
8 hours ago
መድኃኔአለም በሐጢዓት ፈተና ተጠልፎ ከመውደቅ ይጠብቀን🙏
እግዚአብሔር እስራኤልን ከደመና መና አውርዶ፣ ከአለት ውሀ አፍልቆ መገባቸው፡፡
እነርሱ ግን እዚህ ደጋ ላይ ቢሆንለት የውርጭ ሰደቃ እያበጀ፣ ውሀውን እያረጋ፣ መና መገብኳችሁ ይላል እንጅ ቆላ ቢሆነማ ባልተቻለውም ነበር ብለዋል። የርሱን ከሃሊነት፣ የእነርሱንም ሀሰት ሊገልጥ ቢወድ፣ ሙሴን የውሃ ምንጭ የሌለበት በረሐ ይዘሀቸው ሂድ ብሎት በዚያም መናው ወርዶላቸዋል፣ ውሀውም ፈልቆላቸዋል። ነገር ግን ነዘር የሚባል እባብ እየነከሰ ይፈጃቸው ጀመር። በዚህ ጊዜ ከሙሴ ዘንድ ሂደው ከጌታ ምህረት ቸርነት ከእኛ ኃጢአት አይታጣም በእግዚአብሔርና በአንተ ላይ ተናግረን በድለናል እባቦችን እንዲያርቅልን ወደ እግዚአብሔር አመልክትልን አሉት።
ሙሴም ወደ እግዚአብሔር ቢጸልይ ከንጹህ ነሐስ የእባብ ምስል ሠርተህ ከሚገናኙበት አደባባይ ከእንጨት ላይ ስቀልላቸው አለው። እንደተባለው ቢያደርግ እባብም የነደፈችው ሰው ሁሉ የነሐሱን እባብ ባየ ጊዜ ዳነ። “ሙሴ እባብን በምድረ በዳ እንደሰቀለው የሰው ልጅ ክርስቶስ ይሰቀል ዘንድ አለው” ተብሎ በዮሐንስ 3÷14 እንደተነገረ፡፡ አባቶቻችንም በትርጓሜ ወንጌል የበረሐው እባብ የዲያብሎስ፤ የብረቱ እባብ የጌታ ምሳሌ ነው። በእባብ መርዝ እንዳለበት በዲያብሎስም ፍዳ ኃጢአት አለበት።
በነሐሱ እባብ መርዝ እንደሌለበት በጌታም ፍዳ ኃጢአት የለበትም። የነሐሱ እባብ በእባብ አምሳል መሰቀሉ ጌታ እንደ ወንጀለኛ ተቆጥሮ ለመሰቀሉ ምሳሌ ነው። ክርስቶስ ኢየሱስ በመስቀል በተሰቀለ ጊዜ፤ የተሰቀለው የክብር ባለቤት ሰማይን የፈጠረ ነውና ፀሐይ ጨልማለች፣ ጨረቃ ደም ሆኗል፣ ከዋክብት ረግፈዋል።
ገዳማውያኑም በመስቀል የተደረገልንን ማዳን እያሰቡ ዓለምን ንቀው፣ ስጋቸውን ጎድተው ይከተሉታል፡፡ የጽድቃቸው አክሊል እርሱ መድኃኔ ዓለም የሚወደኝ መስቀሌን ተሸክሞ ይከተለኝ እንዳለ፡፡
ድጋፍ ለማድረግ፡- ቤተ ቅዱሳን ፈትለወርቅ ማርያም የእናቶች ገዳም፡-
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000766349227
ወይም
አቢሲንያ ባንክ
262281132
የገዳሙ ስልክ ቁጥር፡- 0944672222 ወይም 0916106921

10 hours ago
መንግስት ሙስና እና የዘመድ አሰራርን ለማስቀረት ጠንካራ እርምጃ ሊወስድ መሆኑን አስታወቀ
ሙስናን እና የወገንተኝነት አሰራርን ለማስቀረት መንግስት ጠንካራ እርምጃዎችን እንደሚወስድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ አስታወቁ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን የገለጹት የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የስራ ዘመን የምክር ቤቱ መመስረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባውን ባካሄደበት እለት ነው፡፡
በዚህም በሃገር ሰላም፣ አገልግሎት አሰጣጡ የተሻለ ለማድረግ፣ ምርታማነት እንዲጨምር እና ጠንካራና ቁጥጥር ያለበት የበጀት አካሄድን አጠናክረው እንደሚሰሩም አንስተዋል፡፡
በተለይ ለህብረ ብሔራዊ ሃገረ መንግስት ግንባታ ወሳኝ የሆነው የወል ትርክት ተገቢውን ትኩረት እንደሚያገኝ ጠቁመዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም የሰላም ሁኔታዎችን የበለጠ ለማስጽናት የውይይትና የይቅርታ መንገድ እንደሚከተሉም አመላክተዋል፡፡ እንዲሁም ጸጥታና ደህነነት ዝግጅትና ክትትል ብሎም ስምሪት እንደሚኖር ተናግረዋል፡፡
የሚዲያ ምህዳሩ ህግን ሃገራዊ እሴቶችን እና ፍላጎቶችን ባከበረ መልኩ እንዲንቀሳቀስ እንደሚደረግ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል፡፡
በዚህም መሰረት እንደ መሶብ አንድ ማዕከል ያሉ አገልግሎቶችን እስከታችኛው እርከን ለማድረስ እና የተጀመረውን የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም በማጠናከር የአገልግሎት አሰጣጥ እንዲዘምን ይደርጋልም ብለዋል፡፡
በአለምነው ሹሙ
#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ

15 hours ago
መንግስት በ2019 በጀት ዓመት ትኩረት የሚያደርግባቸውን 8 አበይት ጉዳዮች ይፋ አደረገ
ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀስላሴ መንግስት በ2019 በጀት ዓመት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ የሚንቀሳቀስባቸውን ስምንት ዋና ዋና ጉዳዮች ይፋ አደረጉ።
የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች 7ኛ የስራ ዘመን 1ኛ ዓመት የጋራ መደበኛ ስብሰባ ላይ ንግግር ያደረጉት ፕሬዝዳንቱ መንግስት በበጀት ዓመቱ በዋናነት ሰላም ለሀገር እድገትና ግስጋሴ ያለውን ከፍተኛ ዋጋ በማጤን ህብረትን ፣ ትብብርን እና ኢትዮጵያን የሚያስቀድም ተግባር ያከናውናል ብለዋል።
በተጨማሪም ጥራትን መሰረት ያደረገ ሁለንተናዊ መዋቅራዊ ሽግግር ለማምጣት ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ አስታውቀዋል።
በማህበራዊ ዘርፍ የትምህርት ፣ የጤና እና የማህበራዊ ጥበቃ ስራዎችን ከስፋት ወደ ጥራት በማሸጋገር ዜጋን ማዕከል ያደረገ ልማት ትኩረት እንደሚሰጥበት የገለጹት ፕሬዝዳንቱ ለእድገት ቁልፍ ፋይዳ ባላቸው የኢንዱስትሪና የግብርና ግብዓቶች እንዲሁም በዘመናዊ የመሰረተ ልማት ግንባታ ሀገራዊ አቅም ራሱን እንዲችል ለማድረግ እንደሚሰራ ተናግረዋል።
በኢኮኖሚና ፋይናንስ ዘርፍ ደግሞ የፕሮጀክትና የፕሮጀክት ፋይናንስ አፈፃፀም ዘመናዊ ፣ ቀልጣፋ እና ተጠያቂነት ያለው እንዲሆን ይደረጋል ብለዋል።
የታክስ መሰረትን በማዘመን ዕዳን ወግ ባለው መልኩ ማስተዳደር እና የመንግስት ገቢና ወጪን በአግባቡ የመቆጣጠር አቅም እንዲያድግ ልዩ ትኩረት ይሰጣል ብለዋል።
በአስተዳደር እና የውጭ ግንኙነት መስክም በፌዴራል መንግስት እና በክልሎች መካከል ያለው የስራ ቅንጅት እና የአፈጻጸም ክትትል እንከን አልባ እንዲሆን እንደሚሰራ ፕሬዝዳንቱ ገልጸዋል።
አክለውም የኢትዮጵያን የውጭ ግንኙነት ከተቀባይነት ወደ ተፅዕኖ ፈጣሪነት በማሸጋገር በተለይም ወዳጆችን በማብዛት እና ለቀጠናዊ ሰላምና ኢኮኖሚያዊ ትስስር ቅድሚያ የሚሰጡ ተነሳሽነቶችን በማጎልበት አለም አቀፍ ተቀባይነትን ለማሳደግ እንደሚሰራ ገልጸዋል።
በፋሲል አረጋይ
#አሐዱ_ሬዲዮ_94 .3
#አሐዱ_የኢትዮጵያውያን_ድምጽ Photo

17 hours ago
«ጌታቸው ረዳ ወደ መቐለ ተመለሱ‼️
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የቀድሞ ፕሬዝዳንት እንዲሁም የጠቅላይ ሚኒስትሩ የአፍሪካ ቀንድ ጉዳዮች አማካሪ የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ፣ መቐለ ከተማ ከህወሓት ታጣቂዎች ነፃ መውጣቷን ተከትሎ ወደ ከተማዋ መመለሳቸውን ሮይተርስ ዘገበ።
🔹 ዋና ዋና ነጥቦች፦
ወደ መቐለ መመለስ፦ የቀድሞው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ ወደ ክልሉ መዲና መቐለ መድረሳቸውን የአለም አቀፉ የዜና ተቋም ሮይተርስ አረጋግጧል።
አካባቢያዊ ሁኔታ፦ አቶ ጌታቸው ረዳ ወደ ከተማዋ የተመለሱት መቐለ ከህወሓት ታጣቂዎች ቁጥጥር ነፃ መውጣቷን ተከትሎ መሆኑ ተመላክቷል።
ወቅታዊ ሁኔታ፦ የአካባቢውን ሰላምና ወታደራዊ ሁኔታ በተመለከተ አዳዲስ መረጃዎች እየወጡ እንደሚገኙ ተገልጿል።
@Yenetube Fikerassefa

19 hours ago
«ጌታቸው ረዳ ወደ መቐለ ተመለሱ» — ሮይተርስ
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የቀድሞ ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ፣ መቐለ ከተማ ከህወሓት አማፂያን ነፃ መውጣቷን ተከትሎ ወደ ከተማዋ መመለሳቸውን ሮይተርስ ዘገበ።
🔹 ዋና ዋና ነጥቦች፦
ወደ መቐለ መመለስ፦ የቀድሞው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ ወደ ክልሉ መዲና መቐለ መድረሳቸውን የአለም አቀፉ የዜና ተቋም ሮይተርስ አረጋግጧል።
አካባቢያዊ ሁኔታ፦ አቶ ጌታቸው ረዳ ወደ ከተማዋ የተመለሱት መቐለ ከህወሓት አማፂያን ቁጥጥር ነፃ መውጣቷን ተከትሎ መሆኑ ተመላክቷል።
ወቅታዊ ሁኔታ፦ የአካባቢውን ሰላምና ወታደራዊ ሁኔታ በተመለከተ አዳዲስ መረጃዎች እየወጡ እንደሚገኙ ተገልጿል።
Seledadotio

1 day ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) ‹‹ክርስቲያኖ ሮናልዶን ይቅርታ አልጠይቀውም›› ሲሉ የፖርቹጋሉ አሰልጣኝ ተናገሩ፡፡ የፖርቹጋሉ አሰልጣኝ ጆርጅ ጀሱስ ከክርስቲያኖ ሮናልዶ ጋር የተፈጠረውን ውዝግብ ተከትሎ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ ‹‹ማንምም ይቅርታ አልጠይቅም›› ብለዋል፡፡ የአምስት ጊዜ የባሎን ዶር አሸናፊ ሮናልዶ አሁን እየተካሄደ ባለው አለም አቀፍ ውድድር በአሰልጣኙ ተመርጦ የነበረ ቢሆንም ውድድሩን ሳያጠናቅቅ የፖርቹጋልን ካምፕ ለቆ በግል አውሮፕላኑ መጓዙ ይታወቃል፡፡ ከዚያም በማህበራዊ ሚዲያው ላይ ለምን ለቆ እንደሄደ ከፖርቹጋል እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር ከተነጋገረ በኋላ ‹‹ሚስጥሩን›› ይፋ እንደሚያደርግ ገልፆ ነበር፡፡
ነገር ግን የ41 አመቱ ተጨዋች ፖርቹጋል ከኖርዌይ ጋር ባደረገችው ግጥሚያ ወቅት ከ18 አመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የተቀያሪዎች ወንበር ላይ ማሳለፉ ይታወቃል፡፡ የብሄራዊ ቡድኑን ካምፕ ለቆ የወጣውም ከዚህ ጨዋታ በኋላ ነበር፡፡ አሰልጣኙ ጀሱስ ትላንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት ከሮናልዶ ጋር ስለተፈጠረው ጉዳይ፣ እንዲሁም ሮናልዶን ይቅርታ ይጠይቁት እንደሆነና በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ ማብራሪያዎችን እንዲሰጡ ተጠይቀው ነበር፡፡ እሳቸውም ግራ በመጋባት ‹‹ይቅርታ የምጠይቀው በምን ጉዳይ ነው?›› የሚል ጥያቄ ካነሱ በኋላ ‹‹ማንምም ይቅርታ አልጠይቅም›› የሚል መልስ ሰጥተዋል፡፡ ስለተፈጠረው ጉዳይ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ቢቆጠቡም ብሄራዊ ቡድኑ ለሮናልዶ በሩን ዝግ እንደማያደርግ ገልፀዋል፡፡
ሲናገሩም ‹‹በሚቀጥለው የአለም አቀፍ ጨዋታዎች እረፍት ለሮናልዶ ጥሪ ይቀርብለታል፡፡ ከፈለገ ያንን ጥሪ ተቀብሎ ይመጣል፡፡ ውሳኔው ግን የእሱ ነው›› ብለዋል፡፡ ጨምረውም ‹‹ይህንን ሁሉ የፈጠረው የማሟሟቅና አለማሟሟቅ እንዲሁም ወደሜዳ መግባትና አለመግባት ነገር ነው፡፡ በእርግጥ እሱ በመሆኑ ብቻ ልክ ሊሆን ይችላል፡፡ ምክንያቱም ትልቅ ስም ያለውና ተምሳሌት ነው፡፡ ነገር ግን ዛሬ ስንት ተጨዋቾች አሟሙቀው ወደሜዳ አልገቡም? ከእነሱ መካከልስ ችግር የፈጠረ አለ? የለም›› በማለት አስረድተዋል፡፡

እናት ባንክ የመጀመሪያውን የሥርዓተ ፆታ ቦንድ ለገበያ ለማቅረብ የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ መሆኑን ገለጸ
እናት ባንክ በሴቶች ለተያዙና ለሚመሩ ኢንተርፕራይዞች የረጅም ጊዜ ፋይናንስ ለማቅረብ ያዘጋጀውን የሥርዓተ ፆታ ቦንድ/ Gender Bond ሽያጭ በቅርቡ ይፋ እንደሚያደርግ የባንኩ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሮ አስቴር ሰሎሞን ገለጹ።
ሰብሳቢዋ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ማብራሪያ እንደተናገሩት፣ የቦንድ ሽያጩን ለመጀመር የሚያስፈልጉ ጥናቶች ተጠናቀው የመጨረሻ ደረጃ ላይ ይገኛሉ ብለዋል።
የቦንዱ የመግዣ ዋጋ እና ወደ ሽያጭ የሚገባበት ትክክለኛ ቀን ቦንዱን ከሚያስተዳድረውና ከሚቆጣጠረው አካል ፈቃድ ሲገኝ የሚወሰን እንደሆነም ነው የጠቆሙት።
ከዚህ የቦንድ ሽያጭ የሚሰበሰበው የፋይናንስ ምንጭ መደበኛ የብድር ዋስትና ማስያዣ ማቅረብ ለማይችሉ ሴቶች ብድር ለማቅረብ ከመዋሉም ባሻገር፣ ለፋይናንሺያል ስልጠናዎችና የሴቶችን የሥራ ፈጠራ አቅም ለማጎልበት በሚደረጉ ድጋፎች ላይ ውላል።
"እስካሁን ሴቶችን ለማገዝ በሰራናቸው ስራዎች በሴቶች ላይ ለውጦችን አይተናል። በዚህ የቦንድ ሽያጭ ላይ ይሳተፋሉ ብለን ያሰብናቸው የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገር አለም አቀፍ ተቋማቶች አሉ። ተቋማቶች የቦንድ ሽያጩ እስኪጀመር እየጠበቁ ነው፣ ከዛም በኃላ ለየትኛውም ህዝብ ክፍት ይሆናል" ነው ያሉት።
ጥናቶች እንደሚያመለክቱት በሱብ-ሳሃራ አፍሪካ የሚገኙ ሴት ሥራ ፈጣሪዎች የ42 ቢሊዮን ዶላር የፋይናንስ አቅርቦት እጥረት ቢኖርባቸውም፣ ሴት ተበዳሪዎች ብድር የመመለስ ታማኝነታቸው ከፍተኛ መሆኑና የማይመለስ ብድር (NPL) መጠናቸው ከወንዶች በ53 በመቶ ዝቅተኛ እንደሆነ ያሳያል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ/ም
@TikvahethMagazine

‹‹ብሄራዊ ጥቅሞችን መሠረት ባደረገ መልኩ ከሁሉም ሀገራት ጋር እንሰራለን›› ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናገሩ
ዛሬ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተካሄደው የመንግስት ምስረታ መርሃ ግብር ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወቅታዊ የቀጣናዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ጉዳዮችን ባደረጉት ንግግር ላይ አንስተዋል።
የዉጭ ግንኙነታችን የኢትዮጵያን ተፅዕኖ ለአለም በሚያሳይ መልኩ እንዲቃኝ ይደረጋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ፤ከሁሉም የአለም አካላት ጋር ብሄራዊ ጥቅምን መሠረት ባደረገ መልኩ አብሮ ለመስራት ዝግጁ ነን ሲሉ ገልፀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸዉ፤ ጎረቤቶቻችን በተፈጥሮ ያገኘናቸው ወዳጆታችን ናቸዉ ያሉ ሲሆን፤በትብብር የመስራት መርሃችንን እንገፋበታለን ብለዋል።
የኢትዮጵያ ስልጣኔ ያለ ባህር በር እዉን መሆን አይችልም፤ በሰጥቶ መቀበል መርህ ኢትዮጵያ ወጥቶ መግቢያ በር እንዲኖራት ይሰራል ብለዋል በንግግራቸው።
በቀጣናው ላይ የአየር የበላይነትን ለመፍጠር የሚያስችል አቅም ትገነባለች ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስተሩ አክለዋል።

"የሕገ መንግሥት ማሻሻያ ይደረጋል!"
#ethiopia | በሀገራዊ ምክክሩ ምክረ-ሐሳብ መሠረት በቀጣይ የሕገ መንግሥት ማሻሻያ ይኖራል።
በ7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ ቃለ መሐላ ፈጽመው የተሾሙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ባደረጉት ንግግር “ኢትዮጵያ አሸናፊ እንጂ ተሸናፊ ልጆች የሌሏት ሀገር ናት” ሲሉ ገልጸዋል።
ሀገርን መገንባት የሚቻለው በውይይት በመሆኑ፣ በየጫካው የታጠቁና ያኮረፉ ኃይሎች የሰላም አማራጭን ተቀብለው ከሕዝብና ከመንግሥት ጋር እንዲሰሩ ጥሪ ቀርቧል።
54 ሚሊዮን ዜጎች የተሳተፉበት 7ኛው ብሔራዊ ምርጫ በብዙ ፈተናዎች ውስጥ አልፎ የኢትዮጵያን ዲሞክራሲ ያጠናከረና ለጠንካራ የመንግሥት ሥርዓት መሠረት የጣለ ነው።
ኢትዮጵያ ባለፉት የኢንዱስትሪ አብዮቶች ተጠቃሚ ሳትሆን ማለፏን በማስታወስ፣ ከአለም አቀፍ ተለዋዋጭ ሁኔታዎች ጋር ለመራመድ አሁናዊ ዝግጅት ማድረግ አስፈላጊ መሆኑ ገልጸዋል።
በሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ከሚቀርቡ የምክረ-ሐሳብ ውጤቶች በመነሳት አስፈላጊ የሕገ መንግሥት ማሻሻያዎችን እንደሚኖሩ አመላክተዋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #getutemesgen

ሳውዲ የዘመናዊውን ስታዲየም ግንባታ ልታቆም ነው !
ሳውዲ አረቢያ ለ 2034 አለም ዋንጫ የምትገነባውን ዘመናዊ ስታዲየም ግንባታ ልታቆም መቅረቧን ሮይተርስ ዘግቧል።
የግንባታ ወጪው 2.5 ቢልዮን ዩሮ ተገምቶ የነበረው ስታዲየሙ የአለም ዋንጫ ጨዋታዎችን ያስተናግዳል ተብሎ ታቅዶ ነበር።
ስታዲየሙ ከመሬት 350 ሜትር ከፍታ ያለው እና 46,000 ተመልካች የመያዝ አቅም ይኖረዋል ተብሎ ነበር።
ይሁን እንጂ በፋይናንስ መዘግየቶች እና መቋረጦች ምክንያት ግንባታው ሊቋረጥ መሆኑ ተገልጿል።

2 days ago
ስለ ቴኒስ #post_2
60 እና 70ዎቹ ላይ የቴኒስ ንግስት ነበረች ማርጋሬት ኮርት፣ ነገር ግን 70ዎቹ መጨረሻ ላይ ከቴኒስ አለም ራሷን አግልላለች በቴኒስ አለምም በሴቶች እንደሷ የስኬትን ፅዋ ደጋግሞ የተጎነጨ የለም ነገር ግን ከስፖርቱ ውጪ ባለው አናኗሯ ምክንያት ስሟ ጠልሽቷል።
ይህን ያህል ካስታወስናት ብዙዎቻችን በቅርብ ከምናያት ሴሪና ዊሊያምስ ጋር እናወዳድራት።
ከሁለቱ ለእናንተ ምርጡ ማነው ?
NB 📊 በስኬት ሚዛን ማርጋሬት ኮርት 24 የግራንድስላም ሽልማቶችን በማሸነፍ ከሴሪና 23 በአንድ ትቀድማለች።
@Bisrat_Sport_433et

“እኛ ህንዶች የሰውን ህይወት የምንቀማ ሳንሆን ህይወት የምናድን ህዝቦች ነን” — ናሬንድራ ሞዲ
#ethiopia | የህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ “እኛ ህንዶች የሰውን ህይወት የምንቀማ ሳንሆን ህይወት የምናድን ህዝቦች ነን” ሲሉ ተናገሩ።
ይህ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ህንድ በአለም አቀፍ መድረክ የምታንጸባርቀውን ሰላማዊ እና ህይወትን የማዳን መርህ የሚያጎላ ነው።
ህንድ ለታዳጊ እና ለበለጸጉ ሀገራት ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸውን አስፈላጊ መድኃኒቶች እና ክትባቶችን በማቅረብ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ህይወት በማዳን ላይ ትገኛለች ብለዋል።
በተለያዩ ሀገራት የተፈጥሮ አደጋዎች፣ ግጭቶች ወይም ወረርሽኞች በሚከሰቱበት ወቅት ህንድ ቀድማ በመድረስ ፈጣን የሰብአዊ እና የህክምና እርዳታ በማቅረብ ትታወቃለች ነው ያሉት።
የህንድ ታሪክ እና ባህል በግጭት እና በጦርነት ሳይሆን በሰላም በወንድማማችነት እሴቶች ላይ የተገነባ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አጽንኦት ሰጥተውበታል።
በአጠቃላይ ሞዲ በንግግራቸው ህንድ ከአለም ሀገራት ጋር ያላትን ግንኙነት በኃይል እና በግጭት ሳይሆን በህይወት አድኚነት፣ በህክምና ድጋፍ እና በወንድማማችነት መንፈስ ላይ ተመስርታ እንደምትቀጥል ገልጸዋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #getutemesgen #pmmodi #narendramodi #india #indiaforeignpolicy #globalsouth #humanitarianaid

የታሪካዊ ጠላቶችን ሴራ ያከሸፈው የኢትዮጵያ ፅናት
**************
የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ፕሮጀክቱ በአለም አቀፍና በቀጣናዊ መድረኮች በርካታ ዲፕሎማሲያዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ጂኦፖለቲካዊ ጫናዎች ሲያጋጥሙት ቆይተዋል።
የኢትዮጵያን ሉዓላዊነትና የልማት መብት ለመገደብ የተደረጉ ሴራዎችም ብዙ ርቀት የተጓዙ ቢሆንም ኢትዮጵያ እነዚህን የውስጥና የውጭ ፈተናዎች በፅናት በመቋቋም የግድቡን ግንባታ በተሳካ ሁኔታ አጠናቃ ለውጤት አብቅታለች።
ዛሬ ላይ የህዳሴ ግድብ መጠናቀቅ የሀገራችን የኢኮኖሚ፣ የዲፕሎማሲና የፖለቲካ ከፍታ ማሳያ ከመሆኑም በላይ ከረጅም ዘመናት የባህር በር ማጣት ጋር ተያይዞ ለተነሳው የፍትሃዊ ተጠቃሚነት ጥያቄ ትልቅ አቅም የሚፈጥር ቁልፍ የታሪክ ምእራፍ ሆኗል።
ግብፅ የቅኝ ግዛት ዘመን ስምምነቶችን መሰረት በማድረግ የኢትዮጵያን ፍትሃዊ የውሃ አጠቃቀም ለመቀልበስ ከፍተኛ ጥረት ስታደርግ ቆይታለች። ጉዳዩን የአረብ ብሄራዊ ደህንነት ስጋት በማስመሰል የአረብ ሊግ አባላት በኢትዮጵያ ላይ ወጥ አቋም እንዲይዙና ዲፕሎማሲያዊ ማእቀብ እንዲጥሉ ከመጎተቷም ባሻገር የግድቡ መሰራት በታችኞቹ የተፋሰስ ሀገራት ላይ ከባድ የውሃ እጥረት እንደሚፈጥር በማስመሰል መጠነ ሰፊ የስም ማጥፋት ዘመቻዎችን አካሂዳለች።
ከአስመራ እስከ ካይሮ ባሉት ሀይሎች የሚመራውና የሚደገፈው ይህ የጥፋት መረብ በኢትዮጵያ ሰላም እንዳይሰፍንና በምጣኔ ሀብት እንዳትለማ ለማደናቀፍ እንዲሁም አልፎ አልፎ የሚነሱ የፖለቲካ አለመግባባቶችን በመጠቀም የሀገራችንን የድርድር አቅም ለማዳከም ጥረት አድርጓል።
ሆኖም ኢትዮጵያ በህዝቧ ሁለንተናዊ ድጋፍና በፅናት ፍትሃዊ እና ተመጣጣኝ የውሃ አጠቃቀም የሚለውን መርህ አፀንታ በመያዝ የናይል ተፋሰስ ሀገራትን የትብብር ማእቀፍ ስምምነት አፅድቃለች።
ይህ በዓባይ ላይ የተመዘገበው ታሪካዊ ድልና እያደገ የመጣው የኢኮኖሚ አቅም ኢትዮጵያ በቀይ ባህር የሚገባትን ስፍራ ለማግኘት የምታደርገውን የመደራደር አቅምን በማሳደግ በከፍተኛ ሁኔታ ይደግፋል።
ኢትዮጵያ ከጥንቱ የአክሱም ስልጣኔ እስከ አዱሊስ ወደብ ድረስ የባህር በር ባለቤት የነበረች ሲሆን ዛሬም ከ130 ሚሊዮን በላይ ህዝብና ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ያላት ሀገር በመሆኗ የባህር በር ማግኘት የህልውናና የልማት ጥያቄ እንጂ ሌላን ሀገር ለመውረር የሚደረግ ጉዞ አይደለም።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተለያዩ አጋጣሚዎች እንደገለፁት ኢትዮጵያ በታሪክም ሆነ በዓለም ህግ መሰረት በሰላማዊ መንገድ የባህር በር የማግኘት መብት ስላላት የጂኦግራፊ እስረኛ ሆና አትኖርም።
ኢትዮጵያ የሕዳሴውን ግድብ በራሷ አንጡራ ሀብትና አቅም ገነብታ የቀጠናው የልማትና የእድገት ማእከል እንዳደረገችው ሁሉ የቀይ ባህር መዳረሻ ፍላጎቷንም ቢሆን ሌሎችን ባገለለ መልኩ ሳይሆን በሰላም፣ በህግ፣ በዲፕሎማሲና በህዝቦቿ የተባበረ ብርታት በጋራ ተጠቃሚነት መርህ ላይ ተመስርታ እውን ታደርጋለች።
በብሌን ደምበሎ
#ትልቅ_ሀገር #ትልቅ_ሕዝብ #ታላቅ_ርዕይ
#ethiopiandiplomacy #sovereignty #ethiopianpanafricanism #geopolitics #hornofafrica

ፖርቹጋል ሮናልዶን ማጣቷ እንዳሰጋት ገለፀች !
የፖርቹጋል ኢኮኖሚ ሚኒስቴር ማኑኤል ካስትሮ አልሜዳ የክርስቲያኖ ሮናልዶ ሁኔታ ሀገሪቱን እንዳሰጋ ገለፁ።
ሚኒስቴሩ ክርስቲያኖ ሮናልዶ " ለፖርቹጋል ብራንድ ሀብት ነው " የሚል እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል።
“ ሮናልዶ ፖርቹጋል ውስጥ ከፍተኛ እውቅና ያለው ሰው ነው " ያሉት ባለስልጣኑ “ ከእሱ በፊት ፖርቹጋልን የሚያውቅ አልነበረም ለእሱ ምስጋና ይግባው “ ብለዋል።
የፖርቹጋል መንግሥት ክርስቲያኖ ሮናልዶን ማጣት ስለሚያመጣው ተፅዕኖ ስጋት እንዳደረበት ጨምረው ተናግረዋል።
ክርስቲያኖ ሮናልዶን ማጣት የሀገሪቱን ገፅታ እና ያላትን አለም አቀፍ ተፅዕኖ ሊጎዳ እንደሚችል ስጋት መኖሩ ተነግሯል።
@tikvahethsport YisakAH

“ የሜሲን ማልያ ለመጠየቅ ተዘጋጅቻለሁ ” የቤኒን ተጨዋች
የቤኒን ተጨዋች ሞሀመድ ቲጃኒ በሊዮኔል ሚሲ የሰንበት ጨዋታ ተሳታፊ መሆናቸው እንዳስደሰታቸው ተናግሯል።
“ በጨዋታው ተደስተናል " ያለው ተጨዋቹ " የሜሲ የመጨረሻ ጨዋታ ተሳታፊ መሆን አስደሳች ነው ” ሲል ገልጿል።
አርጀንቲና ሄደው ያውቁ እንደሆነ የተጠየቀው ተጨዋቹ “ አናውቅም ሜሲን ነው የምናውቀው የአለም ምርጡ ተጨዋች ነው " ብሏል።
“ ለዚህ ጨዋታ ዝግጅት አያስፈልግም በቅፅበቱ መደሰት ነው ያለብን “ ሲል ዝግጅት አላደረግንም ሲል ገልጿል።
አክሎም “ ሜሲን እኔ በጣም እወድሃለሁ ማልያህን ስጠኝ እባክህ ብዬ እጠይቀዋለሁ፣ ማልያውን ቀድሜ አገኛለሁ " ሲል ተደምጧል።

7 ቀናት ብቻ ቀሩ
#ethiopia | የ2026 የአፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ (2026 African Impact Award) የክብር ምሽትን አብረው ለማሳለፍ ይፈልጋሉ?
በዝግጅቱ ላይ የእራት ግብዣ፣ የሙዚቃ ዝግጅት፣ የክብር ዘበኞች ትርኢት እና የዋናው ዝግጅት ተሻጋሪ ለውጥ ያመጡና ተፅዕኖ የፈጠሩ ተሸላሚዎች ዕውቅና አሰጣጥ ይከናወናል።
የተዘጋጁት የትኬት ቁጥሮች ውስን ሲሆኑ፤ ከሽያጩ የሚገኘው ገቢ በሙሉ ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች ድጋፍ ይውላል።
የ2026 የሽልማቱ ተቀባዮች፦
ፕሮፌሰር ዶናልድ ጆሃንሰን (Prof. Donald Johanson) — ታዋቂው የፓሊዮአንትሮፖሎጂስት እና የ"ሉሲ" (ድንቅነሽ) ግኝት ባለቤት
ፖል ቴርጋት (Paul Tergat) — የረጅም ርቀት ሩጫ አትሌት እና የቀድሞ የዓለም ማራቶን ሪኮርድ ባለቤት
እዮብ "ጆ" ማሞ (Eyob "Joe" Mamo) — ስኬታማ የንግድ ባለቤት እና ሥራ ፈጣሪ
አለምፀሐይ ወዳጆ (Alemtsehay Wedajo) — በኪነ-ጥበብ፣ ባህል እና በበጎ አድራጎት ዘርፍ የጎላ አስተዋጽኦ ያበረከቱ
ማክዳ አሰፋ (Makda Assefa) — የፈር ቀዳጅ ሚዲያ መሪ
ቀን፦ እሁድ፣ ጥቅምት 1 ቀን 2019 ዓ.ም (October 11, 2026)
ሰዓት፦ ከምሽቱ 11:30 (5:30 PM)
ቦታ፦ ሜትሮ ፖይንትስ ሆቴል (Metro Points Hotel)፣ ሜሪላንድ - 8500 Annapolis Road, New Carrollton, MD 20784.
ለበለጠ መረጃ እና ትኬት ለመግዛት፦ https://www.eventbrite.com...
3 days ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) ግብፅ የአፍሪካ ህብረትን መግለጫ ‹‹እኛን ወደኢትዮጵያ ቀውስ ውስጥ ለመክተት የተደረገ ሙከራ ነው›› በማለት አጣጣለች፡፡ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ከ2 ቀናት በፊት ባወጣው መግለጫ በኢትዮጵያ፣ በግብፅና በኤርትራ መካከል እየተባባሰ የመጣውን ውጥረት በከፍተኛ ስጋት በቅርበት እየተከታተለው መሆኑን ማስታወቁ ይታወሳል፡፡
በመግለጫው 3ቱም የህብረቱ አባል አገራት ውጥረቱን ሊያባብሱ ከሚችሉ ድርጊቶች ወይንም መግለጫዎች እንዲቆጠቡ ጥሪ አቅርቦ የዲፕሎማሲ መስመሮችን ክፍት እንዲያደርጉና ችግሮቻቸውን በሰላማዊ ውይይት እንዲፈቱም አሳስቦ ነበር፡፡ መና የተሰኘው የግብፅ መንግስታዊው የዜና አገልግሎት አንድ ከፍተኛ የግብፅ መንግስት ምንጭን ዋቢ አድርጎ ባቀረበው ዘገባ ‹‹በአፍሪካ ህብረት መግለጫ ተደንቀናል›› ማለታቸውን አስታውቋል፡፡ ምንጩ ጨምረውም ‹‹በአፍሪካዊ ማንነቷ የምትኮራውና የአፍሪካ ህብረት መስራች የሆነችውን ግብፅ ወደኢትዮጵያ ውስጣዊ ጉዳይ ጎትቶ ለመክተት የተደረገ ያልተገባ ጥረት ነው›› በማለት መግለጫውን እንዳጣጣሉት ገልፆ፣ የአገሪቱ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ በአለም አቀፍ ህግ፣ እንዲሁም በተመድና በአፍሪካ ህብረት ቻርተሮች መርሆዎችና አላማዎች ላይ የተመሰረተና በሉአላዊ አገራት ውስጣዊ ጉዳይ ጣልቃ አለመግባት መሆኑን መናገራቸውን ዘግቧል፡፡
እኚህ የመንግስት ምንጭ አክለውም ‹‹በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ወቅታዊ ቀውስ ውስጣዊ ጉዳይ እንጂ ከግብፅ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም፡፡ በውስጥ ያሉ ችግሮችን መንስኤ ትኩረት ለማስቀየር የሚደረጉ ሙከራዎች መቅረት ይገባቸዋል›› ማለታቸውንም መና አስታውቋል፡፡

“ ሮናልዶ የፖርቹጋል ትልቁ ምልክት ነው ” ፈርናንዴዝ
ፖርቹጋላዊው አማካይ ብሩኖ ፈርናንዴዝ ክርስቲያኖ ሮናልዶ የብሔራዊ ቡድኑ መልክት ነው ሲል ተናግሯል።
“ ሮናልዶ ሁልጊዜም የብሔራዊ ቡድኑ ትልቁ ምልክት ይሆናል “ ያለው ፈርናንዴዝ “ እሱ የአለም እግርኳስ ተምሳሌት ነው "ብሏል።
አክሎም “ እሱ የሁሉም ፖርቹጋላዊ አክብሮት ይገባዋል ፤ ምንም ቢፈጠር ትልቁ ምልክታችን መሆኑ እንደማይቀየር ነግሬዋለሁ “ ሲል ገልጿል።
ብሩኖ ፈርናንዴዝ አያይዘውም በብሔራዊ ቡድኑ ውስጥ መከፋፈል እንዳይኖር ሁለቱም ወገኖች ነገሮችን በጥሩ ሁኔታ እንዲፈቱ ጠይቋል።
“ ሮናልዶ በእርግጠኝነት በታሪክ ከታዩ ታላቅ ተጨዋቾች መካከል እና ፖርቹጋላዊያን ልብ ውስጥ የተረጋገጠ ቦታ አለው “ ፈርናንዴዝ

ቦይንግ 737 MAX 10 ምን ገጠመው?
#ethiopia | ቦይንግ አዲስ የሶፍትዌር ችግር ቢገጥመውም FAA በረራዎች እንዲቀጥሉ ፈቀደ።
የአሜሪካው የፌዴራል ሲቪል አቪዬሽን አስተዳደር (FAA) በቦይንግ 737 MAX የበረራ ኮምፒውተሮች ላይ የተገኘው የሶፍትዌር ችግር ምንም አይነት የደህንነት ስጋት እንደማያመጣ ገለጸ።
ይህ ውሳኔ ለዓመታት የፈቃድ መዘግየት ሲገጥመው ለቆየውና የ MAX ተቋም ትልቁ አውሮፕላን ለሆነው MAX 10 ይፋዊ ማረጋገጫ ለማግኘት መንገድ የከፈተ ሆኗል።
ተመሳሳይ ሶፍትዌር ለሚጠቀመው MAX 7 ተጠቃሚ አየር መንገዶችም እፎይታን ሰጥቷል ተብሏል።
አስተዳደሩ አብራሪዎች የአውሮፕላኑን ሙሉ ተቆጣጣሪነት የመያዝ ብቃት ስላላቸው እና የኮክፒት መረጃዎች ግልጽ በመሆናቸው ሶፍትዌሩ የበረራ አደጋ አያደርስም ብሏል።
ቦይንግ ለአብራሪዎች የማብራሪያ መመሪያ የሚያወጣ ሲሆን FAA ደግሞ ለአለም አቀፍ አቪዬሽን ተቆጣጣሪዎች ማብራሪያ እንደሚልክ ገልጻል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #getutemesgen #aviationnews #boeing #boeing737max

4 days ago
ለፖርቹጋል ብሄራዊ ቡድን ጠንካራ መልዕክት መላክ ፈልጌ ነው።ለሮናልዶ የሚገባውን ክብር እና ዋጋ ካልሰጡት አለም ላይ ብዙ የሚያደንቁት ሰዎች አሉ።
ሆይሉንድ ለምን የሮናልዶን የደስታ አገላለፅ እንደተጠቀመ ሲጠየቅ ብለው [Globesoccer] ይሄን ፖስት አድርገው ነበረ ሰሞኑን።
ግሎብሳከር ይሄንን መረጃ በኢንስታግራም ገፁ ፖስት ቢያረግም ተጨዋቹ ሆይሉንድ ኮሜንት ስር እኔ ይሄን አላልኩም በማለት አዋርዷቸዋል።
Damn😀
@Bisrat_Sport_433et @Bisrat_Sport_433et 🚨 ራስመስ ሆይሉንድ በፖርቹጋል ላይ ጎል ካስቆጠረ በኋላ የክርስቲያኖ ሮናልዶን “SIUUUU” ያደረገበትን ምክንያት ገልጿል፦ “ለፖርቹጋል ቡድን ጠንካራ መልዕክት ማስተላለፍ ፈልጌ ነበር፤ እናንተ ለክርስቲያኖ የሚገባውን ዋጋ ባትሰጡትም፣ በዓለም ዙሪያ በእሱ የተነሳሱ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችና ህፃናት አሉ።” “ክርስቲያኖ ሁሌም ለሁሉም ሰው ምሳሌ እና አርአያ ሆኖ ይቀጥላል።” @Bisrat_Sport_433et …

ግሪክ ለአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት የጥገኝነት ጥያቄዎችን በጊዜያዊነት ማገድ እንዲችሉ ጥያቄ አቀረበች
ግሪክ የህብረቱ ስደተኞች ስምምነት ትልቅ መሻሻል ቢያሳይም ድንገተኛ ቀውሶችን ለመቆጣጠር በቂ አለመሆኑን ገልጻለች። ኔዘርላንድም ይህንን ሀሳብ በመደገፍ እንደ ሴኡታ ያሉት መጠነ-ሰፊ የመጤዎች መረባረብ ከጥገኝነት ይልቅ እንደ ድንበር አስተዳደር ጉዳይ ሊታይ ይገባል ብላለች።
ባለፈው ሐምሌ ወር መጨረሻ ላይ ብቻ ከ72 ሺህ በላይ ስደተኞች ወደ ስፔን ከሰሜን አፍሪካዊ ግዛት ሴኡታ መግባታቸው ይገመታል። ምንም እንኳን አብዛኞቹ ቢመለሱም፣ 10 ሺህ ያህሉ አሁንም በመቆየታቸው በአውሮፓ ከተሞች ውስጥ ጠንካራ እርምጃዎችን እንዲወሰዱ ጥሪዎች እንዲጠናከሩ አድርጓል።
የአውሮፓ ህብረት የስደተኞች ኮሚሽነር ማግኑስ ብሩነር ፍልሰት የጸጥታ ጉዳይ ሊሆን እንደሚችል በመግለጽ፣ ከአለም አቀፍ ህግጋት እና መሰረታዊ መብቶች ጋር የተጣጣመ ድንበር የመጠበቅ አቅም እንደሚያስፈልግ አንስተዋል።
በዚህም ስብሰባ ላይ አባል ሀገራት ከአውሮፓ ህብረት ውጪ የመመለሻ ማዕከላት እንዲያቋቁሙ የሚያስችል አዲስ ደንብ ጸድቋል። ሩዋንዳ ከበርካታ የአውሮፓ ሀገራት ጋር እንደዚህ አይነት ማዕከልን አስተናግዳለው በሚል ቀዳሚ ውይይቶችን አድርጋለች። ግሪክ፣ ኔዘርላንድ፣ ጀርመን፣ ኦስትሪያ እና ዴንማርክን ያካተተው የአምስት ሀገራት ቡድን በጥር 2027 ዓ.ም. ዝውውሮችን ለመጀመር እቅድ ይዟል።ይህ ዜና አውሮፓ ከስደተኞች ጋር በተያያዘ ከጊዜ ወደ ጊዜ ጥብቅ እና ድንበርን አጥብቆ የመቆጣጠር አቅጣጫን እየተከተለች መሆኑን ያሳያል።
ትግስት ላቀው

(ዘ-ሐበሻ ዜና) ኢልሀን ኡመር ‹‹የኢትዮጵያ ህዝብ ሰላምና ፍትህ ያስፈልገዋል›› አሉ፡፡ የአሜሪካ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል የሆኑት ኢልሀን ኡመር የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ መግለጫ አውጥተዋል፡፡ የሚኖሶታ ግዛት ተወካይ የሆኑት ኢልሀን ኡመር መግለጫውን ያወጡት ከካሊፎርኒያው ተወካይ ጆን ጋራሚድኒ ጋር በመሆን ሲሆን በመግለጫቸው ‹‹ባለፈው ሳምንት በትግራይ ክልል እርዳታ ጭኖ ይጓዝ በነበረ ተሸከርካሪ ላይ የኢትዮጵያ ጦር የፈፀመውን ጥቃት ጨምሮ በኢትዮጵያ ውስጥ እየጨመረ የመጣው ግጭት በጣም አሳስቦናል›› በማለት ጀምረዋል፡፡
ሲቀጥሉም ‹‹በሰሜን ኢትዮጵያ የጠመንጃን ድምፅ ባስቆመው የ2022ቱ የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ሁሉም አካላት ግጭትን ለማቆም፣ ሲቪሎችን ለመጠበቅ፣ ለተጎዱ ሰብአዊ አገልግሎት እንዲሰጥ ለመፍቀድና ለሰብአዊ መብት ጥሰቶች ተጠያቂዎችን ለህግ በማቅረብ የሽግግር ፍትህ ለማስፈን ቁርጠኛ መሆናቸውን የገለፁበት ነበር›› በማለት ጠቅሰው ይሁንና ስምምነቶቹ አለመከበራቸውንና ሁኔታዎቹ አለመሟላታቸውን አስታውቀዋል፡፡ በማስከተልም እየጨመረ የመጣው ግጭት መላውን አገሪቱንና ቀደም ባለው የአሜን ኢትዮጵያ ጦርነትና በሱዳን ግጭት የተጎዳውን ቀጠናውን ጭምር አደጋ ላይ የሚጥል መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
በዚህ ውስጥ ሰላማዊ ሰዎች የጥቃቱ ሰለባ እንደሚሆኑ ጠቁመውም ‹‹በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ሁሉም አካላት በአስቸኳይ ለሰላም ድርድሩ ቁርጠኛ እንዲሆኑና በፕሪቶሪያ ስምምነት ስር ያሉ ሀላፊነቶቻቸውን እንዲወጡ እናሳስባለን›› ብለዋል፡፡ የኢትዮጵያ ጎረቤት አገራትና አለም አቀፍ ማህበረሰቡም ውጥረቱን ለማርገብና ሰላምን ለማመቻቸት መስራት እንደሚገባቸው ጥሪ አቅርበዋል፡፡ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የተፈጠረውን ግጭት ለማስቆምና በዚህ ሀላፊነት ያለባቸውን ተጠያቂ ለማድረግ ከሁሉም አካላት ጋር እንዲሰራ ያሳሰቡት እነኢልሀን ኡመር በማጠቃለያቸውም ‹‹የኢትዮጵያ ህዝብ ሰላምና ፍትህ ያስፈልገዋል›› ብለዋል፡፡

9 ቀናት ቀሩት
የ2026 የአፍሪካ ኢምፓክት አዋርድ (2026 African Impact Award) የክብር ምሽትን አብረው ለማሳለፍ ይፈልጋሉ?
በዝግጅቱ ላይ የእራት ግብዣ፣ የሙዚቃ ዝግጅት፣ የክብር ዘበኞች ትርኢት እና የዋናው ዝግጅት ተሻጋሪ ለውጥ ያመጡና ተፅዕኖ የፈጠሩ ተሸላሚዎች ዕውቅና አሰጣጥ ይከናወናል።
የተዘጋጁት የትኬት ቁጥሮች ውስን ሲሆኑ፤ ከሽያጩ የሚገኘው ገቢ በሙሉ ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች ድጋፍ ይውላል።
የ2026 የሽልማቱ ተቀባዮች፦
ፕሮፌሰር ዶናልድ ጆሃንሰን (Prof. Donald Johanson) — ታዋቂው የፓሊዮአንትሮፖሎጂስት እና የ"ሉሲ" (ድንቅነሽ) ግኝት ባለቤት
ፖል ቴርጋት (Paul Tergat) — የረጅም ርቀት ሩጫ አትሌት እና የቀድሞ የዓለም ማራቶን ሪኮርድ ባለቤት
እዮብ "ጆ" ማሞ (Eyob "Joe" Mamo) — ስኬታማ የንግድ ባለቤት እና ሥራ ፈጣሪ
አለምፀሐይ ወዳጆ (Alemtsehay Wedajo) — በኪነ-ጥበብ፣ ባህል እና በበጎ አድራጎት ዘርፍ የጎላ አስተዋጽኦ ያበረከቱ
ማክዳ አሰፋ (Makda Assefa) — የፈር ቀዳጅ ሚዲያ መሪ
ቀን፦ እሁድ፣ ጥቅምት 1 ቀን 2019 ዓ.ም (October 11, 2026)
ሰዓት፦ ከምሽቱ 11:30 (5:30 PM)
ቦታ፦ ሜትሮ ፖይንትስ ሆቴል (Metro Points Hotel)፣ ሜሪላንድ - 8500 Annapolis Road, New Carrollton, MD 20784.
ለበለጠ መረጃ እና ትኬት ለመግዛት፦ https://www.eventbrite.com...
4 days ago
ኤዲን ዤኮ ዛሬ ማታ ከስዊድን ጋር ለቦስኒያ የመጨረሻውን የአለም አቀፍ ጨዋታውን ሲያደርግ በቦስኒያዋ ሳራዬቮ የሚታየው ውብ ገጽታ! 🥹
በዋና ከተማዋ ግዙፍ ህንፃ ላይ የዤኮ ማሊያ ተሰቅሏል!
ጄኮ ለመጀመሪያ ጊዜ ለአገሩ የተሰለፈው እ.ኤ.አ. በ2007 ሲሆን፣ እስካሁን በ151 ጨዋታዎች ላይ በመሳተፍ አስደናቂ የሆነ 73 ግቦችን አስቆጥሯል!
በ40 ዓመቱ አገሩን በአለም ዋንጫው በአምበልነት ከመራ በኋላ፣ ይህ አስደናቂ የአለም አቀፍ የእግር ኳስ ጉዞ ወደ ፍጻሜው እየደረሰ ነው!
Thank You, Edin 💙💛
@Bisrat_Sport_433et @Bisrat_Sport_433et

አሐዱ መድረክ ክፍል-2
ሰላም የሰው ልጅ ሕልውና፣ የሀገር እድገት እና የትውልድ ዕጣ ፈንታ መሠረት ነው። ነገር ግን ዛሬ በሀገራችን ሰላም ሲነሳ፣ ማህበራዊ መከፍፈሎች ሲበራከቱ እና የሞራል እሴቶች ሲፈተኑ እናያለን። ይህንኑ የሰላም እጦት ከሥረ-መሰረቱ ለመፈወስና የሕዝብን ቁስል ለማከም የሀይማኖት ተቋማት ሚና ምን ሊሆን ይገባል? ፖለቲካን ከእምነት ተቋማት ነጥሎ የማስኬዱ ፈተናስ የት ደርሷል?
በዛሬው የአሐዱ መድረክ ፕሮግራማችን፤ ሰላም የሚል ርእስ ያለውን መጽሐፍ ለንባብ ያበቁት፣ ለሰላም ግንባታ ላበረከቱት አስተዋጽኦ አለም አቀፍ/ሀገራዊ እውቅና የተሰጣቸው፣ የኢትዮጵያ ሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ጸሐፊ ሊቀ ትጉኃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ እንግዳችን ናቸው ፡ ቃለ ምልልሱን እንደትከታተሉት ጋብዘናችኋል።
https://youtu.be/qK6CPplnz... የምንጣላው ከራሳችን ጋር ነው||Ahadu TVሰላም የሰው ልጅ ሕልውና፣ የሀገር እድገት እና የትውልድ ዕጣ ፈንታ መሠረት ነው። ነገር ግን ዛሬ በሀገራችን ሰላም ሲነሳ፣ ማህበራዊ መከፍፈሎች ሲበራከቱ እና የሞራል እሴቶች ሲፈተኑ እናያለን። ይህንኑ የሰላም እጦት ከሥረ-መሰረቱ ለመፈወስና የሕዝብን ቁስል ለማከም የሀይማኖት ተቋማት ሚና ምን ሊሆን ይገባል? ፖለቲካን ከእምነት ተቋማት ነጥሎ የማስኬዱ ፈተናስ የት ደርሷል?
በዛሬው የአሐዱ መድረክ ፕሮግራማችን፤…

Comments